በተሽከርካሪ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የኤጀርሳ ለፎ ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጂን ፍቃዱ ሙሉጌታ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ትላንት ማምሻውን በወረዳው ለገ ሁሉቆ በተባለ አካባቢ ነው።
ከአዲስ አበባ ወደ ጊንጪ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3– 30485 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3 –52989 ኦሮ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል።
በአደጋው የሚኒባሱ አሽከርካሪን ጨምሮ ሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉን ተናግረዋል።
በሚኒባሱ እና በአይሱዙ ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩት ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች በጳውሎስ ሆሲፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው መሰጠቱን የገለጹት ዋና ሳጂን ፍቃዱ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን !
እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉ ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።
መልካም በዓል! #TikvahFamily
Photo : Social Media

#Berlin : የኢትዮጵያ 🇪🇹 ልጆች የደመቁበት የበርሊን ማራቶን !
በበርሊን የሴቶች ማራቶን የመጀመሪያ የበርሊን ውድድሯን ያደረገችው ጎትይቶም ገብረ ስላሴ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
ህይወት ገብረ ኪዳን ሁለተኛ እንዲሁም ሄለን ቶላ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወንዶቹ የበርሊን ማራቶን በአትሌታችን ጉዬ አዶላ አሸናፊነት ተጠናቋል።
የዘንድሮው የውድድር ዓመት የበርሊን ማራቶንን በቀዳሚነት ሊያሸንፍ ይችላል ተብሎ ትልቅ ግምት አግኝቶ የነበረው #ቀነኒሳ_በቀለ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል ።
More : @tikvahethsport

#መልዕክት
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት ፦
- በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲኬድ የፀጥታ አካላት በየቦታው ፍተሻ ያደርጋሉ፤ ይህንንም ህዝበ ክርስትያኑ እንዲገነዘብ ተብሏል። ምናልባት ፍተሻው 2 እና 3 ቦታ ቢሆን እንኳን ፍተሻው ለራስ ደህንነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይሰላች ለፍተሻው እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።
- ከባንዲራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ - ወደበዓሉ ቦታ በሚኬድበት ጊዜ ፣ የወጣት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት እንዲሁም ሌሎች አካላት በሀገሪቱ ህገመንግስት የፀደቀውን የፌዴራል አርማ ያለበትን ባንዲራ ብቻ መጠቀም ይገባል ተብሏል፤ አላስፈላጊ ሎጎዎችን እና ህጋዊ ከሆነው ባንዲራ ውጪ መጠቀም አይቻልም፤ ለዚህም ለፀጥታ አካላት ትብብር ማድረግ ያስፈልጋል።
- ከኢትዮጵያ ብሄራዊው ባንዲራ ውጪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» የሚል አርማ ያለበትን ባንዲራ መጠቀም ይቻላል፤ ህዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ባንዲራ ሲጠቀም በስነስርስአቱ የታተመ፣ በሁለቱም በኩል ሎጎው እንዳለ የሚያሳይ መሆን አለበት።
- ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲሄድ የኮቪድ-19 መከላከያ ጥንቃቄዎችን መፈፀም እንዳለበት አደራ ተብሏል። ማስክ ያድርጉ፣ ሳኒታይዘር ያዙ ፤ ርቀታችሁንም ጠብቁ።
- የጤና ሚኒስቴር በመስቀል አደባባይ የኮቪድ-19 የክትባት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፤ በቦታው ላይ ክትባት ስለሚሰጥ ቀደም ብሎ በመገኘት የክትባቱ ስነሥርዓት ተሳታፊ መሆን እንደሚቻል ተገልጿል።
- ከመስቀል አደባባይ ውጭ የሚደረጉ የመስቀል ደመራ ስነስርዓቶች የፀጥታ ኃይሎችን በመተባበር እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
- ለበዓሉ ድምቀት በሚል ርችት መተኮስ አይፈቀድም።

ፎቶ : የመስቀል ደመራ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ክርስቲያን በተገኘበት በፍፁም ሰላም ተከብሯል።
ከአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው መስቀል ደመራ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው ዓመት እጅግ በጣም በውስን ተሳታፊዎች መከበሩ አይዘነጋም።
ፎቶ : አዲስ አበባ - መስቀል አደባባይ (2014 ዓ.ም)
#TikvahFamily

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 32 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,076 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 869 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 798 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

" ... የእኛ ሰላምና እርቅ በየጊዜው እለት እለት ልንፈጽመው የሚገባን ተግባር መሆን አለበት " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዛረው በበዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው ዕለት የምናከበው በዓለ መስቀል የእግዚአብሔር ሰላምና እርቅ ፍለጋ በብርቱ የተንቀሳቀሰችው ታላቋ ክርስቲያናዊት ንግሥት ዕሌኒ የፈጸመችውን የቅድስና ተግባር እና ያስገኘቸውን ሃይማኖታዊ ስኬት መነሻ አድርገን ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ነው ብለዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ የሰውን ልጅ መርገመ ሃጢያት እንዲወገድ በማድረግ ሰው ወደቀደመ ቦታው ገነት እንዲገባ ምክንያት መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት መስቀል ከሁሉም በላይ ነው ሊባል መቻሉን ገልጸዋል።
የእኛ ሰላምና እርቅ በየጊዜው እለት እለት ልንፈጽመው የሚገባን ተግባር መሆን አለበት ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ አንገታችን ላይ ያለው መስቀል ጌጥ ሳይሆን በእግዚአብሄር እና በሰው፣ በእኛ እና በስነፍጥረት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳ በመሆኑ ልንጠብቅበት ይገባል ካሉ በኋላ በዓለም ላይ ሰላም ፍቅር እና አንድነት እንዲሰፍን ጠንክረን እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/MESKEL-09-26-2