TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኤርትራ

ኤርትራ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረን አውሮፕላንን ከአየር ክልሏ ማስወጣቷ ተነግሯል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ባየርቦክ ትላንት እንዳስታወቁት፤ ወደ ጂቡቲ ሲጓዝ የነበረው የጀርመን መንግስት አውሮፕላን ያለ እቅድ ሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዱን ገልጸለዋል።

ይህ የሆነ በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማለፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ በጉዞ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውም ጂቡቲ ነበረች።

ሚኒስትሯ ፤ ያለ እቅድ በሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዳቸው በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያለውን አለመረጋጋት ያመለክታል ብለዋል።

ትላንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው ለማደር የተገደዱት ሚኒስትሯ ዛሬ በጅቡቲ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ " አውሮፕላኑን በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማብረር ፈቃድ እንዳልተሰጠው ያወቅነው ትናንት ጠዋት ከበረራው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነበር " ብሏል።

አውሮፕላኑ #በበረራ_ላይ_እያለ ፈቃዱን ያገኛል ተብሎ በመወሰኑ ወደዚያ መሄዱንም ገልጿል።

ከቤርቦክ ጋር የተጓዙት ልዑካን ፤ አውሮፕላኑ እየበረረ ፈቃድ ማግኘት እንግዳ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ቤርቦክን ፤ የሱዳን ጦርነት ጉዳይ እና የቀይ ባህር የመርከብ መንገድ ጉዳይ ትኩረት አድርጓል የተባለው የምሥራቅ አፍሪቃ ጉብኝታቸውን ነገ በደቡብ ሱዳን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

#AlAinNews #DW

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል።

ለ7 ቀናት ያህል በሚቆየው የአዲስ አበባው ምክክር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በምክክሩ የውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን የሚያመጡ ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፤ እነዚሁ ተሳታፊዎች በተስማሙባቸው የጋራ አጀንዳዎች ላይ የመፍትሔ ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመልክቷል። #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Africa #Kenya " በሙስና የተዘፈቀውን ካቢኔዎትን ይበትኑ ! " - የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን ቢሰርዙም ተቃውሞው ቀጥሏል። የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ፕሬዜዳንቱ ካቢያናቸውን እንዲበትኑ ጠይቀዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና በርከታ ኬንያውያን ሩቶ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና እንዲያጸዱ ጥሪ እያቀረቡ…
#Kenya #Update

ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ።

ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ።

ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት።

የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው።

ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝደንት ራጋቲ ጋቻጉ ሲቀሩ ሌሎቹን ሚኒስትሮቻቸውን በሙሉ ማሰናበታቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ እርምጃውን የወሰዱት የሕዝባቸውን ድምፅ በመስማት መሆኑን ተናግረዋል።

#DW
#CitizenTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል። ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል። " አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።…
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
#Kenya

@tikvahethiopia
#Sudan

" በ2 ሳምንት ውስጥ ለቃችሁ ውጡ " - የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች

የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የውጪ ዜጎች ከዋና ከተማዋ ካርቱም እና በዙሪያ ካሉ አካባቢዎች እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ።

ፖሊስ ባወጣው ማሳሰቢያ ፥ የውጪ ዜጎች ከተባሉት የሱዳን አካባቢዎች ለመውጣት የ2 ሳምንት ጊዜ ብቻ ነው የተሰጣቸው።

የሱዳን በመንግሥት ወታደሮች እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገቡ በርካታ ወራት አልፈዋል።

ውጊያ አሁን ድረስ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የውጪ ዜጎች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ አካባቢውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው ነው ፖሊስ ያሳሰበው።

በሌላ በኩል ፥ ' በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ውስጥ የሌላ ሀገር ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አሉ ' በሚል በመገናኛ ብዙሃን መዘገቡን ተከትሎ በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመጡ የውጪ ዜጎች ላይ ጥላቻ ይስተዋላል።

ከቀናት በፊት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ከ150 በላይ የውጪ ዜጎች መታሰራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

#DW
#Reuters
#SudanMilitary
#RSF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው…
#USA

የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩነታቸው ትላንት ተቀብለዋል።

ከቅዳሜው የግድያ ሙከራ በኋላ ሪፐብሊካኖች ለዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ ድጋፋቸውን ከምን ጊዜውም በላይ አሳይተዋል። 

" የሁሉም አሜሪካውያን ፕሬዝዳንት እሆናለሁ " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ፦

- በሀገር ውስጥ ሕገወጥ ስደተኞችን ማባረር፣

- ኢኮኖሚውን ማሳደግ

- ግብር መቀነስን በዋና ግብነት አስቀምጠዋል።


በውጪ ግንኙነታቸውም የጋዛና የዩክሬይንን ግጭት መፍትኄ ከመስጠት ጀምረው ዓለምን ካጣችው ሰላም ጋር እንደሚያስታርቋት ቃል ገብተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳሉ የዴሞክራቶች ፓርቲን በመወከል ተወዳድረው የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚደንት የነበሩት ባራክ ዖባማ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጩ የኋይት ሐውስ ተወዳዳሪ መሆናቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ባራክ ኦባማ ሁሉ የቀድሞዋ የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲም ሥጋታቸውን ገልጠዋል። #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም  "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል። አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን…
#Update

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።

በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል።
#DW

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን " የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው " ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት እንደሆነ ተነግሯል።

ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ " በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ " መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብም በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ተዘግቧል።

#AFP #DW

@tikvahethiopia