#WolaitaSodo
ከጥቂት ቀናቶች በፊት በአርባምንጭ ከተማ የምስረታ ጉባኤውን ያደረገው የ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት " ዛሬ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ያካሂዳል።
የፌዴሬሽኑ 12ኛው ክልል የስራ ማስጀመሪያውን መርሀግብር የሚያከናውነው በዛሬው ዕለት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ነው።
ከተማዋም ባለፉት ሳምንታት አዲሱን የክልሉን አመራር አቀባበል ለማድረግ ዝግጅቷን ስታካሂድ ነበር።
ዛሬ ለሚካሄደው የስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር የፌዴራልና የአዲሱ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ ከተማው ገብተዋል።
በአዲሱ አደረጃጀት የተቋማት ክፍፍል መሰረት " ዎላይታ ሶዶ " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዋና መቀመጫ እንዲሁም የክልሉ ዋና የፖለቲካ ማዕከል ናት።
ፎቶ፦ የዎላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የከተማው ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ምስጋናው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ወላይታ ሶዶ ከተማ አራዳ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራበት ኪዳነ ምህረት ቀጠና ላይ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ አደጋ ተከስቷል። በዚህ አደጋ የ2 ሰዎች (ወንድና ሴት) ሕይወት ሲያልፍ ችሏል" ብለዋል።
" ሌሎቹ 17 የሚሆኑ ወንዶች፣ 6 ሴቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያሉ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያና ኦቶና ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ዋና ኢንስፔክተሩ፣ "አንደኛዋ ሟች ከሹፌሩ ጋር የነቀረች ሴት ናት። አንደኛው ደግሞ ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪ ነበር" ነው ያሉት።
አደጋው የተከሰተውም በሕዝብ ማመላለሻ፣ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ)፣ በባለ ሁለት እግር ሞተር፣ በአንድ የቤት መኪና መካከል መሆኑን ገልጸው፣ "ሁሉም ላይ ጉዳት ደርሷል" ብለዋል።
" የአደጋው መንስኤ፣ ጥፋት የማነው? የሚለውን በሂደት ላይ ነን፣ ሹፌርም ተጎድቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የወላይታ ሶዶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በበኩሉ፣ " የአፈር ማዳበሪያ የጫነው የጭነት መኪና ፍሬን በመበጠስ ምክንያት ከባድ የመኪና አደጋ ተከስቷል " ብሎ በዚህም 2 ሰዎች ሞተዋል ፤ 24 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አሳውቋል።
በአደጋው ፦
- አንድ ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና
- ሁለት ቶዮታ ቪትዝ
- ሶስት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
More - https://t.iss.one/ThiqaMediaEth/301
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን