TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
H.R. 6600

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የፕሬዜዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ፣ ኤርትራና ከግጭት ጋር ተያይዞ ለደረሱ በደሎች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ ግለሶች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ አስተዋውቀዋል።

ረቂቅ ሕጉ ተፈጻሚ ቢሆን የጦርነቱ ተሳታፊዎች ተገደውም ቢሆን ወደ ድርድር እንዲመጡ ያስችላል የሚሉ እንዳሉት ሁሉ፤ በረቂቅ ሕጉ ላይ የፕሬዜዳንት ባይደን ፊርማ ቢያርፍ ፤ ተራው ዜጋ ሰርቶ እንዳይገባና በልቶ እንዳይደር ከፍተኛ ጫና ያሳድራል የሚሉ አሉ።

የረቂቅ ህጉ ምን ይዘት አለው ?

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት አጥብቀው የተቃወሙት ይህ ረቂቅ ሕግ በፕሬዝደንት ባይደን የሚጸድቅ ከሆነ አሜሪካ በደኅንነት፣ በፋይናንስ/በኢንቨስትመንት እና በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ በሁለቱ አገራት ላይ አዲስ ማዕቀብ ትጥላለች።

'የኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ሕግ' በሚል ርዕስ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፤ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ በደኅንነት እና ፀጥታ ላይ የምታደርገው ድጋፍ ላይ ገደብ ይጥላል።

ይህ ረቂቅ ሕግ ተፈጻሚ ከሆነ አሜሪካ ተሰሚነቷን እና ድምጽ የመስጠት መብቷን ተጠቅማ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ብድሮች ወይም የብድር ማራዘሚያዎች እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፎች እንዳያገኙ እንድትሰራ ይጠይቃል።

ይህ ብቻ አይደለም፤ በኢትዮጵያ መረጋጋት እና የዲሞክራሲ ሥርዓት እንዳይኖር ምክንያት ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ የንብረት እግድ እና የቪዛ ማዕቀቦች ይጣላሉ።

@tikvahethiopia
#ይበቃል

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ፍትህን እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

ዘመቻው ሳዑዲ ያሉ ዜጎቻችን እምነበረድ ላይ ለብሰው የሚተኙትን ጥቁር ፌስታል በመልበስ አጋርነት የሚገለፅበት ነው።

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በርካታ ዜጎቻችን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።

የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽም እንዲሰጥ የሚጠየቅበት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ነው እየተካሄደ ያለው።

ዘመቻው ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።

በሳዑዲ አረቢያ ስላሉት ወገኖች የሰማነው ተስፋ ሰጪ ዜና እስካሁን የውሀ ሽታ እንደሆነ ነው።

የማህበራዊ ሚዲያው ዘመቻው በሳዑዲ አረቢያ ላሉት ወገኖች ድምፅ የሚኮንበት፣ ዜጎቻችን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ድምፅ የሚኮንበት ፣ በሳዑዲ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር / መሰረታዊ የሆነው የእስረኞች አያያዝን ተግባራዊ እንዲያደርግም ግፊት የሚደረግበት ነው።

የአረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆናችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በይበልጥ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሳዑዲ አረቢያ ባለልስጣናት እና የዓለም መንግስታት የዜጎቻችንን ስቃይ እንዲያውቁ መልዕክቶችን በማጋራት ድምፅ ሁኑ።

#ይበቃል
#ጥቁር_ፌስታል

#الحرية_للسجناء_الاثيوبيين
#العدالة_للسجناء_الاثيوبيين

ፎቶ፦ ሶሻል ሚዲያ

@tikvahethiopia
#ተከልክሏል

ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳይወስድ የ 'በጎ አድራጎት ኮሚቴ ' በማቋቋም ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እንዳይሰራ መከልከሉን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ ሳይኖራቸው የበጎ አድራጎት ኮሚቴ አቋቁመው በገንዘብ ማሰባሰብ ላይ የሚገኙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከባለስልጣኑ ፈቃድ በመውሰድ ወደ ህጋዊ አሰራር መግባት እንዳለባቸውም አሳስቧል።

ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ ተገቢ የሆነ ማጣራት በማድረግ አስፈላጊውን ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳይኖራቸው በህዝብ ስም በማንኛውም መንገድ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራዎችን መስራት የተከለከለ መሆኑን የገለጸው የባለስልጣኑ መረጃ፤ በህዝብ ስም የሚሰበሰብ ገንዘብ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይባክን የመከላከልና የመጠበቅ ስልጣን እንዳለው አመልክቷል።

#ENA

@tikvahethiopia
#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ እንዲደረግላቸው ውሳኔ አሳለፈ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ሴኔቱ በዛሬው ዕለት ከስዓት በፊት በነበረው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ከነበሩት መካከል የመምህራን የደረጃ እድገት እና የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች የጥሪ ሁኔታን የሚመለከቱ ነበሩ።

ሴኔቱ ከነባር የመጀመሪያ አመት ኤክስቴሽንና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በመቀጠል የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችል ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑ በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተማሪዎቹ እንዲጠሩ ውሳኔ አሳልፏል።

በሌላ አጀንዳ የመምህራንን የደረጃ እድገት ተመልክቶ 10 መምህራን ከጤና ኮሌጅ ፣ 1 መምህር ከግብርና ኮሌጅ በጥቅሉ 11 መምህራኖቻችን የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ የማወዳደሪያ መስፈርት ተመዝነው ከሌክቸረርነት ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ደረጃ ያደጉ በመሆኑ ሴኔቱ የደረጃ እድገቱን ገምግሞ አፅድቋል።

በደረጃ እድገቱ የተተካቱት መምህራን፦ ረ/ፕ አብዱ ሰይድ ሙሃመድ ፣ ረ/ፕ አደም ወንድሜነህ በላይ ፣ ረ/ፕ አዲሱ ጌቴ ንጋቱ ፣ ረ/ፕ አጃናው ነገሰ ፣ ረ/ፕ አስማማው ደምስ ብዙነህ ፣ ረ/ፕ አየልኝ መንገሻ ካሴ፣ ረ/ፕ ብርሃን አለምነው ታመነ፣ ረ/ፕ ብሩክ በለጠው አባተ ፣ ረ/ፕ ጌታሁን ፈንታው ሙላው ፣ ረ/ፕ ጌትነት ገደፋው አዘዘ እና ረ/ፕ ሙሃመድ አህመድ ይማም ናቸው።

መረጃውን ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#US_Embassy_AA

የሙሉ ጊዜ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆናችሁ እና አሜሪካ ውስጥ የልውውጥ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ይህ እድል ለእናተ ነው።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የ2022-23 የፉልብራይት የማስተማር ልቀት እና ስኬት (TEA) ፕሮግራም ማመልከቻ መቀበል እንደተጀመረ ዛሬ ገልጿል።

ስኬታማ የሆኑ አመልካቾች #ለ6_ሳምንታት የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና የክፍል ውስጥ ምልከታ ለማድረግ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ።

በአሜሪካ ቆይታቸው ከአስተናጋጅ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ወደ የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ፉልብራይት (TEA) በስቴት ዲፓርትመንት የትምህርት እና የባህል ጉዳዮች ቢሮ (ECA) የሚደገፍ ፕሮግራም ሲሆን በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በ #IREX የሚተዳደር ነው።

ለበለጠ መረጃ ፦ https://ow.ly/t4FO50HQPPe
ለማመልከት ፦ https://ow.ly/aIaK50HQPPc

የመጨረሻው ማመልከቻ ቀን እ.ኤ.አ የካቲት 27/ 2022 ወይም የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray #Afar #Amhara

ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?

#Tigray

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በኢትዮጵያ አፋጣኝ የሰብዓዊ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መረጃ #በአፋር ያለው ውጊያ የረድኤት አቅርቦቱን አሁንም እንዳስተጓጎለ ነው ብለዋል።

የአፋር ክልሉ ውጊያ ምግብ እና ሌሎች የዕርዳታ ቁሳቁሶች የሚያስፈልጋቸው ከ5 ሚልዮን በላይ ተረጂዎች ወዳሉበት ትግራይ ክልል ይላክ የነበረውን ዕርዳታ እንዳይደርስ አድርጓል ነው ያሉት።

በነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ፣ እንዲሁም የረድኤት አቅርቦት እጥረቱ የሰብዓዊ እርዳታ ሥራውን በእጅጉ መቀነሱን የተናገሩት ቃል አቀባዩ፣ ባለፈው ሳምንት አንድ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት ከ14 ሜትሪክ ቶን በላይ መድሃኒት ወደ ትግራይ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል። ይሁንና የነፍስ አድን ዕርዳታውን በአየር ማድረስ መቻሉ መልካም ቢሆንም መጠኑ ከሚያስፈልገው አንጻር ግን በእጅጉ ያነሰ ነው ነው ያሉት።

ዱጃሪች አክለውም ቁጥራቸው ስድስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ሕጻናትን መድረስ የቻለ የሁለተኛ ዙር የጸረ-ኩፍኝ ክትባት ዘመቻ በትግራይ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለው የነዳጅ እጥረት ሳቢያ የጤና ባለሙያዎች በአንዳንድ አካባቢዎች የክትባት አገልግሎት ለመስጠት እስከ 35 ኪሎ ሜትር በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የተወሰነ የምግብ ሥርጭት መቀጠሉን ተናግረው ካለፈው የጥቅምት ወር አጋማሽ አንስቶ ለ880 ሺህ ሰዎች ምግብ መታደሉን፤ ይህም መጠን በየሳምንቱ መድረስ የነበረበት ነው ብለዋል።

#Afar

በአፋር የቀጠለው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን ገልጠው ተረጂዎቹ አስቸኳይ ምግብ እና የጤና አገልግሎት ዕርዳታ ማግኘት አለባቸው” ብለዋል።

ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ወደ አካባቢው ለመድረስ ያላቸው ዕድል ግን የተገደበ መሆኑን ነው የተናገሩት። ቀደም ሲል ሊደርሱ በቻሉባቸው ከፊል የአፋር ክልል አካባቢዎች ባለፈው ሳምንት 85 ሺህ ያህል ሰዎች የምግብ እርዳታ ማግኘታቸውን ከጥቅምት ወር አጋማሽ አንስቶም የምግብ ዕርዳታ ማግኘት የቻሉት ሰዎች ቁጥር በጠቅላላው 500 ሺህ መድረሱን አስረድተዋል።

#Amhara

በአማራ ክልል ቁጥሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሰው ባለፈው ሳምንት መርዳት መቻሉን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Sekota

" ችግሩ እልባት የሚያገኘው ወደ ቀያችን ስንመለስ ብቻ ነው " - ተፈናቃዮች

በሰቆጣ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የፃግብጂ ወረዳ ተፈናቃዮች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እየደረሰ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ተፈናቃዮች ህፃናትና እናቶች በመጠለያ ችግር ለበሽታ እየተጋለጡ መሆኑን በመግለፅ የመጠለያ ችግር እንዲቀረፍ ፣ የህክምና አገልግሎት እንዲመቻች ከምንም በላይ ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ቀን ሩቅ እንዳይሆን ሲሉ ነው ጥይቄ ያቀረቡት።

" የተጋረጠብን ችግር ወቅቱ ያመጣው ቢሆንም ችግሩ እልባት የሚያገኘው ደግሞ ወደ ቀያችን ስንመለስ ብቻ ነው " ሲሉም ገልፀዋል።

" የፀጥታ ሀይሉ ፃግብጂን ነፃ ሊያወጣ ይገባል። " ያሉት ተፈናቃዮች " ይህ ካልሆነ የተፈናቃዮች ቁጥር አሁን ካለው ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ህዝቡን ለከፋ ርሃብና ችግር ይዳርጋል " ብለዋል።

የፃግብጂ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የት/ት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ደሳለኝ ተፈናቃዮቹ ባነሱት ጥያቄ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኃላፊው፥ " የእናንተ ጥያቄ የኛም ጥያቄ ነው። በተለይ የፃግብጂ ህዝብ ወደ አካባቢው እንዲመለስና ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖር ደጋግመን ጠይቀናል። የፃግብጂን ህዝብ ጥያቄ ችላ ያልንበት አግባብ የለም " ብለዋል።

ከመጠለያ ችግር ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ የመጠለያ ችግር እንዲፈታ የክልሉን መንግስት የጠየቅን ሲሆን የመጠለያ ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

ለተፈናቃዮች የመጣን ማንኛውም ዓይነት ድጋፍ ያለአግባብ የተጠቀመ አካል ካለ ህዝቡ እንዲጠቁምና ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረው እስከ አሁን 11 ሺ 136 ተፈናቃዮች ድጋፍ እንደሚሹ ለክልልና ፌደራል መንግስት ማሳወቃቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoH በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ትላንት የካቲት 1 ይፋ ሆኗል። ተመዛኞች ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ በ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እንዲሁም የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን እየተመለከቱ ነው። በሌሎችም የሙያ ዘርፎች ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤት በቅርብ ቀን ይፋ ይደረጋል ተብሎ…
#MoH

ከዛሬ የካቲት 4 ጀምሮ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤታቸው ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ከታህሳስ 21 - 27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከዛሬ የካቲት 04/2014 ዓ/ም ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ውጤት የመመልከቻ አድራሻ hple.moh.gov.et ላይ ሲሆን ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤት መመልከት ይቻላል።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማሩበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣ የጃንሜዳና ልሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት…
#update

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት በአሁን ሰዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ስብሰባ ተቀምጠዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አልተገኙም።

በስብሰባው ያልተገኙት ቀድሞ በተያዘው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከመስቀል አደባባይና ሌሎች የኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከሰቱ ችግሮች ዙርያ ዛሬ የካቲት 4 ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል።

በስብሰባው ላይ ከአቶ ዣንጥራር አባይ በተጨማሪ አቶ ጥራቱ በየነ የሥራ አስኪያጅ ፣ ዶ/ር ቀንአ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ፣ አቶ ተተካ በቀለ እና አቶ አለማየሁ እጅጉ ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፖርቲ ተገኝተዋል።

ፎቶ፦ EOTCTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት በአሁን ሰዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ስብሰባ ተቀምጠዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አልተገኙም። በስብሰባው ያልተገኙት ቀድሞ በተያዘው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል። ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ…
#Update

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የፊታችን ማክሰኞ በመንበረ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛሉ።

ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትም ቀጠሮ ተይዟል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

በስብሰባው ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ከሌሎይ ኃላፊዎች ጋር ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በዚህም ስብሰባው ከንቲባዋ በተገኙበት የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 8 እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ቋሚ ሲኖዶስ በሌሎች አጀንዳዎች ውይይቱን መቀጠሉ ተገልጿል።

ፎቶ፦ EOTCTV

@tikvahethiopia
#Sumuni

ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ መተግበሪያ " ስሙኒ " ምንድነው ? እንዴትስ ላግኘው ?

ትላንት " ስሙኒ " የተሰኘ ኩባንያ ከኮካ ኮላ ቢቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ በመተግበሪያ እንዲሁም በድህረገጽ በይፋ አስጀምረዋል።

ስሙኒ የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችንና ባለሃብቶች ማገናኛ በስራ ፈጠራ ስነምህዳር ውስጥ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚገናኙበት እና የሚተሳሰሩበት የኦንላይን መድረክ ነው።

መድረኩ የውጭ ኢንቨስተሮች በሀገር ቤት ስታርታአፖች ላይ መዋለ ንዋይ እንዲያፈሱ በማስቻል ምንዛሪ በማስገኘት እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት እድገት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ታምኗል።

በተጨማሪም በባለድርሻ አካላት መካከል የኢኮኖሚ ትስስርና ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ኮካ ኮላ ቤቭሬጅስ በስሙኒ መገናኛ መተግበሪያ በኩል በዚህ ዓመት ለ10 ስታርታፖች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር ስራ ማስጀመሪያ ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም 10,000 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን፣ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን እና አነስተኛ የንግድ ባለቤቶችን አቅም ለመገንባት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የክህሎትና የዕውቀት ድጋፍ በማድረግ ከሌሎች ኢንቨስተሮችን የማገናኘት ስራ ይሰራል፡፡

መተግበሪያውን እና ድረገፁን እንዴት ላግኘው ?

ድረገፁ : https://139.59.95.164/sumuni.net/index.php

መተግበሪያው : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sumuni.sumuni_new

@tikvahethiopia