TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AbdelazizBouteflika

በኢትዮጵያ 🇪🇹 እና በኤርትራ 🇪🇷 መካከል ተከሄደው ጦርነት መቋጫ የሆነው አልጀርስ ስምምነት እንዲፈረም ሚና የነበራቸው የቀድሞ የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በ84 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በፈረንጆቹ 1999 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ቦተፍሊካ እጅግ ከባድ የሚባለውን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት አንዲፈቱ ሃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከልም ስምምነት እንዲፈረም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ቦተፍሊካ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2019 ስልጣናቸውን ከመልቀቃቸው በፊት ሰሜን አፍካዊቷን ሀገር አልጀሪያን ለሁለት አስርት አመታት መርተዋል፡፡

የቀድሞውየአልጀሪ ፕሬዝዳንት ቢተፍሊካ፣ በሀገሪቱ የተካሄደውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ነበር ከሁለት አመታት በፊት ስልጣናቸውን የለቀቁት፡፡

ለሁለት አስርት አመታት አልጀሪያን ያስተዳሩጽ ቦተፍሊካ ፤ የአልጀሪያ የነጻነት ጦርነት ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን በፈረንጆቹ 2019 የህዝብ ተቃውሞ በመዝዛቱ ስልጣናቸውን ለ6ኛ ዙር የማራዘም እቅዳቸውን ሰርዘው ስልጣን ለቀዋል፡፡

ቦተፍሊካ ከፈረንጆቹ 2013 እስሚሞቱበት ጊዜ ድረስ በአደባባይ ብዙም አይታዩም ነበር፡፡

ለረጅም ጊዜ ታመው እንደነበር የተነገረላቸው አብደላዚዝ ቦተፍሊካ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Credit : አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
የመላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፈ።

ድርጅቱ በፃፈው ደብዳቤ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ አለም ፣ ጊዳ አያና እና ሊሙ የወረዳ ከተሞች ፤ በሌላ በኩል በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ፣ አሙሩ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ በተሰየመው "ሸኔ" /ፓርቲው "ኦነግ ሸኔ" ሲል ነው የገለፀው/ ከአንድ ወር በላይ ከበባ ተደርጎባቸው ህይወታቸው እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ይገኛል ብሏል።

መኢአድ በከበባ ውስጥ ናቸው ያላቸው ዜጎች እስከሁን ከመንግስት ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ አልተደረገላቸው፤ እነዚህ ዜጎች በየደቂቃው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

ከሽብር ቡድኑ በየዕለቱ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰባቸው ነው ያለው መኢአድ በርካታ ወረዳን ከወረዳ ጋር፣ ወረዳን ከዞን እንዲሁም ምስራቅ ወለጋን ከጎጃም ቡሬ የሚያገናኙ መንገዶች ከተዘጉ መሰንበቱን ጠቁሟል።

በአሁን ሰዓት በርካታ መንገዶች መቆፈራቸውን እና መቆራረጣቸውን አክሏል።

መንግስት ' መንግስታዊ አቅሙን እና ኃላፊነቱን ' ተጠቅሞ የእነዚህን ወገኖች ህይወት እንዲያተርፍና የዘር ማጥፋትና ሀገርን የማፍረስ አጀንዳ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ፤ ለዚህም በጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ በኩል የሚሰጡ መመሪያዎች መኖር እንዳለባቸው ፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

በጠ/ሚኒስትሩ በኩል ሊወሰዱ ሚገባቸው እርምጃዎች የህፃናትን ፣ የሽማግሌዎችን፣ የእናቶችን፣ የአቅመ ደካሞችን ፣ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት የመታደግ ኃላፊነት በእጃቸው ላይ እንዳለ ፓርቲው አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
የመስከረም 20 ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር /ኦብነግ ONLF/ ከምርጫ እራሴን አግልያለሁ ብሏል።

ግንባሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ አመልክቷል።

የኦብነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጅግጅጋ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው ከምርጫው እራሱን ማግለሉ ያሳለፈበት ውሳኔ ላይ ደረሰው።

ፓርቲው ከምርጫው ወጥቻለሁ ካለባቸው ምክንያቶች መካከል ፦

- ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በመቅረቱ።
- ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ችግሮች ስላሉ።
- የምርጫ ካርድ የተሰራጨው ለሕዝቡ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ለራሳቸው ወገኖች ነው።
- የመራጮች የምዝገባ ሂደት ማጭበርበር የተሞላበት በመሆኑ።
- የዕጩዎች ምዝገባን ማገድ፣ ዕጩዎችን እና አባላትን ማጥቃትና ማዋከብ እንዲሁም ትክክለኛ የመራጮች ምዝገባ ማደናቀፍ ስለነበረ።
- በሶማሌ ክልል በበለጠ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ በመሆኑ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ፓርቲው ፥ ምርጫውን ለ3 ወራት በማራዘም የተፈጠረው የሕዝብ ተስፋ፣ ምርጫ ቦርድ የተበላሸውን አሰራር ባለማስቆሙ ሂደቱ ጠልሽቷል ብሏል።

ኦብነግ ከምርጫ ለመውጣት በመወሰኑ ማዘኑንና በቀላሉም እዚህ ላይ እንዳልደረሰ ገልጿል።

ኦብነግ ትጥቅ ትግሉን ለማቆም ዋናው ምክንያት የሶማሌ ክልል ሕዝብ መብቶችን በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስከበር በመሆኑ ነው ቢልም ከምርጫው ተገዶ መውጣቱን ገልጿል።

Credit : ቢቢሲ
Photo : ONLF

@tikvahethiopia
#SolianaShimeles

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 /2014 ዓ/ም ለሚያካሂደው ምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ ምርጫው በሶማሊ፣ ሐረሪ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በተያዘለት መርሀ ግብር መስከረም 20/2014 ይካሄዳል ብለዋል።

አስፈላጊው ዝግጅትም ከወዲሁ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ በዕለቱ ከምርጫው ጋር ጎን ለጎን አብሮ እንደሚካሄድ ወ/ሪት ሶሊያና ገልፀዋል።

Credit : ኢፕድ
Photo : Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ኦባንግ ሜቶና ለጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው የ 2013 ዓ/ም የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ ነው ለአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ለጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ የክብር ዶክትሬት የሰጠው።

@tikvahuniversity
የ4G LTE አገልግሎት :

- በደምቢዶሎ፣
- በነቀምቴ፣
- በጊምቢ፣
- በባኮ እና በሻምቡ ከተሞች ጀመረ።

ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ሪጅን የ4G LTE ፈጣን የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ደምቢዶሎ፣ ነቀምቴ፣ ጊምቢ፣ ባኮና ሻምቡ ከተሞች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ፥ በተጠቀሱት ከተሞች የሚገኙ ከ256 ሺ በላይ ደንበኞቹ የ4G LTE ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

ወ/ሪት ፍሬህይወት ፥ በቀጣይ የ4G አገልግሎት በሌሎች አካባቢዎች እደሚስፋፋ የገለጹ ሲሆን ፤ የ5G አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አሜሪካ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሏን አምና ይቅርታ ጠየቀች።

አሜሪካ ባለፈው ወር በአፍጋኒስታን ካቡል በፈፀመች የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን በመግለፅ ይቅርታ ጠይቃለች።

የአሜሪካ ጦር ትላንት አርብ ድርጊቱን "አሳዛኝ ስህተት" ሲል ገልጾ ይቅርታ ጠይቋል።

ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በርካታ መረጃዎች ሲቪሎች በግፍ መገደላቸውን ሲገልፁ የአሜሪካ ጦር ምናልባት በስህተት ሲቪሎች ተገድለው ሊሆን ይችላል ሲል ፤ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ጄነራል ደግሞ ጥቃቱን ትክክለኛ ሲሉ ገልፀው ነበር።

ነገርግን በቅርቡ በጥቃቱ ዙሪያ በተደረገ ዝርዝር ጥናት እና ምርመራ የአሜሪካ ጦር ታጣቂዎችን ሳይሆን ሰላማዊ ሰዎችን እንደመታ ለማወቅ ተችሏል።

አሜሪካ በፈፀመችው የድሮን ድብደባ 9 የአንድ ቤተሰብ አባላትን (6ቱ ህፃናት ናቸው) ጨምሮ 10 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#enterAir

የፖላንድ አውሮፕላን ድንገተኛ የሞተር ብልሽት ገጥሞት በአዲስ አበባ ለማረፍ ተገደደ።

ንብረትነቱ የኢንተር አየር (enter air) መንገድ የሆነ አውሮፕላን በሞተር ላይ በገጠመው ድንገተኛ ብልሽት ምክንያት በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን የፖላንድ መንግስት አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ከኬንያ ሞምባሳ 167 ሰዎችን አሳፍሮ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት በአንደኛው የሞተር ክፍሉ ላይ የተሳሳተ መረጃ በመነበቡ ምክንያት አዲስ አበባ እንዲያርፍ ተገዷል ብለዋል።

በአውሮፕላኑ ሞተር ላይ በገጠመ ብልሽት ምክንያት የተሳፈሩ ሰዎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ ተተኪ አውሮፕላን ከፖላንድ መላካቸውን የሀገሪቱ ም/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ፒዮትር ዋውርዚይክ ተናግረዋል።

ምክትል ሚኒስትሩ ፥ ተተኪው አውሮፕላን ዛሬ አ/አ ከተማ እንደሚደርስ ጠቁመው እስከዛው ተጓዦቹ በሆቴል መቆየት የሚያስችላቸውን የኢትዮጵያ ቪዛ እንዲያገኙ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፖላንድ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።

አውሮፕላኑ ተሳፋሪዎቹን ጭኖ ስለመነሳቱ በቂ መረጃ ሰጥቶን ነበር ያሉት የፖላንድ አየር መንገድ ሃላፊ፤ የሞተሩ ቴክኒካዊ ብልሽት ምክንያት ምን እንደሆነ እየተመረመረ መሆኑንም ተናግረዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ30,192 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

* ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል #AdmasUniversity

- አጠቃላይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 67 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና 2ኛ ድግሪ በቀንና በማታ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 532ቱ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በ @tikvahuniversity ተከታተሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሏን አምና ይቅርታ ጠየቀች። አሜሪካ ባለፈው ወር በአፍጋኒስታን ካቡል በፈፀመች የድሮን ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን በመግለፅ ይቅርታ ጠይቃለች። የአሜሪካ ጦር ትላንት አርብ ድርጊቱን "አሳዛኝ ስህተት" ሲል ገልጾ ይቅርታ ጠይቋል። ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በርካታ መረጃዎች ሲቪሎች በግፍ መገደላቸውን ሲገልፁ የአሜሪካ ጦር ምናልባት በስህተት ሲቪሎች…
" ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሜሪካን ተጠያቂ ማድረግ አለበት " - የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አሜሪካ በካቡል በፈፀመችው ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሲቪሎችን መግደሏን ማመኗ ፤ ድርጊቱንም "አሳዛኝ ስህተት" ስትል ገልፃ ይቅርታ መጠየቋ ይታወቃል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ 7 ህፃናትን ጨምሮ 10 ሲቪሎች በአሜሪካ ጦር መገደላቸውን በመግለፅ ፥ አሜሪካ እንዲህ ዓይነቱን ተደጋጋሚ ግፍ “ስህተቶች” እና ተጎጂዎችንም እንደ “ኮላተራል ዳሜጅ /የእግረ መንገድ ጥፋት/” እያለች በመግለጽ እራሷን ነፃ ማድረግ አትችልም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ፥ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሜሪካ ለዓመታት በፈፀመችው ወረራ እና ሁከት ተጠያቂ ሊያደርጋት ይገባል ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአሜሪካ የድሮን ድብደባ በግፍ ሰለባ ከሆኑት ንፁሃን መካከል የህፃናቱን ፎቶ በማያያዝ ነው መልዕክቱን ያሰራጨው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 25 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 25 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,464 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,509 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 800 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia