TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ሀገራችን 🇪🇹 አዲሱን 2014 ዓ/ም አንድ ብላ ጀምራለች።

እንሆ 2013ትን ተሰናብተነው አዲሱን ዓመት ጀምረናል። የአዲስ ዓመት በዓልም በሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ስናከብር ከተቸገሩት፣ ካጡት ወገኖቻችን ጋር ማዕድ በማጋራት ሊሆን ይገባል።

የጦርነት ቀጠና በሆኑ አካባቢዎች አቅራቢያ የምትገኙ ምናልባትንም ይህንን መልዕክት ኔትዎርክ አግኝታችሁ የምታነቡ የቲክቫህ አባላት ከቀያቸው ተሰደው፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በሀዘን ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በመደገፍ፣ አብሮ በመብላት፣ በማፅናናት፣ ተስፋን በመስጠት እንድታከብሩ እንማፀናለን።

በሌሎች የሀገራችን ከተሞች የምትገኙ አባላት ደግሞ በጦርነት ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን በማሰብ፣ ስለሀገራችን ፍቅር እና ሰላም በመፀለይ ፣ በአካባቢያችሁ ከተቸገሩት ጋር ማዕድን በማጋራት ይህንን በዓል እንድታከብሩት በትህትና ዝቅ ብለን እንጠይቃለን።

የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የስኬት ዓመት ይሁንልን!

Photo Credit : Social Media

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ23 ዜጎች ህይወት አልፏል።

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 23 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,169 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 845 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 733 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን … 6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬሽን ጀመረች። ከ6ቱ 5ቱ የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ናቸው:: ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ለወራት ያህል የእስር ቤት ክፍላቸውን ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ዋሻ ለመሥራት ሲቆፍሩ ቆይተዋል ተብሏል።…
ፎቶ : ከጊልቦዋ እስር ቤት ካመለጡት ፍልስጥኤማውያን 4ቱ ተይዘዋል።

የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥበቃ ከሚደረግለት የእስራኤል እስር ቤት ጊልቦዋ ካመለጡት 6 ፍልስጤማውያን መካከል 4ቱን መልሰው ይዘዋቸዋል።

ከተያዙት ፍልስጤማውያን መካከል ሁለቱ የተገኙት የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ነው። ሌሎች ሁለቱ ደግሞ ናዝሬት ከተማ አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ስድስቱ ፍልስጤማውያን ባለፈው ሰኞ ከእስር ቤት ካመለጡ በኋላ በፖሊሶች ሲፈለጉ ነበር።

ፍልስጥኤማውያኑ በሰሜን እስራኤል ከሚገኘው ጊልቦዋ እስር ቤት ያመለጡት በማንኪያ መሬት ሰርስረው ነበር። እስረኞቹ ካመለጡ በኃላ በርካቶች በትንግርት ጉዳዩን ሲቀባበሉት፤ በጋዛ ምድርም ደስታ ሆኖ ነበር።

እስራኤል የእስረኞቹ ማምለጥ ቢያስደነግጣትም ፤ የፍልስጤም ታጣቂዎች ግን በተፈጠረው ነገር ኩራት ተሰምቷቸዋል።

እንደ ቢቢሲ መረጃ ፥ ፍልስጤማውያን ከእሰራኤል ከእስር ቤት በዚህ መንገድ ካመለጡ 20 ዓመታት ተቆጥረዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray : ኢሰመኮ በትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት ወደ አጎራባች ክልሎች መስፋፋት የፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳደረ መሆኑ እንደሚገነዘብ ገልጾ በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብሏል።

በአንዳንድ የክልሉ ቦታዎች የተወሰነ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የተመለሰና፤አንዳንድ የባንክ ቅርጫፎች የኔትዎርክ ግንኙነት ባይኖርም በአካባቢ አስተዳዳሪዎች ትዕዛዝ መሰረት መጠነኛ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን መረዳት እንደቻለ ኢሰመኮ ገልጿል።

ነገር ግን በክልሉ ከፍተኛ የምግብ እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት መከሰቱ፣የምግብና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ውስን ስለሆነ ሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ መቸገራቸውን ለማወቅ እንደቻለ አስታውቋል።

ስለሆነም ጉዳዮ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ለሲቪል ነዋሪዎች የሚቀርበው ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይሰናቀፍ እና እንዲሻሻል ተገቢውን ሁሉ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢሰመኮ ጠይቋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ባለፉት 2 ወራት በአዲስ አበባ በፀጥታ ኃይሎች በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረዋል በሚል ከተያዙ የትግራይ ተወላጆች እና የንግድ ቤቶች መዘጋት ጋር በተያያዘ በሚደርሰው በርካታ አቤቱታ ተመስርቶ በተለይ በ2 ክ/ከተሞች ትኩረት በማድረክ ክትትል ማድረጉን አሳውቋል።

ድርጅቶቹ የተዘጉት በደንብ መተላለፍና በወንጀል በመጠርጠር በሚል አዲስ በተቋመውና የህገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ ክትትል እና ቁጥጥር ግብረኃይል ውሳኔ ቢሆንም በርካታ የድርጅት ባለቤቶች በተጠረጠሩበት ወንጀል ወይም ደንብ መተላለፍ ጉዳይ ውሳኔ ስላልተሰጣቸው ድርጅቶቹ ለረጅም ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ ተደርጓል።

ያንብቡ : telegra.ph/EHRC-09-11

@tikvahethiopia
ታላቁ አሊምና ፈቂህ ሐጅ ሙሐመድ አልሳፊ አረፉ።

ሸይኽ ሙሐመድ አልሳፊ ከሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሀቢብ ጋር በመሆን መጅሊስን ከመሰረቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ለኢስላም ሲባል በደርግ መንግስት ታስረው ከፍተኛ የሆነ ግርፋትና ድብደባ የተፈፀመባቸውና በዚህም ምክንያት የመናገር ልሳናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሸይኽ ሙሐመድ አልሳፊ የቀብር ስነ ስርአት ትላልቅ መሻኢኾች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 2 ኮልፌ በሚገኘው መቃብር ከዙሁር በኋላ ይፈፀማል።

Credit : Ethiopia Islamic Affairs Supreme Council

@tikvahethiopia
"እኔም ለወገኔ አለሁ"

በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በደሴ በ13 የመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖቻችን ለአዲሱ ዓመት ዘመን መለወጫ በአል 13 በሬዎች ተበረከተላቸው።

በአሉን ምክንያት በማድረግ "እኔም ለወገኔ አለሁ" ሲሉ 10 በሬዎችን ወሎ ዩንቨርስቲና 3 በሬዎችን የአቶ ሳህሉ ጌታሁን ልጆች በአሜሪካ ከሚኖሩ ልጆቻቸው በወንድማቸው በአቶ በሠለሞን ሳህሉ አማካኝነት አቅረበዋል።

በጠቅላላው 13 በሬዎችን ለተፈናቀሉ ወገኖች አበርክተዋል፡፡

ተፈናቃይ ወገኖችም በአሉን በጋራ በአብሮነትና በአንድነት እንዳከበሩት የደሴ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በአማራ ክልል ውስጥ በጦርነት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በተለያየ መጠለያ ጣቢያ ፤ የቀሩትም በየዘመዶቻቸው ቤት ተጠልለዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየተባባሰ ይገኛል።

በወረርሽኙ ሳቢያ የኮቪድ-19 ህክምና መዕከሎች እየሞሉ መሆኑንም የጤና ባለሞያዎች እየጠቆሙ ናቸው።

የፅኑ ህሙማን ክፍሎችም ሞልተው ታካሚዎች የሚስተናገዱት በወረፋ ነው።

#DrYaredAgidew

@tikvahethiopia
ዛሬ የሀገራችንን 🇪🇹 ልጆች የሚፋለሙበት የእግር ኳስ ግጥሚያ ይኖራል።

ፍልሚያው በአፍሪካ የክለቦች ውድድር ላይ ሲሆን ኢትዮጵያችንን 🇪🇹 የሚወክሉት ደግሞ ፋሲል ከነማ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች ናቸው።

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ የክለቦች ሻንፒዮንስ ሊግ #ከሱዳኑ ሀያል ክለብ አል ሂላል ጋር በባህር ዳር በኢንተርናሽናል ስታዲየም ይጫወታል።

ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ከዩጋንዳው ገቢዎች ባለስልጣን እግር ኳስ ክለብ (URA FC) ጋር ይጫወታል።

ድል ለሀገራችን ክለቦች ፤ ድል ለኢትዮጵያ ልጆች !

@tikvahethsport
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) 85 ሜትሪክ ቶን ህይወት አድን ድጋፎችን ለኢትዮጵያ ማድረጉን ገልጿል።

ድርጅቱ ወደ ኢትዮጵያ ድጋፍ ያደረገው በዱባይ ከሚገኘው መጋዝኑ ውስጥ ሲሆን በአውሮፕላን በማጓጓዝ ወደ ኢትዮጵያ ማድረሱን ገልጿል።

ይህ የዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ ድርጅቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎችን ለመርዳት የያዘው አቅድ አንዱ አካል መሆኑን በድረገጹ የወጣ መረጃ ያስረዳል።

ለኢትዮጵያ በድርጅቱ በኩል የተሰጠው ድጋፍ የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ይህ የጤና ድጋፍ በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት አውሮፕላን በተደረገ የአውሮፕላን ድጋፍ ወደ አዲስ አበባ መግባቱን ዘገባው አክሏል።

በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሃላፊ ዶክተር ቦሬማ ሳምቦ ድጋፉን አስመልክተው አንደተናገሩት በኢትዮጵያ ፦
- በተፈጥሮ አደጋዎች ፤
- በግጭቶች ፤
- በወረርሽኞች እና መሰል ምክንያቶች የጤና ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ምከንያት አሁን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ሀላፊው በቀጣይ ከሌሎች የሰብዓዊ እና ጤና ተቋማት ጋር በመሆን ከ2 ነጠብ 5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia
#Amhara #Afar #Tigray #ICRC #ERCS

በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ህይወታቸውን ለማዳን ቤታቸውን ጥለው በመሠደዳቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮቹ ምቹ ማረፊያ ባለማግኘታቸው በተጨናነቁ መጠለያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍት ቦታ ላይ ለመተኛት ተገደዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ በተሰደዱበት አካባቢ በሚኑሩ ማህበረሰቦች ቢደገፉም፣ በቂ የውሀና የምግብ አቅርቦት ይሻሉ።

የጤና ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት ዋነኛው የሰብአዊ ጉዳይ ሆኗል።

በቅርቡ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

የአለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በአማራና አፋር ክልሎች የመጠለያ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረገ ነው፡፡

ከነሐሴ ወር መጀመሪያ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለ100,600 ሰዎች ፦
- ብርድልብሶች፣
- የማብሰያ ዕቃዎች
- የፋኖስ መብራቶች የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች ስርጭት አድርጓል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ 18 ሆስፒታሎች ለ145,000 ህሙማንና የህክምና ባለሙያዎች የምግብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአማራ ክልል ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች ደግሞ 2000 ቁስለኞችን ለማከም የሚበቃ መድሐኒት ተሠራጭቷል፡፡

በተጨማሪም በአፋር ለሚገኘው የዱፕቲ ጠቅላላ ሆስፒታልና በትራይ የሱሁልና ሽራሮ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በትግራይ ክልል የሚገኙ 14 የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎችን መሠረተ ልማት መልሶ የመገንባት ስራም ተሠርቷል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/ERC-09-12

@tikvahethiopia