TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የUAE መሪዎች ዛሬ በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደስታ መግለጫ ልከዋል።

የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት የላኩት የUAE ፕሬዝደንት ሼክ ክሃሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ የዩኤኢ ምክትል ፕሬዝደንት፤ ጠቅላይ ሚኒስትርና የዱባይ ገዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም እንዲሁም የአቡዳቢ ዘውዳዊ ልዑል እና የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ናቸው።

መሪዎቹ፤ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ ስለተመረጡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የኤርትራው ፕሬዝዳንት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደስታ መግለጫ ልከዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ፤ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ በመፈጸማቸው በራሳቸው እና በሚመሩት ሕዝብ ስም መደሰታቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ እና አስመራ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከግጭት እና ከፍጥጫ በመውጣት ሰላምና ወዳጅነትን መመስረታቸው ለአፍሪካ ቀንድ አወንታዊ ማመላከቻ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል።

በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል።

እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል።

እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም።

@tikvahethiopia
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ለሚመሰርቱት መንግስታቸው ፣ ለህዝብ ተ/ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አዳዲስ አመራሮች በተጨማሪ በቅርቡ ለተቋቋሙ አዳዲስ የክልል መንግስታት አመራሮች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገለፀ።

አዳዲሶቹ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት በእውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መላው የሀገሪቱን ህዝብ በቅንነት እና ታማኝነት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርቧል።

በከፍተኛ የሰላም እጦት ፣ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ ከአዲሱ መንግስት በርካታ አፋጣኝ ውሳኔዎችን ትጠብቃለችም ብሏል ነእፓ።

ፓርቲው ፦

- በጦርነት፣ በግጭት እና በፍትህ እጦት የሚንገላቱ በርካታ ዜጎች ከጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመንግስታቸው በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እውን እንዲሆን ፈጣን ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።

- በከፍተኛ ድህነት፣ የኑሮ ውድነት እና ስራ አጥነት አዙሪት ውስጥ ለሚሰቃዩ እልፍ አእላፍ ኢትዮጵያውያን ከአዲሶቹ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተጨባጭ የመፍትሄ እርምጃዎችን በታላቅ ተስፋ ይጠብቃሉ።

- በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በግጭት እና በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ወደ ቀያቸው ተመልሰው የሰላም አየር የሚተነፍሱበት ሰዓት በጉጉት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፤ በመሆኑም እነዚህ እና ሌሎች በርካታ የሀገሪቱ ዘመን ተሻጋሪ ውስብስብ ችግሮች የአዲሱን መንግስት አፋጣኝ ውሳኔ ይሻሉ ብሏል።

ነእፓ፥ " ዶ/ር ዐቢይ እና መንግስታቸው የሀገሪቱን እና የህዝቡን ድርብርብ ችግሮች ለመቅረፍ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን " ሲል መልዕክቱን አስተላልፋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Facebook ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል። በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል። እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል። እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገሮች ውስጥ አገልግሎታቸው መቋረጡን ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ክስተቱ በአገር ደረጃ ካለ የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር ያልተገናኘ መሆኑንም ጠቁሟል።

እስካሁን በፌስቡክ በኩል ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Update

የተቋረጠው የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኢትዮ ቴሌኮም መልእክት አስተላልፏል።

ፌስቡክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት በተቻለ ፍጥነት ነገሮችን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል ፤ ለተፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግርም ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተቋረጠው የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኢትዮ ቴሌኮም መልእክት አስተላልፏል። ፌስቡክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት በተቻለ ፍጥነት ነገሮችን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል ፤ ለተፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግርም ይቅርታ ጠይቋል። @tikvahethiopia
#Update

ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም።

እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የካቢኔ ሹመት ጉዳይ ? ዛሬ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት የካቢኔ ሹመት አልፀደቀም። የካቢኔ ሹሙቱ ነገ ወይም በቀጣይ ቀናት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
#Update

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ የካቢኔ ሹመት ያፀድቃል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው መርሃ ግብር መሰረት የመንግስት የካቢኔ ሹመትን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
በመኪና አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 15 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደረሰባቸው።

መነሻዉን አርባ ምንጭ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3 03348 የሆነ ቅጥቅጥ FSR 45 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ትላንት ከጠዋቱ 2:30 አካባቢ ከአርባ ምንጭ መናኸሪያ ተነስቶ ወደ ጅንካ ሲጓዝ ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰው ከባድ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው መኪናው ባጋጠመዉ የፍሬን ችግር ምክንያት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሕይወታቸውን ካጡ 8 ሰዎች በተጨማሪ በ6 ሰዎች ላይ ከባድ እንድሁም በ9 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአሌ ልዩ ወረዳ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል። ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም። እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ከ6 ሰዓታት በላይ አገልግሎቶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።

የተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ መከሰቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የኩባንያውን ውስጣዊ መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ላይ ተፅእኖ በማሳደሩ ችግሩን ለመፍታት አዳጋች አድርጎታልም ሲል ገልጿል።

መግለጫው አክሎም "ተቋርጠው በነበሩበት ሰዓታት የተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ የለም" ብሏል።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ አገልግሎቶቹ በመቋረጣቸው ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች ይቅርታ መጠየቃቸውን #BBC / ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
7ቱ የተመድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ለቀው ወጥተዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ይታወሳል።

ግለሰቦቹ በምን አይነት ህገወጥ የሆኑ ድርጊቶች ላይ ሲሳተፉ እንደነበረ በዝርዝር ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

እነዚህ ግለሰቦች እሁድ ዕለት ኢትዮጵያን ለቀው መውጣታቸውን የተመድ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) በድረገፁ አስነብቧል።

7ቱ የተመድ ሰራተኞች ላይ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ውሳኔ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ዩኬ እና የአውሮፓ ህብረት አውግዘው ነበር ፤ ከዚህ በተጨማሪ ተመድ የኢትዮጵያ መንግስት ባልደረቦቼን ከሀገር የማባረር መብት የለውም ማለቱ አይዘነጋም።

እንደ AFP ዘገባ ግን በ72 ሰዓት ከሀገር እንዲወጡ ቀጭን ትዕዛዝ የተሰጣቸው የተመድ ሰራተኞች እሁድ እለት ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ም/ቃል አቀባይ ፈርሃን ሀቅ ባለስልጣናቱ ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ሃቅ ፥ "ደህንነታቸው ለማረጋገጥ ሲባል ከሀገሪቱ ወጥተዋል" ብለዋል።

በUN ስር ባሉ ኤጀንሲዎች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት 7ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ፦

• የUNICEF የኢትዮጵያ ተወካይ - አዴል ኮደር
• የUN ሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ባልደረባ - ሶኒ ኦኒግ ቡላ
• የUN የሰላምና ልማት አማካሪ - ከውሲ ሳንቼሎቲ
• የUN የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ - ግራንት ሊያቲ
• የUN የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ - ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ፣
• የUN የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ምክትል አስተባባሪ - ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ
• የUN የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ኃላፊ - ማርሲ ቪጎዳ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ የካቢኔ ሹመት ያፀድቃል። ምክር ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው መርሃ ግብር መሰረት የመንግስት የካቢኔ ሹመትን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
የካቢኔ ሹመት የማፅደቁ ስራ ለነገ ተላለፈ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ካቢኔ ሽመትን የማፀደቅ ሥራውን ለነገ ያስተላለፈ መሆኑን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ነው። የ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" መስራችና ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ የፌደራል ፖሊስ አሳወቀ። ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያሳሰወቀው ለቢቢሲ ነው። ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ከቅዳሜ መስከረም 22/2014 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ ያለበትን እንደማያውቁ የሥራ ባልደረቦቹ እና ጓደኞቹ መናገራቸው ይታወቃል። የፌደራል ፖሊስ የወንጀል…
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ከእስር ተለቀቀ።

የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ከእስር መለቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቢቢሲ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ከእስር መለቀቁን ከጠበቃው ሽብሩ በለጠ እንዲሁም ከራሱ ከጋዜጠኛው እንዳረጋገጠ በድረገፁ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ለ3 ቀናት ያህል በእስር ላይ ቆይቷል።

ቅዳሜ ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ዛሬ ቃሉን መስጠቱንም ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#CentralStatisticsAgency

የመስከረም ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 34.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ ሪፖርት አመላከተ።

የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በማነፃፀር የሚገኘው ውጤት ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 42.0 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በተለይ በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፦
- የሩዝ፣
- የእንጀራ፤
- የዳቦ፤
- የጤፍ፤
- የስንዴ፤
- የማሽላ፤
- የበቆሎ፣
- የገብስ፣
- የስንዴ ዱቄት፣
- የፓስታና ማካሮኒ ዋጋ በፍጥነት ጨምሯል፡፡

በተጨማሪም ፦
- ሥጋ፣
- የምግብ ዘይት (ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ከውጭ የሚገባው የምግብ ዘይት ዋጋ እጥፍ በለይ ሆኗል)፣
- ወተት፤
- አይብና ዕንቁላል፤
- ቅቤ፣
- ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨውና በርበሬ)
- ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር (መስከረም) ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወር ከፍ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ25.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/CSA-10-05

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia
#WFP : በአፋር እና አማራ ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች፤ የመጀመርያ ዙር የምግብ እርዳታ ማዳረሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሳውቋል።

ድርጅቱ በግጭት ምክንያት እርዳታዎችን ማዳረስ ያልተቻለባቸው ቦታዎች ቢኖሩም 2,200 ሜትሪክ ቶን የሚገመት የምግብ እርዳታ ወደ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ሊያድርስ መቻሉን ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የእርዳታ ስርጭት 210 ሺ ሰዎች ለመርዳት እንደተቻለ ድርጅቱ አሳውቋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፥ በአፋር ክልል 80 ሺ ሰዎች እርዳታ ማግኘታቸውን ገልፆ ካለው የችግሩ መጠን አንጻር በቀጣይ ዙር የሚረዱ ዜጎች ቁጥር ወደ 500 ሺ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁሟል።

እአአ ከነሃሴ 15 ወዲህ በአማራና አፋር ክልሎች ለሚገኙ 300 ሺ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ መዳረሱንም ገልጿል።

ለትግራይ ክልል የሚደረገው እርዳታ በተመለከተ “በተለያዩ እንቅፋቶች፤ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እንደፈለጉ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ ኋላ ቀርቷል” ብሏል።

ከግንቦት 27 ወዲህ ከሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ ተፈናቅለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች እርዳታ ማዳረሱን ገልጿል፡፡

“እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 200 ሺ ህጻናት እና እድሜያቸው ከ39 እስከ 71 የሆኑ ነፍሰጡር እና አጥቢ እናቶች” የተመጣጠነ የምግብ እርዳታን ካገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ዱንፎርድ ፥ “ሪፖርቶች እንደሚያመክቱት ከሆነ ፤ባለው ሁኔታ በርካታ ቤተሰቦች ከቤታቸው እየሸሹ በመሆናቸው በሶስቱም ክልሎች ያለው የምግብ እጥረት ሁኔታ እየጨመረ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Credit : www.wfp.org / አል ዓይን

@tikvahethiopia