" ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ከሌሎች የፀጥታ ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ሰራዊቱን በአግባቡ እየመሩ ይገኛሉ " - የአማራ ክልል ፖሊስ
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህብረተሰቡ በሀሰተኛ ወሬ እንዳይታለል አሳሰበ።
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን ከህወሓት ጋር ግንኙነት ስለአላቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል በሚል የሚነዛው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን አስገንዝቧል።
ኮሚሽኑ ወሬውን 'በሬ ወለደ' ወሬ ነው ያለ ሲሆን ፥ " በህወሓትና ለሆዳቸው ባደሩ ተላላኪ ቅጥረኞቹ አማካኝነት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር ተመልክተናል " ብሏል።
ጥቂት ግለሰቦችም ባለማወቅም ይሁን ባለማወቅ አጋርተውታል ሲል ገልጿል።
" እውነታው ግን ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች የፀጥታ ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ሰራዊቱን በአግባቡ እየመሩ ይገኛሉ " ሲል አሳውቋል።
የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ፥ ሁሉም አካል መሰል የሀሰት ወሬዎችን ከማጋራቱ በፊት መረጃው ከሚገኝበት ቦታ ወይም ከመረጃው ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ስለወጣው መረጃ ትክክለኛነት በመጠየቅ መረዳት ይገባል ሲልም አስገንዝቧል።
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከሀሰት ወሬ እንዲጠነቀቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
" መዋሸታችሁን አቁሙ፤ እዚህ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ፤ አፍጋኒስታን እዚህ የለችም " - ላውረንስ ፍሪማን
ከ30 ዓመታት በላይ የአፍሪካን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ በመተንተን የማታወቁት አሜሪካዊው የአፍሪካ ፖሊሲ ተመራማሪ ላውረንስ ፍሪማን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ላውረንስ ፍሪማን አዲስ አበባ መግባታቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፥ " መዋሸታችሁን አቁሙ፤ እዚህ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ፤ አፍጋኒስታን እዚህ የለችም " ብለዋል።
የኢኮኖሚ ተንታኝ እና ተመራማሪው የአሜሪካ መንግስት እና ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ከከፈቱት የስነልቦና ጦርነት በቀር ሁሉም ነገር አዲስ አበባ ውስጥ የተረጋጋ ነው ብለዋል።
" ባርና ሬስቶራንቶች በምሽትም ጭምር ክፍት ናቸው ፤ ሆቴሎችም ስራ ላይ ናቸው " ያሉት ፍሪማን " ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ የመጣሁበት አውሮፕላን መቀመጫዎች በመንገደኞች ለመሙላት የተቃረቡ እንደሆነ ታዝቢያለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።
ፍሪማን ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ሁሉም ነገር እንደሁል ጊዜው ሰላማዊ እና የተረጋጋ እንደነበር የተናገሩ ሲሆን " መዋሸታችሁን አቁሙ በተሳሳተ መረጃ ማደናገራችሁን አቁሙ፤ የስርዓተ መንግስት ለውጥም እዚህ አያስፈልግም " ብለዋል።
Credit : ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WFP
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶች እየጨመሩ መሆኑን ገልጿል።
በአፋር ክልል ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከ30% በላይ መሆኑንም አመልክቷል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ከሚገኙ ማህበረሰቦች፣ ከክልሉ ባለሥልጣናት እና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ወሳኝ የሆነ የምግብ ድጋፍ ለማድረስ በቅርበት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

#ሪፖርት
Afar Region | Conflict Situation
የአፋር ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህወሓት በክልሉ ላይ በፈፀመው ወረራ በ4 ዞኖች (21 ወረዳዎች) 377,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና በአሁን ሰዓት በክልሉ 1.3 ሚሊዮን ህዝብ ለችግር ተጋልጧል ሲል አሳውቋል።
- በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ376,502 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።
- ከ205,178 በላይ ሰዎች ከአውሲራሱ፣ ከብላቲራሱ፣ ከፋንቲራሱ እና ከሃሪራሱ ዞኖች አዲስ ተፈናቃዮች ናቸው።
- ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ተፈናቃይ የተመዘገበው ከጭፍራ (42156)፣ አዳአር (33,696)፣ ዳዌ (30,000)፣ ሃዳሌላ (21,000)፣ ሳማሮቢ (18,000) እና ተላሌክ (23,288) ነው። (እኤአ በህዳር 2021)
- መፈናቀሉ አሁንም በአውሲራሱ፣ ቀብላቲራሱ፣ ፋንቲ ራሱ እና ሃሪራሱ ዞኖች እንደቀጠለ ነው።
- በአጠቃላይ በግጭት ምክንያት የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎች ውስጥ ወደ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ለችግር አጋልጧል።
(የአፋር የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል)

#Update
በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት አውድ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተቋቋመው የሚኒስቴሮች ግብረ-ሀይል ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
ግብረ ኃይሉ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።
* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

" የሰላዮች ልዑካን እንጂ ታዛቢዎች አልነበሩም " - ኒኮላስ ማዱሮ
በዓለም ላይ አነጋገሪ ከሚባሉት የሀገራት መሪዎች አንዱ የሆኑት የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ትላንት በሀገራቸው ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው የሰጡት ቃል መነጋገሪያ ሆኗል።
በቬንዝዌላ ባለፈው ሳምንት ክልላዊ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ፕሬዜዳንት ማዱሮ ይህንን ምርጫ ለመታዘብ የተላኩትን የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አባላትን “ሰላዮች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
የማዱሮ ይህን ውግዘት ያሰሙት ታዛቢዎቹ በአራት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዋሚ እጩዎች የተሳተፉበት ምርጫ ካለፉት አመታት በተሻለ ሁኔታ የተካሄደ ነበር ካሉ በኃላ ነው።
ይሁን እንጂ በምርጫው በአስተዳደራዊ ምክንያቶች በእጩዎች ላይ የዘፈቀደ እገዳዎች፣ የምርጫ ማእከላት መዘግየቶች እና "በዘመቻው ውስጥ የመንግስት ሀብቶችን መጠቀምን" በተመለከተ ያሉ ክፍተቶችን ታዛቢዎቹ አንስተዋል።
የገዢው ሶሻሊስት ፓርቲ መሪ ማዱሮ " የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት ለማበላሸት ፈልገው አልቻሉም " ብለዋል ።
ማዱሮ ፥ " የሰላዮች ልዑካን - ታዛቢዎች አልነበሩም! በነጻነት በሀገሪቱ ዙሪያ እየተዘዋወሩ የሀገሪቱን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህይወት እየሰለሉ ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።
በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በተላለፈው ስርጭት ፕሬዜዳንት ማዱሮ ምርጫው "እንከን የለሽ፣ ቆንጆ" ነበር ብለዋል።
የታዛቢ ልዑኩ ለፕሬዜዳንቱ ውግዘት ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

" በአንዳንድ አካባቢዎች የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አይመለከትም " - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እንደማይመለከት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ገለጸ።
አሁን ላይ ባለው ሀገሪቱን የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢታወጅም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡ ተግባራዊ አይደረግም ተብሏል።
ይህ የሆነው በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና ስለሚያሳድር እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችን ወደ ኪሣራ ስለሚያስገባቸው መሆኑ ተገልጿል።
የተቀመጠው ሰዓት እላፊ ገደብ ሁሉንም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት ታውቆ ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ስራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ ተጠቁሟል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#NO_MORE በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል :: የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል :: የዛሬው ሰልፍ…
#SouthAfrica
ባለፈው ሳምንት በ22/11/2021 በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠራዉ #Nomore ንቅናቄ ምላሽ በመስጠት በበብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ኤንባሲ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚታወስ ነው።
ዛሬ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሐይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ መሐበር አመራሮች እና ሌሎች አፍሪካዊያን የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፋ ላይ የዉጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸዉን እንዲያቆሙ የተጠየቅ ሲሆን በተለይም የተሳሳቱና አላማቸዉ ሐገር ማወክን ያደረጉ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰልፈኞቹ አሳስበዋል።
የዛሬውን ሰልፍ የተባበሩት ኢትዮጵያ መሀበረሰብ መሀበር ያዘጋጀው ሲሆን ማህበሩ ከዘር ከፖለቲካ ከሃይማኖት የፀዳ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሀገር ወዳዶች የመሠረቱት ማህበር ነው።
በዛሬው ሰልፍ ላይ ኤርትራውያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ዜጎች ተሳትፈዋል።
FAYA(Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዪ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የካሜሮን እና የኮትዲቭዋር ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ግለሰቦቹ በጋራ በመሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ የእንግዳ ማረፊያ ውስጥና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት ነው በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ያስደረገው።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ ፦
- 107 ሺህ 330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብር፣
- የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣
- ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣
- ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣
- ፈሳሽ ኬሚካሎች፣
- የወረቀት መቁረጫ፣
- በርካታ ቾክ፤ በርካታ ወረቀት፣
- 9 ሞባይል ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁሶች መያዛቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
Credit : #ENA