TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል። 11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል። ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው   @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።

የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል።

የስልጣን ገደብም የተቀመጠ ሲሆን÷ በተለያየ ምክነያት ከጊዜያቸው ቀድሞ ሊለቁ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ረጅም ጊዜ ቢቆዩ ከ10 ዓመት እንዳይበልጥ ተመላክቷል።

የብዝሓ ማዕከል ወይንም ዋና ከተማ እንዲኖርም ተደንግጓል፣ የትኞቹ ከተሞች እንደሚሆኑ በዝርዝር ህግ በም/ ቤት እንዲወሰንም በህገ መንግስቱ መጠቀሱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈጉባኤ ፤ ወይዘሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል። ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። @tikvahethiopia
#Update

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ም/ርዕስ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ በክልልና በሀገር ደረጃ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የውሃና መስኖ ሚንስቴር ዴኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

ም/ርዕስ መስተዳደሩ በጉባኤው አባላት ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

@tikvahethiopia
#WFP #USAID

USAID በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ ከአገሪቱ ሊወጣ ነው የተባለ ሐሰት ነው ሲል አስታወቀ።

ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

USAID እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቀጠሉን አስታውቋል።

የተቋሙ ቃል አቀባይ ሬቤካ ክሊፍ ፥ " የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሠራተኞቻችን ከአገሪቱ ቢወጡም፤ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፦የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ኮምቦልቻ ውስጥ ያሉት የሰብዓዊ እርዳታ ማከማቻ መጋዘኖቹ መዘረፋቸውን ዛሬ ገልጿል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ ፥ ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ድርጅት በአማራ ክልል ኮምቦልቻ የሰብዓዊ እርዳቃ እንዲያቀርብ ፍቃድ አግኝቷል ብለዋል።

ድርጅቱ ባደረገው ቅድመ ግምገማ መሠረት በርካታ ንብረቶቹ መውደማቸውን እና መጋዘኖች ውስጥ የነበረ እህልም መዘረፉን አሳይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እንደሚዘምቱ ካሳወቁ በኃላ የአብን አመራር እና የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል። አቶ ክርስቲያን…
#ETHIOPIA

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አሉ።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ይህ ያሉት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው።

" በኢትዮጵያ የተደቀነው አደጋ አፍሪካን የማንበርከክ ዓላማ ጭምር ያነገበ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሙከራ ነው " ያሉት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ፥ " " ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት ናት ፤ ኢትዮጵያን በማንበርከክ የጥቁር ሕዝቦችን አኩሪ ታሪክ ለመቀማት የተቀናጀ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ እየተከናወነ ይገኛል" ብለዋል።

ከዚህ አኳያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ክብር ወደ ግንባር መዝመታቸው አገሩን ከሚወድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተል ጥሪ አቅርበዋል።

መላ አፍሪካዊያን ትግሉ የሁሉም ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን በመገንዘብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

አትሌት ኃይሌ ፦ "ኢትዮጵያን ብለን ተሸንፈን አናውቅም፤ ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ናት" ሲሉ ነው የተናገሩት።

በአንድ ወቅት የጎበኟት የቱሪስት መናኸሪያ የነበረችውን የሶሪያዋ አሌፖ ከተማ በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ምክንያት ወደ ፍርስራሽነት መቀየሯን ጠቅሰዋል።

"በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ላይ ይህን መፍቀድ የለብንም" ያሉት አትሌት ኃይሌ ፤ " ከዚህ አንጻር ከደጀንነት ባሻገር በግንባር በመሰለፍ ጭምር አገሬ በምትፈልገኝ ቦታ ለማገልግል ዝግጁ ነኝ " ብለዋል ለኢዜእ በሰጡት ቃላቸው።

@tikvahethiopia
#StateofEmergencySomalia

ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው።

እየተባባሰ በመጣው ወቅታዊ የድርቅ ሁኔታ ላይ የሃገሪቱን ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሮብል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አውጀዋል፡፡

“ሃገራችን በድንገተኛ ሰብዓዊ አደጋ ላይ ትገኛለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያጋጠመውን አስከፊ ድርቅ ሰላባዎች እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ባለችው ጎረቤት አገር ሶማሊያ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡

በርካቶች ለችግር መዳረጋቸውን የተመድ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማስተባበሪያ አስታውቋል፡፡

በሶማሊያ ባለፉት ሶስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ያልዘነበ ሲሆን በተለይም ጁባ እና ሸበሌ ወንዞች የውሃ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ የድርቁን ደረጃ እንዳባባሰው ድርጅቱ አክሏል፡፡

የድርቅ መጠኑ በተለይም ከቀጣዩ ታህሳስ ወር ጀምሮ እስከ መጋቢት ድረስ እንደሚባባስ የገለጸው ድርጅቱ ተጎጂዎችን ለመርዳት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

Credit : Al AIN News

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,049 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 231 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ አባላት እና ደጋፊዎች ወደ ግንባር ለመዝመት ውሳኔ አሳለፉ።

የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህዳር 14/ 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል።

ፓርቲው በአስቸኳይ ስብሰባው አሁን ላይ እንደሀገር ያለንበት ወቅት ሁሉን አቀፍ አርበኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን ግምት ውስጥ በመክተት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ አባላትና ደጋፊዎቹ ግንባር ድረስ በመዝመት፣ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠትና ሌሎችንም ተግባራት በመከወን የሀገርን ህልውና የማረጋገጥ ስራ ለመስራት ውሳኔ አሳልፏል።

* የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ Jeune Afrique በተባለ የፈረሳይኛ መፅሄት እና የእንግሊዝኛ ትርጉሙ The Afirca Report ላይ እሳቸውን የተመለከቱ ፅሁፎች መውጣታቸውን መመልከታቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቷ ከጋዜጠኛው ጋር ተገናኝተው እንደማያውቁ አሳውቀዋል።

ፅሁፉ ዛሬ መውጣቱ የአጋጣሚ ጉዳይ አይመስለኝም ያሉት ፕሬዜዳንቷ " በዚህ ደረጃ በኃላፊዎች መካከል መከፋፈል ያለ ለማስመሰል የተደረገ ሙከራ ነው" ብለውታል።

ይህንን አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል፦

"የተለያዩ አገሮች ከገጠማቸው የፖለቲካ ችግሮችና የእርስ በእርስ ጦርነቶች እንዲወጡ የሰራሁ በመሆኔ አገራችን ዛሬ ያለችበትን ሁኔታ በአግባቡ እረዳለሁ። እንደሁላችንም ልቤ ተሰብሯል። የእርስ በእርስ ጦርነት በጣም አስከፊ ነው።

ሌላው መታወቅ ያለበት ከእንደዚህ ያለ ሁኔታ ለመውጣት One size fits all የሚባል ነገር የለም። መላውን መፈለግ የእኛ ፋንታ ነው።

ኢትዮጵያ ካለችበት አስከፊ ሁኔታ ለማውጣት ከምንግዜውም በላይ ሁሉንም ልጆቿን ትሻለች። መንግስትን የሚመሩት ጠ/ሚ አቢይ አህመድ በመሆናቸው ያስቀመጡትን አቅጣጫ ተቀብለን በምናውቀው፣ በሰራንበት፣ በሙያችን እየተረባረብን እንገኛለን።

በግጭት አፈታት ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ፍለጋ ሁሌም ያለጉዳይ ነው። በዚያኑ መጠን ሳይወዱ ጦርነት መግባትም እንዳለ መዘንጋት የለበትም። ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ መንግስት ለንግግር ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጡ ይታወሳልና የሰላም ፍለጋው አካል መሆኑ ለእኛ እንግዳ አይደለም።

ብዙ አትናገሪም እባላለሁ። በየአጋጣሚው መናገሬ አልቀረም። ከወር በፊት ፓርላማን ስከፍት ያልኩትን ልድገም <<እጆቻችን በእሾህ ተወግተው እየደሙ ከሆነ ፅጌረዳዋ እሩቅ አይደለችም ማለት ነው>> እየደማን ነው። ፅጌረዳዋ እንዳትርቀን እንተባበር እንበርታ።"

@tikvahethiopia