TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HawassaUniversity

ዛሬ ጠዋት መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ በደረሰው ጉዳት አዝናለሁ ብሏል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

" ሁኔታቸዉን መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ " ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር " ወላጆች እንዳይደናገጡ እንጠይቃለን " ብሏል።

ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ አሳስቧል።

ሁኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ፎቶ ፦ክብሩ ግዛቸው

@tikvahethiopia
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ሁኔታ በዝርፊያ እየተፈተነ ይገኛል።

አላግባብ ለእስር ታዳረግን ያሉ ሰራተኞችም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።

ለአመታት በሚሰጠዉ ትምህርትና ለማህበረሰቡ በሚያደርገዉ ድጋፍ  የሚታወቀዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዝርፊያ ምክኒያት አየተፈተነ ነዉ።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ከኮምፒዉተር እስከ ቀላልና ከባድ ማሽኖች ከመንገድ ላይ መብራት እስከ ግድግዳ ላይ የተገጠሙ ሶኬቶች ሳይቀር አየተዘረፈበት ሲሆን ዳፋዉ የደረሳቸዉ ተማሪዎችም ዘግተዉት የወጡት በር እየተሰበረ ከአልባሳት እስከ ኤሌክትሮኒክስ ከመማሪያ ቁስ እስከ መመረቂያ ሱፍ መዘረፋቸውን ይጠቁማሉ።

ችግሩን ዉስብስብ ያደረገዉ ደግሞ ዝርፊያዉን ለመመርመር የሚመጡት የህግ አካላት በተደጋጋሚ የግቢዉን ሰራተኞች ማሰራቸዉ እንደሆነ ቅሬታች አቅራቢዎች ገልጸዋል።

ከዚህዉ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ለእስር መዳረጉን የገለጸልን የዩኒቨርስቲው መምህር በስሙ የነበሩ ኮምፒዉተሮች ተሰርቀዉ ማደራቸዉን ተከትሎ ለዘጠኝ ቀናት ለእስር መዳረጉን ይገልጻል።

መምህሩ እንደሚገልጸዉ " ስንት ጥበቃ ባለበት ግቢ ዉስጥ እቃ ተሸክሜ መዉጣት እንደማልችል እየታወቀ የተያዝኩበት መንገድ አሳፋሪና አግባብነት የጎደለዉ ነበር " ሲል ያስታዉሳል።

ሌላኛዉ ከዝርፊያ ጋር በተያያዘ ለሁለት ቀናት እስር መዳረጉን  የገለጸልን መምህር ደግሞ መምህራኑ የሚታሰሩት ሌሊት ተሰርቆ በሚያድር እቃ መሆኑን ገልፆ ጉዳዩ ተጣርቶ ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ፋይላቸዉን ለመዝጋት የሚወስደዉ ጊዜ ከብዙ ጉዳይ እንደሚያስቀራቸዉና  ለእንግልት እየዳረጋቸዉ መሆኑን ያነሳል።

ከዚህዉ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ  ምክትል ፕሬዚዳንት ዶር ሳሙኤል ጅሎ እንደሚገልጹት መምህራን ለእስር የሚዳረጉበት ምክኒያት ቢሯቸዉ በቁልፍ ተከፍቶ እቃዉ ጠፍቶ መገኘቱን ተከትሎ የምርመራ ትኩረት እነሱ ላይ የሚያነጣጥር በመሆኑ ነው በማለት ገልጸዋል ።

ዶ/ር ሳሙኤል አክለዉም መምህራን በሚያዙበት ወቅት በአግባቡና በክብር እንዲሆን የጸጥታ አካላትን እያነጋገሩ መሆናቸዉን ገልጸዉ ምርመራዎች በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲያልቅና ፋይላቸዉ አንዲዘጋም ጥረት እንደሚያደርጉ አመላክተዋል።

በግቢዉ ዉስጥ የሚስተዋለዉን ዝርፊያ ለመቆጣጠር አሁን ላይ የጥበቃ አሰራሩን አዉትሶርስ ለማድረግ ጨረታ ላይ መሆናቸዉን የሚገልጹት ዶክተር ሳሙኤል አዉትሶርስ በማይደረጉ ክፍሎችም የጥበቃ ቁጥር ለመጨመር መታሰቡን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አሁን ላይ ዩኒቨርስቲው ችግሩን ለመቅረፍ አንዳንድ ህንጻዎችን የስማርት ሴኪዉሪቲ ሲስተም መጠቀም መጀመሩን ተከትሎ ለዉጦች ቢኖሩም የስማርት ሲስተሞች የራሳቸዉ ክፍተት መኖርና የችግሩ ስር መስደድ ግን ሁኔታዉን ከባድ ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ምክንያት ሆኗል።

@tikvahethiopia
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱት የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቹ 99% ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለመመረቅ ብቁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ተቋሙ ይፋ ባደረገው ዳታ ፤ በ ' ዶክተር ኦፍ ሜዲስን ' ካስፈተናቸው 190 ተመራቂዎች 189 ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ፈተና አልፈዋል።

More 👉 @tikvahuniversity
#HawassaUniversity

በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲውስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲልኩ ነበር።

ለዚህ ቅሬታ መነሻቸውም አንድ ተለጥፎ ያዩት ማስታወቂያ ነው።

ማስተወቂያው ፦

° በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት ተማሪዎች ወደቤት መሄዳቸውን ይጠቁማል።

° የገበያው አለመረጋጋት አቅራቢዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና እና በቀን ለ1 ተማሪ የተወሰነው 22 ብር ዕለታዊ ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የመግቢያ ቀን መራዘሙን ያሳያል።

° ኢንተርን ሽፕ ላይ ያሉ እና ካፌ ተጠቃሚ የነበሩ እጩ ዶክተሮች በምግብ ምትክ የሚሰጠውን የነን ካፌ ፎግም ሞልተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይላል።

° የተማሪዎች መግቢያ እስኪገለጽ ከቀን 29 /11/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ በተለያዩ ምክንያቶች ግቢ ያሉ ተማሪዎች በ4 ቀን ለቀው እንዲወጡ ይላል።

የተማሪዎች ቅሬታስ ምንድነው ?

መልክዕታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቅሬታቸው ፦

- ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ ነው።
- የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል።
- መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም።
- በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያችን ተቃጥሏል። ወሁን የመመረቂያ ጊዚያችን ተራዝሟል።
- በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንድንወጣ ተደርገን ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ነው የተጠራነው። በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ተገፋ። አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰማን። ይህ ትክክል አይደለም።
- የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች ቅሬታን እንዲሁም የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይዞ ዩኒቨርሲቲው አለኝ የሚለውን ማብራሪያ ለተማሪ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ  ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ምን አሉ ?

የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም።

ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ አይወጡም። ዶርማቸውንም አይለቁም። ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ነው የተገለጸው።

ይህ የሆነው አሁን ላይ ለ3 አመት ውል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር  ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ትክክለኛ ቀኑንም  ለተማሪዎች በይፋ ይነገራቸዋል።

ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልተቻለው ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነው።

በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ከግቢ መውጣታቸውን ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸው የሚወስድባቸውን ጊዜ  ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዛ ይሄዳል።

ተማሪውን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እውቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ምን አለ ?

👉 ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመውጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት አልደረሰባቸውም። ማስታወቂያውም ያለኛ እውቅና ነው የተለጠፈው።

👉 ተማሪውን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ውሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነው።

👉 ተማሪዎች ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ውስጥ ከሚያስተካክላቸው አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት ነው።

👉 ተማሪዎች በጊዜ ወደ ግቢ ባለመግባታቸው በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲያስብበት ተነጋግረናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

More - @tikvahuniversity

@tikvahethiopia