TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNICEF

UNICEF በደብረ ብርሃን ከተማ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ለአዳዲስ ተፈናቃዮች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ህይወት አድን የሆነ የተመጣጠነ ምግብና ውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ UNICEF አሳውቋል።

UNICEF የህጻናት ህይወት፣ ጤና፣ ደህንነት እና የወደፊት ህይወት ንፁህ ውሃ እና ንፅህና ሳያገኙ ሲቀሩ አደጋ ላይ ይወድቃል ብሏል።

@tikvahethiopia
#Borana #Dawa

የIOM WASH ቡድን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ለህብረተሰቡ የውሃ ማጓጓዝ ስራ መስራት መጀመሩን ገልጿል።

IOM በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በከባድ ድርቅ ለተጎዱ እና አስተማማኝ የውሃ ምንጭ ለሌላቸው ማህበረሰቦች ውሃ የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

ይህንን ተግባር ለማከናወን የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ልግስና ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሊ ክልል በዳዋ ዞን በከፋ ድርቅ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ሰዎችም በውሃ እጥረት ለከፋ ችግር መጋለጣቸው መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል። አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን…
" የትኬት ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ ይችላል " - አምባሳደር ፍፁም አረጋ

1 ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደሀገር ቤት በታኅሣሥ 29 ቀን 2014 እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት አገር ወዳድ ወገኖች የአውሮፕላን ትኬት እየገዙ መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ፍፁም ፥ የትኬት ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ እንደሚችል በሎስ አንጀለስ ላይ ተገኝተው መረዳት እንደቻሉ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

"አየር መንገዳችን ፣ ሆቴሎችና ሌሎችም የመስተንግዶ ተቋማት ጥሪውን የሚመጥን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ይታየናል" ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሏን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ…
" እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስን ጨምሮ ሁሉም አገልጋይ መነኮሳት ጉዳት አልደረሰባቸውም " - ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት እንዳልደረሰበት ገልጿል።

ህወሓት ካሳለፍነው ነሀሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ላሊበላ ከተማን ተቆጣጥሮ ቆይቶ ነበር፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በወሰዱት መልሶ ማጥቃት አካባቢውን ከሶስት ከሚልቁ ወራት በኋላ መልሰው ተቆጣጥረዋል።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ቅርሶቹ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከአል ዓይን ኒውስ የተጠየቁት የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ፥ ላሊበላ ከተማን ጨምሮ አካባቢው ከህወሃት ወረራ ነጻ መሆኑን ተከትሎ የቅርሱ ደህንነትን በተዘዋዋሪ ማጣራታቸውን ተናግረዋል፡፡

" እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስን ጨምሮ ሁሉም አገልጋይ መነኮሳት ጉዳት አልደረሰባቸውም " ብለዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች እና አመራሮች ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ገልጸዋል፡፡

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ከ43 ዓመት በፊት ነበር በተመድ የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) በዓለም የሚዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው፡፡

መረጃው ከአል ዓይን ኒውስ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
" CNN ኢትዮጵያ እና ዓለምን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል " - ቢልለኔ ስዩም

CNN አዲስ አበባ ተከባለች በማለት የዓለም ማህበረሰብን ከዋሸ አንድ ወር እንደሆነው የጠ/ሚር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ቢልለኔ ስዩም በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አማፅያንን ከዋና ዋና ስፍራዎች እያጸዳ ባለበት ወቅት ፣ CNN በመረጃ ማዛባት ያለመረጋጋት መሳሪያ ሆኖ በማገልገሉ ኢትዮጵያ እና ዓለምን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#iTena

ህብረተሰቡ መሰረታዊ የጤና ትምህርት በነፃ የሚያገኝበት ማዕከል ተመረቀ፡፡

" የጤና ትምህርት ለሁሉም " በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የማኅበረሰብ የጤና ስልጠና ማዕከል ለህብረተሰቡ ውስብስብ ባልሆኑ እና አሳታፊ በሆኑ መንገዶች የጤና እውቀት ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል፡፡

iTena(አይ ጤና) በተሰኘው ተቋም የሚሰጠው ይህ አገልግሎት ከዚህ ቀደም የጤና ትምህርት የጤና ባለሙያ መሆን ለሚፈልግ ሰው ብቻ መሰጠቱን የሚያስቀር መሆኑም የተቋሙ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እየሩሳሌም ማሞ ገልፀዋል።

በማዕከሉ ወሳኝ የጤና ትምህርት ናቸው ተብሎ በሚታመንባቸው ፦
- የጤናማ አመጋገብ ስርዓቶች፣
- የስነ ተዋልዶ እና የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርቶች፣
- እንደ ስኳር እና የደም ግፊት አይነት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣
- እንደ ሰሞነኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አይነት ተላላፊ በሽታዎች እና ሌሎችም ትኩረት ተደርጎ ይሰጣል ብለዋል።

በተጨማሪ ከበሽታ መከላከያ ትምህርቶች ባሻገር በተለያዩ በሽታዎች ለተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች በሽታው የባሰ ጉዳት እንዳያደርስባቸው ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና አጠቃላይ ማንቃት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች እንደሚሰጡም አሳውቀዋል።

ይህም በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሕይወታቸው የሚያልፍ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የተነገረው፡፡

iTena(አይ ጤና) በ አራት ሃኪሞች የተመሰረተ እና ለማህበረሰቡ የቆመ ድርጅት መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ከዚህ አገልግሎት በተጨማሪም የህክምና ጥሪ ማዕከል፣ የቤት ለቤት ህክምና እነዲሁም እና ተቋማት ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎትን በመስጠት ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡

(በጋዜጠኛ አሸናፊ)

@tikvahethiopia
#በድጋሚ

ቴሌግራም ላይ Tikvah-Marketና Tikvah-Mart በሚል በአጭበርባሪዎች የተከፈቱ እንጂ ትክክልኛ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ያሉ አይደሉም።

ገፆቹ በመቶ ሺዎች ሚቆጠሩ ሰዎች ያሉባቸው መሆኑን የተመለከትን ሲሆን ሁሉም ድርጊታቸው ከቲክቫህ ጋር የማይገናኝ እና ስራቸውም በስማችን ማጭበርበር ነው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከመሰል አጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ በድጋሚ አደራ እንላለን።

በዚሁ አጋጣሚ በየዕለቱን የቲክቫህ አባል እየሆናችሁ ለምትገኙ በሺዎች የምትቆጠሩ ቤተሰቦቻችን በኛ ስር ያሉት ትክክለኛ ገፆች የሚከተሉት ናቸው ፦

🕊 @tikvahethiopia (ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethmagazine (ከ240 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethsport (ከ145 ሺህ በላይ አባላት ያሉት)
🕊@tikvahuniversity (ከ103 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethAFAANOROMOO (ከ19 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 ቲዊተር twitter.com/tikvahethiopia?s=09

NB : ቲክቫህ ኢትዮጵያ Face book ሆነ አሁን ላይ አገልግሎት የሚሰጥ የYou Tube አካውንት በስሙ የለም።

ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ሰብዓዊነትን ያስቀደሙ እና ሀገራቸው ኢትዮጵያን የሚያከብሩ እንዲሁም የሚወዱ ዜጎች መሰባሰቢያ መድረክ ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ክንውኖች ዙሪያ የእርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ ይደረግበታል።

ከየትኛውም የፖለቲካ ፣ የብሄር፣ የሃይማኖት ውግንና የራቀ ሲሆን ኢትዮጵያን እንደሀገር ያከበሩና ሀገሪቱን አደጋ ላይ የማይጥሉ የተለያዩ አመለካከቶች እንዲሁም አስተሳሰቦች ያሏቸውን ቤተሰቦቹን የሚያሰባስብ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች፤ ለገና በዓል ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ እንግዶች ቅናሽ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው።

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ንግድ ዘርፍ ማህበር፤ ለመጪው የገና በዓል ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ እንግዶች በስሩ የሚገኙ ሆቴሎች ልዩ ቅናሽ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡን www.ethiopiainsider.com ዘግቧል።

ማህበሩ ጥሪውን ያቀረበው 170 ገደማ ለሆኑ ሆቴሎች መሆኑን ተገልጿል።

ማህበሩ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ባሰራጨው ደብዳቤ፤ የማህበሩ አባል የሆኑ ሁሉም ሆቴሎች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ እንግዶች የተለየ ቅናሽ እና አቀባበል እንዲያደርጉ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በቴፒ ከተማ የእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በደ/ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን በተለይ በየኪ ወረዳ እና ቴፒ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር በእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ ለመፍታት ያለመው የእርቅ እና የሰላም መድረክ በቴፒ ከተማ በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል። @tikvahethiopia
#TEPI

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሀዘኑን ገልፆ ለደረሰው ጉዳትና እና ህዝብ ላይ ለደረሰው በደል ይቅርታ ጠይቋል።

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ ዛሬ በከተማው በነበረ የሰላም ኮንፈረንስ መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል።

ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ ባሰሙት ንግግር ፥ ባለፉት ዓመታት በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸው ለደረሰው ጉዳናት፣ የህዝብ በደል ይቅርታ ጠይቀዋል።

ከመለያየትና መቃቃር ለውጥ እንደማይመጣ ያነሱት ከንቲባው በመፈቃቀርና በመቻቻል ከሠራን ቴፒ ከተማ እንዲሁም ዞኑ ለሁሉም ይበቃል ብለዋል።

በቴፒና አካባቢዋ ሠላም እንዲሰፍን ከፍተኛ ሚና ለተወጡ ባለድርሻ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ጫካ ሸፍተው ከነበሩት ውስጥ ሁለቱ የታጠቁትን መሣሪያ ለፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስረክበው ፤ በህዝቡ ፊት ቀርበው ይቅርታ ጠይቀው ከህዝቡ ጋር መቀላቀላቸው ተገልጿል።

ሌሎችም በዚህ መልኩ የታጠቁትን ለኮማንድ ፖስቱ በሠላም እያስረከቡ ከህዝቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።

ተጨማሪ የዛሬው የሰላም ኮንፈረንስ በተመለከተ ከደቡብ ምዕራብ ክልል ኮሚኒኬሽን የተገኘውን መረጃ በዚህ https://telegra.ph/SWER-12-04 መመልከት ይቻላል።

@tikvahethiopia
ላሊበላ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መውደሙ ተገለፀ።

የታሪካዊቷ እና የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ላሊበላ ከተማ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጿል።

የጋይንት ጋሸና ግንባር ኮማንድ ፖስት የህወሓት ቡድን የኤርፖርቱን መሰረተ ልማት እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ማውደሙን አሳውቋል።

የላሊበላ ከተማ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋሏ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia