TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 10,758
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 3,779
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 7
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,080

በአሁን ሰዓት 413 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EXCLUSIVE አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ ተብሏል። ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ሮይተርስ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከ9 ወራት የስልጣን ቆይታ በኋላ በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ መስማቱን ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር…
የአምባሳደር ፌልትማን ጉዞ ተሰርዟል ?

ሮይተርስ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በተያዘው ወር መጨረሻ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ዘግቧል (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለው ነገር ባይኖርም) ።

ይህ የተሰማው ትላንት ለሊት ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ እና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ እንደሚነጋገሩ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው።

ምንም እንኳን አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነት እንደሚለቁ ቢገለፅም የሀሙስ የኢትዮጵያ ጉዟቸው እንደተጠበቀ መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ሲለቁ ይተኳቸዋል የተባሉት በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደርነት ጊዜያቸውን የጨረሱት አምባሳደር ዴቪድ ሰተርፊልድ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የአምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በተመለከተ ምን አሉ ?

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፦

" የፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት አዲስ ጉዳይ አዲስ ነገር ይዞ ይኖራል ወይ የሚለው የሚመጡት እሳቸው ስለሆኑ የሚመጡበትን አጀንዳ ይዘው ሲመጡ ወቅቱም የገና በዓል ነው ከበዓሉም ጋር አስተሳስረን እንቀበላቸዋለን።

በፍቅር መቀበል ኢትዮጵያዊ ባህል ነው።

ስለዚህ አዲስ ነገር ይዘው መጡ አዲስ ነገር ይዘውም አልመጡ ያው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የረጅም ጊዜ የታሪክ ግንኙነት ባለቤቶች ናቸው የትኛውንም ሀሳብ ይዘው ከመጡ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ፤ ህዝቦቿን የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ኢትዮጵያ ትቀበላለች።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ፣ የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ፣ የኢትዮጵያን ልማት ኢትዮጵያን አለማቀፋዊ ተሳትፎ ፣ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት የሚገዳደር ከየትኛውም ወገን ይምጣ ከየት ኢትዮጵያ አትቀበልም።

ስለዚህ የፌልትማን መምጣት በዚህ አቅጣጫ መሰረት የሚፈፀም እና የሚመራ ይሆናል። "

@tikvahethiopia
#GeezWatches

🎁 እነሆ የገና ስጦታ አንድ ግዕዝ ሰዓት ሲገዙ ፤ ተጨማሪ አንድ ማሰሪያ በነፃ።🎁

የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀላሉ 👇
https://t.iss.one/geezwatches

@GeezWatchesjewelryBot

አድራሻችን መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድሞል 2ተኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 239። ለበለጠ መርጃ 0929157545 /0946663939 ይደውሉልን በየአሉበት ቦታ እናደርሳለን ።
#MedStore

Medsstore.et የህክምና እቃ አስመጪ እና አቅራቢ ነዎት?

እንግዲያዉስ አብረዉን ይስሩ በዲጂታል መድረካችን አማካኝነት ተደራሽነትዎን ያስፉ፡፡

አሰራርዎን ያዘምኑ ከጊዘው ጋር ይራመዱ፡፡

ድህረ ገጻችን https://medstore.et/

Join and Follow
Telegram Linkedin Facebook Twitter
#UPDATE😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦

🇫🇷 ፈረንሣይ ሀገር በኮቪድ-19 የተያዙ ነገር ግን ጥቂት ወይም ምንም ምልክት የሌላቸው የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከማግለል ይልቅ ህመምተኞችን ማከም እንዲቀጥሉ ፈቅዳለች። ውሳኔን የሰራተኞችን እጥረት ለመቅረብ የተወሰደ ነው። በፈረንሳይ የኮቪድ ወረርሽኝ ክፉኛ እየተስፋፋ ነው።

🇳🇱 ኦሚክሮን ዝርዘ በዋነኝነት እየተስፋፋ ነው በተባለበት ኔዘርላንድስ በአንድ ቀን ብቻ ሪከርድ ነው የተባለ 24,500 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

🇸🇪 የስዊድን ጤና ባለስልጣናት ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ምግብ ቤቶች ፣ የባህል ቦታዎች እና የመዝናኛ ማዕከላት ደንበኞቻቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባት መከተባቸውን የሚያረጋግጥ ዲጂታል ማረጋገጫ እንዲያሳዩ እንዲያደርጉ መክረዋል።

🇯🇵 የቶኪዮ ባለስልጣናት በከተማው እየተስፋፋ ከመጣው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ የጃፓን መንግስት የአደጋ ጊዜ እርምጃዎችን እንዲመልስ ሊጠይቁ ይችላሉ ተብሏል። ከእርምጃዎቹ መካከል በባር እና ሬስቶራንቶች የስራ ሰዓት ላይ የሚጣል ገደብ የሚጨምር ነው። ከተማይቱ 6ኛ ዙር ማርበል ሳያጋጥማት አልቀረም ተብሏል።

🇮🇱 እስራኤል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ አስመዝግባ የማታውቀውን ከፍተኛ ኬዝ አስመዝግባለች። በሀገሪቱ በአንድ ቀን 11,978 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

🇨🇳 በቻይና ዢያን ከተማ በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የምግብ እጥረት ስጋት በመፈጠሩ ነዋሪዎች ንብረታቸውን በምግብ እየቀየሩ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። በማኅበራዊ ሚዲያ በተለቀቁ መረጃዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ሲጋራዎችን እና የቴክኖሎጂ መገልገያዎችን በምግብ ሲቀይሩ ታይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመራውን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ቻይና ባለፉት 100 ዓመታት በCPC መሪነት ያስመዘገበችውን ትልቅ እድገት አድንቀዋል። ዓለም አቀፍ ህግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ አለም አቀፋዊ ስርዓት እንዲመጣ ቻይና ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል። ፕሬዜዳንት…
ዋንግ ዪ ኬንያ ይገኛሉ።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ትላንት የኤርትራ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ኬንያ ሄደዋል።

በኬንያ የሁለት ቀን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን ትላንት ሞምባሳ ኤርፖርት ሲደርሱ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪይቼል ኦማሞ ተቀብለዋቸዋል።

የዋንግ ዪ ጉብኝት በኬንያ እና በቻይና መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ስትራቴጂያዊ ትብብር ስምምነቶችን በመፈረም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እድል ይሰጣል ተብሏል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ ?

እዚሁ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከዚህ ቀደም ከፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ከ15 ጊዜ በላይ ዜጎቹ ሀገር ለቀው እንዲወጡ ሲወተውት ነበር።

ኤምባሲው አሁንም በዚሁ ጥሪው የቀጠለ ሲሆን ዛሬም " በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ እና የደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሊበላሽ ይችላል " በማለት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሀገር ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።

ይህ የኤምባሲው መልዕክት እንደሁል ጊዜው እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ሲሆን የኤምባሲው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ አስተያየት መስጫ የአሜሪካን ድርጊት በሚያወግዙ መልዕክቶች ተሞልቷል።

አሜሪካ ዜጎቼ ውጡ እያለች ባለችበት በዚህ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን / የአሜሪካ ዜግነትም ያላቸው የሌሎችም ሀገራት ዜጎች ለበዓል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ይገኛሉ።

የ " ደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ ነው " በሚል ዜጎቼ ውጡ እያለች የምትወተውተው አሜሪካ በአንድ በኩል ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን ከፍተኛ የስራ ኃላፊ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ዛሬ ወደኢትዮጵያ እንደምትልካቸው ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ኤምባሲ ሆነ ሌሎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ፤ ደህንነት አልተሰማንም ካሉም / ለሰራተኞቻቸው ምቹ ሁኔታ የለም ካሉ በየትኛውም ጊዜ መውጣት መብታቸው እንደሆነ ፤ ኢትዮጵያ ግን ሰላሟን፣ ደህንነቷን ይዛ እንደምትቀጥል የኤምባሲዎች መኖር የኢትዮጵያን ደህንነት እንደማያረጋግጥ ማሳወቋ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SUDAN

ሌ/ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን ሚመሩት የሱዳን ጦር ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሳያሳትፍ ለሱዳን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሾም እንደማይደግፉ አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ፣ ኖርዌይ እና የአውሮፓ ህብረት አስጠንቅቀዋል።

በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ላይ አሁንም ተቃውሞ እና የሚደርስበት ጫና ቀጥሏል።

የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ከቀናት በፊት በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል። ይህን ተከትክሎ የሱዳን መንግስት ሙሉ ለሙሉ በጦር ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደርገዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ🇪🇹የፊታችን እሁድ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ኢትዮጵያችን በመጀመሪያው ጨዋታ ከኬፕ ቨርዴ ጋር የምትፋለም ይሆናል።

ይህ ጨዋታ በ " ኦሌምቤ ስታዲየም " የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱን በደማቅ ሁኔታ ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የሀገራችን ልጆች ለዚሁ ትልቅ ውድድር ቀደም ብለው ካሜሮን ገብተው ጠንካራ ልምምድ እና ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ለአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን የሚገኙት የቲክቫህ ስፖርት አባላት በፎቶ እና በቪድዮ የተደገፉ መልዕክቶችን በ @tikvahethsport በኩል ይልኩላችኃል።

https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ስነ ስርዓትን እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ጋር እሁድ ጥር 1 ቀን የሚያደርጉትን ፍልሚያ በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በግዙፍ እስክሪን አብረን እንመልከት ይሎታል።

ምግቡ መጠጡ ሙዚቃው ሁሉም ተሰናድቶል። ከምሽቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ክፍት ይሆናሉ።

#መግቢያ_በነፃ

ቪዛ ካርድ የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ ኦፊሻል ስፖንሰር።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ https://t.iss.one/BoAEth

#አቢሲንያ #የሁሉም_ምርጫ #visa
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህውሃት ጋር ባላቸው ልዩ ልዩ ግንኙነት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲጣራባቸው ከነበሩ ግለሰቦች መካከል በድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ የጠየቁትን፣ ከፍተኛ ወንጀል ያልፈፀሙ እና ከእሥር ቢወጡም ለከተማዉ ስጋት የማይሆኑት በዋስ ከእስር እየተለቀቁ ነው ብሏል።

የተቀሩትንም እንደ ድርጊታቸው ክብደትና ቅለት እየታየ ወደፊት እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዋስ የተለቀቁ ግለሰቦች ወደፊት እንደ ጥፋታቸው በህግ እንደሚጠየቁ እና በህግ አካላት ጥሪ ሲደደረግላቸው የመቅረብ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሽብርተኛ ከተፈረጀው ቡድን ጋር ግንኙነት ማድረግ ሆነ የሽብር ቡድኑን ዓለማ ማራመድ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተረድቶ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት እና የመንግስት ምላሽ !

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ትላንት ረቡዕ ባወጣው ሪፖርት፤ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ የመብት ጥሰት መፈጸሙን ገልጿል።

ተቋሙ በሪፖርቱ፤ ከስደት ተመላሾቹ ላይ “የዘፈቀደ እስር እና እንግልት ደርሶባቸዋል፤ ደብዛቸውም ጠፍቷል” ብሏል።

የሂዩማን ራይትስ ዎች የስደተኞች እና የስደተኛ መብት ተመራማሪ ናዲያ ሃርድማን “በሳዑዲ እስር ቤት አሰቃቂ በደል የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች፤ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በማቆያ እስር ቤቶች እየተቆለፉ ይገኛሉ” ብለዋል።

ሙሉ ሪፖርቱ : https://www.hrw.org/news/2022/01/05/ethiopia-returned-tigrayans-detained-abused

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ሂዩማን ራይትስ ዎች በትላንትናው ዕለት ያወጣው ሪፖርት “ድርሰት ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የተቋሙ ሪፖርት “በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጫናዎች አካል ነው” ብለዋል።

“በሰፈር፣ በማንነት የተለየ እና የተጎዳ ሰው አልነበረም። እንደዚያ አይነት አሰራርም አልነበረም” ያሉት አምባሳደር ዲና ፥ “ሂዩማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያን በሚመለከት መዓት ድርሰቶች አሉት፤ ይሄም ከድርሰቶቹ አንዱ ነው” ብለውታል።

በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ ማብራሪያ የሚሰጠበት እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵየ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia