TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,145 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 226 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
" የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚፃረር ማንኛውም እንቅስቃሴ አጥብቄ አወግዛለሁ " - ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ

ከሰሞኑን የሰላምና ልማት ማዕከል (PDCI) ካዘጋጀው የኦንላይን ውይይት ቪድዮ ጋር በተያያዘ ስማቸው መነሳቱ እንዳሳዘናቸውና ይህንንም እንደማይቀበሉት ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ ገለፁ።

ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ ፥ " ለሀገሬ እና ለህዝቤ ያለኝን ያልተገደበ ፍቅር እና ሰላምን በመሻት በሃምሌ 2020 ከበርካታ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ጋር በፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ አስተባባሪነት የቀረበልኝነን የሰላም ኢኒሼቲቭ ተቀላቀዪ ጥያቄ ተቀብያለሁ " ብለዋል።

አክለው ፥ " በእነዚህ ጥረቶች እስከ ጥቅምት 2020 ድረስ ተሳትፌያለሁ እናም ከአንድ አመት በላይ የማንኛውም የPDCI ስብሰባ ተሳታፊ አልነበርኩም። PDCIም ወዲያውኑ ስሜን ከቦርዱ እንዲያነሳና ከPDCI እና ተዛማጅ ተግባራቶቹ እኔን እንዲያስወጣኝ ጠይቄያለሁ " ሲሉ አስረድተዋል።

" እኔ የየትኛውም የፖለቲካ ቡድን አባል ሆኜ አላውቅም " ያሉት ፕሮፌሰር ሰናይት ፥ " የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረር ማንኛውም እንቅስቃሴን አጥብቄ አወግዛለሁ " ብለዋል።

" ለሀገሬ እና ለህዝቤ ያለኝ ቁርጠኝነት የማይናወጥ ነው " ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አሉ። አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ይህ ያሉት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው። " በኢትዮጵያ የተደቀነው አደጋ አፍሪካን የማንበርከክ ዓላማ ጭምር ያነገበ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሙከራ ነው " ያሉት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ፥ " " ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት…
" እግር ላይ ወድቀን ለምነናል ፤ እኔ አባቴ እግር ላይ ወድቄ አላውቅም ግን ሌሎች እግር ላይ ወድቂያለሁ " - አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ

በመላው አለም የሚታወቀው አንጋፋው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ሌሎች ታወቂ ሰዎች ዛሬ ማለዳ በተደረገ ሽኝት የጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጥሪ በመቀበል ወደ ግንባር መዝመታቸው ተገልጿል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ፥ ስለሰላም የተከፈለን ዋጋ ለረገጠ እና ሀገርን ለማፍረስ ለተነሳ ጠላት ምላሹ ሀገራዊ በመሆኑ ወደግንባር መዝመቱን ለሚዲያዎች በሰጠው ቃል አሳውቋል።

" ሀገር ሲባል ነው የተነሳነው። ከዚህ በፊት ሰላም ይስፈን፣ ፍቅር ይሁን፣ እርቅ ይሁን እያልን ዞረናል፣ ለምንነናል፣ እግር ላይ ወድቀን ለምነናል። እኔ አባቴ እግር ላይ ወድቄ አላውቅም ግን ሌሎች እግር ላይ ወድቂያለሁ፤ ይህ ሁሉ ስላልሆነ ነው ተነስተን የምንወጣው ፤ ለሌላ ለምንም አይደለም ሀገር መፍረስ የለበትም! የለበትም! የለበትም! " ሲል ተናግሯል።

አትሌት ኃይሌ ከኢትዮጵያ በፊት እኔ ልውደቅ የሚለው ሀሳቡ እንደሆነ ተናግሮ ሌሎችም ይሄንን ይረዱልኝ ሲል ጠይቋል።

" አሁንም ደጋግሜ የምነግራቸው ከኢትዮጵያ በፊት ልሞት፣ ልወድቅ፣ ልነሳ ነው የምሄደው ፤ ስለዚህ አደራ ነው የምለው እባካችሁን ተረዱን ፤ ይሄንን መረዳት ከቻልን ብቻ ነው ኢትዮጵያን የምናስከብረው " ብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው መርሃግብር ላይ ከሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በተጨማሪ ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ወደግንባር ለሚያደርጉት ጉዞ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

@tikvahethiopia
ዶ/ር እሌኒ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት ተነሱ።

ዶክተር እሌኒ ገ/መድህን ከዛሬ ኅዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ ፥ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት ኅዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን በምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት አቋም ማዘኑን ገልጿል።

ዶ/ር እሌኒ ፥ በገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባል ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

በመሆኑም የገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤቱን ውሳኔ መነሻ በማድረግና ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በመንግስት እና በህዝብ ታምነው የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ ይሁንታ የሰጠውን መንግስት ቀይሮ የሽግግር መንግስት ስለማቋቋም በግልጽ ምክክር ሲያደርጉ በመገኘታቸው ከዛሬ ህዳር 19/2014 ዓ/ም ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

* ሚኒስቴሩ ያወጣው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርታቸውን የሚያከፋፍሉላቸው ወኪል የንግድ ድርጅቶችን ስምና አድራሻ #በአስቸኳይ ለመንግስት እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላለፈ።

ትዕዛዙን ያስተላለፈው የማዕድን ሚኒስቴር እንደሆነና ሚኒስቴሩ ይህን ትዕዛዝ ሊያስተላልፍ የቻለው ከንግድ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ኮሚሽን ጋር በመሆን ከሲሚንቶ ምርትና የግብይትና ሥርጭት ሥርዓት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ለጀመረው የጋራ ጥረት መረጃ ለማግኘት እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተፈርሞ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የተላከው ደብዳቤ ፥ " የፋብሪካችሁን የሲሚንቶ ምርት በወኪልነት የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች ስም ዝርዝርና የሚገኙበትን አድራሻ በመግለጽ በአስቸኳይ እንድትልኩልን " ሲል ያመለክታል፡፡

በሲሚንቶ ምርት ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈታ አዲስ መመርያ እስኪዘጋጅ ድረስም ለአዲስ የምርት አከፋፋይ ወኪሎች ፋብሪካዎች ፈቃድ እንዳይሰጡ ደብዳቤው እንደሚያሳስብ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም " - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

የሱዳን ጦር በድንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮቼ የኢትዮጵያ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ተገደሉብኝ ሲል ክስ አሰምቷል።

የሱዳን ጦር ትላንት ባወጣው መግለጫ ፤ “በአል-ፋሻቃ የሚገኘውን የመኸር ምርትን ለመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሃይሎቻችን… በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ሚሊሻዎች በቡድን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ ገበሬዎችን ለማስፈራራት እና የመኸር ወቅትን ለማበላሸት ፈልገው ነበር” ሲልም ነው ክስ ያሰማው።

የሱዳን ጦር በመግለጫው ላይ ምን ያህል ወታደሮቹ እንደተገደሉበት ባይገልፅም ሮይተርስ የዜና ወኪል የወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበ በጥቃቱ ቢያንስ 6 ወታደሮች ተገድለዋል።

ይህንን መረጃ ከትላንት ጀምሮ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ሲሆን ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥብቅ መሆኑን በመግለፅ ጎረቤት ሀገሯን ሱዳንን የምታጠቃበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ገልፀዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ጁላ "የድንበር ጭቅጭቅ አለ ይሄ የድንበር ጭቅጭቅ በሰላማዊ መንገድ ነው መፈታት ያለበት የሚል ፅኑ አቋም አላት ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ አሁን ከጁንታው ጋር ጦርነት ላይ እያለች በጣም ብዙ ትርፍ ኃይል ኖሯት ሱዳንን የምታጠቃበት አይነት ቁመና ላይ አይደለችም ያለችው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሬትን በተመለከተ በሰላምና በድርድር በህግ ይመለሳል ብለዋል።

ጄነራል ብርሃኑ ፥ " ብዙ ጊዜ የመሬት ጭቅጭቅ መጨረሻ ፍርድ ቤት ነው የሚሄደው ይሄን ስለምናውቅ እኛ ሱዳንን የመተናኮል ፍላጎት የለንም ነገር ግን ሱዳን የመተናኮል ምልክቶች እያሳየች ነው፤ ጁንታውን በብዛት አስገብታለች እንደገና የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ እየሰራች ነው እናውቃለን፤ እነሱ የላኳቸው ኃይሎች እየመጡ እየደመሰስናቸው ነው።

የራሳችንን ተላላኪ መደምሰስ እንጂ ለምን ትልካላችሁ ብለን ከሱዳን ጋር ወደአታካራ መግባት አንፈልግም ፤ ከሱዳን ጋር ግጭትም ጦርነትም አንፈልግም፤ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል ነው የምንፈልገው በጣም ይሻሻላል ብለንም እናስባለን።

እንዳንድ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት የማይወክሉ ግን በሌላ ሶስተኛ ወገን የተገዙ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግንኙነት ለማበላሸት የሚሰሩ አሉ ፤ እነማን እንደሆኑም ለይተን እናውቃቸዋለን፤ ታሪክ ይፈርዳል፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝብ ችግሩን በህዳሴ ግድብም ይሁን በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Niger

ትላንትና ቅዳሜ በምዕራብ ኒጀር ከቡርኪነፋሶ በኩል በአጀብ የገቡ የፈረንሳይ ወታደሮች ከተቃዋሚዎች ጋር በፈጠሩት ግጭት ቢያንስ 2 ሰዎች ሲገደሉ 18 መቁሰላቸውን የኒጀር መንግስት አስታውቋል።

የፈረንሳይ ጦር ሰራዊት ደግሞ ፥ ወታደራዊ አጀቡ በገጠመው ተቃውሞ የተነሳ ከቡርኪናፋሶ ለአንድ ሳምንት ያህል መውጣት አቅቶት እንደነበርና በዛው መቆየቱን ገልጿል።

የፈረንሳይ ወታደሮች አሸባሪዎች የሚወስዱትን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም በሚል ነው በቡርኪናፋሶ ተቃውሞ የገጠማቸው።

አሸባሪዎች ቡርኪናፋሶን እና በአካባቢው ያሉ አገራትን እንዲያጠቁ የፈረንሳይ ጦር ድጋፍ እያደረገ ነው በሚልም ነው ጦሩ ተቃውሞ የገጠመው።

ምንም እንኳን ከአንድ ሳምንት እገታ በኃላ ኒጀር የገባው የፈረንሳይ ጦር በኒጀርም ኃይለኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

እየተፈጸሙ ያሉ የሽብር ጥቃቶች በመጨመራቸው ምክንያት የአካባቢው አገራት ዜጎች ፈረንሳይ ጦሯን እንድታስወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

ፈረንሳይ ወደ ቀድሞ የቅኝ ግዛቶቿ ወታደር ማዝመቷ ቡርኪናፋሶ፣ ኒጀር እና ሌሎችም የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#StateofEmergencySomalia ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው። እየተባባሰ በመጣው ወቅታዊ የድርቅ ሁኔታ ላይ የሃገሪቱን ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሮብል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አውጀዋል፡፡ “ሃገራችን በድንገተኛ ሰብዓዊ አደጋ ላይ ትገኛለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያጋጠመውን አስከፊ…
#Somalia

ጎረቤታችን ሶማሊያ በድርቅ ክፉኛ እየተጎዳች ነው።

በደቡብ ሶማሊያ ውስጥ በድርቅ ከተመቱ አካባቢዎች አንዱ በሆነው በጌዶ ክልል ፣ ሉቅ ወረዳ የ5 ልጆች እናት በረሃብ መሞቷ ተነግሯል (ፎቶ ከላይ ተያይዟል) ።

ከአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ እንደተሰማው በረሃብ ህይወቷ ያለፈው እናት የሳምንት እድሜ ያቃስቆጠረ ልጇን ጡት ስታጠባ ነበር።

እንደ ጋሮዌ መረጃ ከብቶቻቸውን በድርቅ በማጣታቸው ምክንያት ነው ህይወቷ ያለፈው እናት ከምትኖርበት አካባቢ ተሰዳ ወደ ሉቅ የገባችው።

ሶማሊያ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች። በሀገሪቱ 2. 3 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Somalia

በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በሰዎች እና በከብቶች ላይ ጉዳት እየደረሰ በሚገኝባት በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ አንዳንድ የደቡብ እና መካከለኛ ክልሎች ዴየር ዝናብ እንደጣለ ተሰምቷል።

ሶማሊያ ውስጥ ባለፉት ሶስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ያልዘነበ ሲሆን በተለይ ጁባና ሸበሌ ወንዞች የውሃ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ በሀገሪቱ ያለውን ድርቅ እንዳባባሰው የUN መረጃ ይጠቁማል።

ፎቶ ፦ SNTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም " - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የሱዳን ጦር በድንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮቼ የኢትዮጵያ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ተገደሉብኝ ሲል ክስ አሰምቷል። የሱዳን ጦር ትላንት ባወጣው መግለጫ ፤ “በአል-ፋሻቃ የሚገኘውን የመኸር ምርትን ለመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሃይሎቻችን… በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ሚሊሻዎች በቡድን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ ገበሬዎችን ለማስፈራራት እና የመኸር…
" የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ እየተባለ የሚነዛው ወሬ #ሀሰተኛ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ዶ/ር ለገሰ ፥ " አሸባሪው ኃይል በተለያየ መልኩ ሱዳን ውስጥ የሚያሰለጥናቸውን ሰርጎ ገቦች በተለያየ ቦታ በተለይም በመተማ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜያት ያስገባል ፤ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ሰርጎ ገቦች ይገባሉ፤ በዚህ መሰረት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰርጎ ገቦች ፣ ሽፍታዎች እና አሸባሪዎች በዛ መስመር ገብተው ነበር በዛ መስመር የገባውን ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻ መቷቸዋል ፤ ደምስሷቸዋል " ብለዋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚነዙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ፈፅሟል የሚለው መሰረተቢስ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፥ " ቢኖረው ኖሮ የሱዳን ኃይሎች ወረው በግድ የያዙት መሬት አለ ፤ ይሄንንም በሰላማዊ ሁኔታ በውይይት እና በድርድር እንፈተለን ብሎ የተቀመጠ ነው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ አዲስ የመጣ የተከሰተ ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን የህወሓትን ተልዕኮ ለማስፈፀም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ሽፍታዎችን ደምስሰናቸዋል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
የተቀጣጠለው የ #NoMore ንቅናቄ ፦

አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና በሀገራቱ ሚዲያዎች የሚሰራውን የኢትዮጵያን ህዝብ የማሸበር የሀሰተኛ መረጃ ዝውውር በመቃወም በተለያዩ ሀገራት #NoMore በሚል በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኤርትራ ዜጎች የተቀውሞ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

ትላንት እሁድ እንዲሁም ቅዳሜ በአይርላንድ (ደብሊን ፣ ኮርክ፣ ጋልዌይ) ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኖርዌይ፣ ጣልያን የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል።

በተጨማሪ በአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት መቀመጫ ዋሽንግቶን ዲሲ ትላንት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ የውሥጥ ጉዳዮች እጇን እንድትሰበስብና በሀገሪቱ ያሉት ሚዲያዎች በሀሰተኛ መረጃ ህዝብን ከማሸበር እንዲታቀቡ ተጠይቋል።

#NoMore ዘመቻ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እየተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህ መካከል በጉልህ የሚጠቀሱት የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው።

የቻይና መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዌንቢን ፣ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁዋን ቹኒንግ፣ በሊባኖስ የቻይና ኤምባሲ ኮንሱላር ካኦ ይ የ #NoMore በቃ ንቅናቄ ድጋፋቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ያንፀባሩቁ ናቸው።

ባለስልጣናቱ፥ " O ዴሞክራሲ፤ በስምሽ ስንት ወንጀሎች ተፈጸመ "ብለዋል።

ባለስልጣናቱ ከመልእክታቸው ጋር ያያዙት ምስል " ለUS ኢምፔሪያሊዝም ቀጣዩ ማን ነው?" የሚል ሲሆን አፍጋኒስታን፤ ኢራቅ፤ ሊቢያ እና የመን ወድመዋል፤ ማነው ተረኛው? "ሲልም ያጠይቃል።

ከፖለቲካ ሰዎች በተጨማሪም ሴኔጋላዊ-አሜሪካዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ ኤኮን #NoMore ንቅናቄን ተቀላቅሏል።

@tikvahethiopia