TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Egypt #Djibouti

ኢማኤል ኦመር ጌሌ ግብፅ ገብተዋል።

የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ናቸው የተቀበሏቸው።

በዛው ዕለት ሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚኖራቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

ፎቶ፦ የጅቡቲ ፕሬዜዳንት (ኢሳማኤል ኦመር ጌሌ)

@tikvahethiopia
#Djibouti #Ethiopia

የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ " ያሉ ሲሆን " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Djibouti #Ethiopia የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ…
#Ethiopia #Djibouti

ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትላንት ኢትዮጵያ የገቡት የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና ልዑካቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ልዑካቸው ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ፦

👉 የንግድ፣
👉 የግብርና ሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣
👉 የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣
👉 ቱሪዝም፣
👉 ኢነርጂ እና ሌሎች ዘርፎችን ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ባማከለ መልኩ ማጠናከር ይገኙበታል።

መረጃውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደተገኘው መረጃ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ ለማልማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የነዳጅ ማከማቻው በጂቡቲ ነጻ ወደቦች ቀጠና የሚካሄድ ነው።

የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራቱ ወደፊት በዘርፉ ለሚያካሂዱት ልማት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ እድሎችን ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#Djibouti

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጅቡቲ ያቀኑት ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ በደረሱበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው።

ትላንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ኢማኤል ኦማር ጌሌ ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ፣ ናይሮቢ እንደነበሩ ይታወሳል።

#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት፣ እ.ኤ.አ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል ሽልማታቸውንም በጅቡቲ ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia
#Djibouti

45 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

ከየመን 310 ስደተኞችን በመጫን በጉዞ ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው እስካሁን ባለው 45 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ እንዳስታወቀው አደጋው በሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር አካባቢ ካለው የባህር ዳርቻ 150 ሜትሮች ርቆ ነው የተከሰተው።

ከሰኞ ጀምሮ በተደረገው ፍለጋ በህይወት የተረፉ 115 ሰዎች ማዳን እንደተቻለ የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጥበቃ አሳውቋል።

እስካሁን በርካታ ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን ጅቡቲ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ አሊ የሱፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካኑ በጅቡቲ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

Via The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia