Audio
AudioLab
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሙሩ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች በሚደርስባቸው ''ዛቻና ማስፈራሪያ'' ወፌና ኢላሞ ከሚባሉ የገጠር ከተሞች ተሰደው በአጋምሳ ከተማ በሚገኝ ት/ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸውልናል።
* የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።
@tikvahethiopia
* የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
AudioLab
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፤ አሙሩ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚደርስባቸው ''ዛቻና ማስፈራሪያ'' ወፌ እና ኢላሞ ከሚባሉ የገጠር ከተሞች ተሰደው በአጋምሳ ከተማ በሚገኝ ት/ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸውልናል።
በቁጥር 11 ሺ ይሆናሉ የተባሉት ነዋሪዎች ወደ አማራ ክልል በመሰደድ ላይ እያሉ ተከልክለው በትምህርት ቤቱ መጠለላቸውን ችግራቸውን ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ ሰላም ሚኒስቴር የመጡት ሼህ ሀሰን መሐመድ ይናገራሉ።
ከእነዚህ ከተሞች በተጨማሪ በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ በገጠር እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አራት ሆነው እንደሆነ የሚገልጸው ካሳነው አህመድ ከአከባቢው 40 አባወራ አስቀድመው መውጣታቸውንና አሁን ላይ በዛህ ለሚገኙ ወገኖቻቸው ለማመልከት እንደመጡ ይናገራል።
''አሁን ላይ ህይወታቸውን በእንዴት እንደሚያመልጡና እንደሚያተርፉ ለማመልከት ነው የመጣነው'' ሲል በጹሑፍ ለሰላም ሚኒስቴር ማስገባታቸው፤ ሆኖም የሚያናግራቸው እንዳላገኙ ይናገራል።
በወረዳው የኦነግ ሸኔ ኃይል በምን ደረጃ ይገኛል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ''አከባቢው ላይ ወዲያ ወዲህ ሲል የሚታየው "ኦነግ ሸኔ" ነው መሳሪያ እናከፋፍላለን እስከማለትም ደርሰዋል'' ሲል ምላሹን ያስቀምጣል።
ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-25

#ኢትዮጵያ
ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር ክልል በሚያዋስኑ አካባቢዎች ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች እየወጡ ነው።
በአካባቢው ስላለው ሁኔታ ተጨባጭ የሆነ መረጃ ማግኘት አዳጋች ሆኗል ፤ ዝርዝር መረጃም ማግኘት አልተቻለም።
በግጭቱ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተፈናቀሉ ናቸው።
ከቀናት በፊት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ ፥ "ህወሓት" በአፋር ላይ ክፍቶታል ያሉትን ጥቃት የክልሉ ሕዝብ ተጥቅ አንግቦ ራሱን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበው ነበር።
ርዕሰ መስተዳዳሩ ማንኛውም አፋር ባለው የጦር መሳርያ ምድሩን ያስጠብቅ ዘንድ ነው ጥሪ አቅርበው የነበረው፤ ይህም በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቦ ነበር።
ዛሬ ደግሞ የአማራ ክልል ር/መስተዳደር የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገር በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከነገ ጀምሮ ለህልውናው ዘመቻ እንዲዘምት የክተት ጥሪ አስተላልፈዋል።
አቶ አገኘሁ ከተናጠለ ተኩስ አቁሙ በኃላ የህወሓት ቡድን በራያ፣ በወልቃት ፣ በዋግ እንዲሁም በጠለምት ግንባሮች ጥቃት መክፈቱን የገለፁ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልል ልዩ ኃይሎች በጥምረት በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ በቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱበት እንደሆነ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል የነበረው ግጭት በጀመረበት ወቅት ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው እና በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የ ''ህወሓት ቡድን" የትግራይ ህዝብ ባለው የጦር መሳሪያ ሁሉ ወጥቶ እንዲታገል ጥሪ ሲያቀርብ እንደነበር አይዘነጋም፤ አሁን ላይ ደግሞ የአፋር እና አማራ ክልል መሪዎች ለህዝባቸው የክተት አዋጅ አውጀዋል።

#Ethiopia
'MIND ETHIOPIA' በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲኖር በቅርቡ ሀገራዊ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጅ ማስታውቋል።
MIND ETHIOPIA የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ 8 የሀገር ዓቀፍ ድርጅቶች ጥምረት ነው።
ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ሀገራዊ ምክክር በ1 ቀን ተደርጎ የሚቆም ሳይሆን ሒደት እና ቀጣይነት ያለው መሆኑን MIND ETHIOPIA ገልጿል፡፡
የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪና የMIND ETHIOPIA አባል የሆኑት አቶ ንጉሱ አክሊሉ ፥ "ኢትዮጵያ ተለዋዋጭ የፖለቲካ ሁኔታ ያላት በመሆኑ ሁሉን አካታች ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለማድረግ ጠንካራ ሒደቶች እና ሕዝባዊ ድጋፍ ያስፈልጋል፤ ለዚህም ከሀገር ውስጥ እስከ ዴያስፖራው ማሕበረሰብ ድረስ በመነጋገር ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው" ብለዋል።
አቶ ንጉሱ አክለው ፥ ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ዓመታት የገጠሟት የማንነት ፤ የድንበር፤ የሕገ መንግስት ብሎም የታሪክ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በጠረጴዛ ዙሪያ መፈታት እንዳለባቸው ገልጸው ለዚህም ከወር በኋላ ትልቅ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እንደሚኖር አስታውቀዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክርን ' በሕግ አግባብ ' ከሚፈቱ ግጭቶች መለየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል አቶ ንጉሱ ስለማስገንዝበባቸው አሀዱ ሬድዮ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ 'MIND ETHIOPIA ' ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ንግግር እና እርቅ እንዲፈጠር እያደረገ ያለው ጥረት ደግፋለሁ ብሏል።
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፊልትማን ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና የUSAID ተወካዮች ከ 'MIND ETHIOPIA' ጋር መወያየታቸው ታውቋል።
ውይይቱ የነበረው 'MIND ETHIOPIA' በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ንግግር እንዲጀመር እና በብሄራዊ እርቅ እንዲሰፍን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ዙሪያ እንደነበር ተሰምቷል።

#ItsMyDam🇪🇹 ዛሬ ይፋ በተደረገው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማድረጊያ የድረገፅ ፕላትፎርም ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል። Mygerd.com የተሰኘው ድጋፍ ማድረጊያ ድረገፅ ይፋ በተደረገ በደቂቃዎች ውስጥ 36 ሰዎች ባደረጉት ልገሳ ስለማድረጋቸው ታውቋል። በዚህም 1,899 የአሜሪካ ዶላር ሊሰበሰብ ችሏል። አምስትሰዎች ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ስለመቀላቀላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ…
#ItsMyDam🇪🇹
Mygerd.com ይፋ መደረጉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ህዳሴ ግድብን በገንዘብ እንዲደግፉና አሻራቸውን ዕድል ፈጥሯል።
እስካሁን 291 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 23,410 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 28 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡
ድጋፉ ቀጥሏል፡፡ ግድቡም ይጠናቀቃል።
#የኢኤኃ

#Somali
በሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው የበደር የትራንስፖርት ማህበር በዛሬው እለት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ፡፡
ማህበሩ በከተማ ትራንስፖርትና በመካከለኛ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰማራ ሲሆን በቅድሚያም አገልግሎቶቹን በጅግጅጋ ፤ ቱጉጫሌ ፤ ደገሀቡርና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚጀምርም ነው የተገለፀው፡፡
#SRTV

PHOTO : 2ኛው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ የቶኪዮ ተሳታፊ ቡድን ጃፓን ገባ።
ቡድኑ ትላንት ምሽት ወደ ቶኪዮ፣ ጃፓን የተጓዘ ሲሆን #ቶኪዮ በሰላም ደርሷል።
በድኑ ቶኪዮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ፦
- ዶ/ር ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣
- ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የኢአፌ ፕሬዝዳንት፣
- የኢትዮጵያ ኦምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ ዳዊት አስፋው
- ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር
- ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የኢአፌ አቃቤ ንዋይ የአትሌቲክስ ቡድን መሪ ኤርፖርት ተገኝተው ለቡድኑ አቀባበል አድርገውለታል።
#EAF #DrFethWeldesenbet

#Somalia
የሱማሊያ ምርጫ ተራዘመ።
ዛሬ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረውና ለወራት የዘገየው የሱማሊያ ምርጫ ተራዝሟል።
4 ቀናት የሚፈጀው እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የምክር ቤት አባላት እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የሚመረጡበት ምርጫ ዛሬ መጀመር ነበረበት።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የሶማሊያ ምርጫ ኮሚሽን አባል " በተለያዩ ግዛቶች የላይኛው ም/ቤት አባላት ምርጫ ዛሬ ይጀመራል የሚል ዕቅድ የነበረ ቢሆንም እንደታቀደው የሚካሔድ አይመስልም" ሲሉ ለፍራንስ 24 ተናግረዋል።
ግለሰቡ፥ ምርጫው እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የሶማሊያ ግዛቶች የእጩ ተወዳዳሪዎችን ስም ዝርዝር ባለማቅረባቸው እና በየአካባቢያቸው ድምጽ ለመስጠት ኮሚቴ ሳያዋቅሩ በመቅረታቸው ምክንያት ነው ብለዋል።
የሶማሊያ ፌድራል መንግሥት ቃል አቀባይ መሐመድ ኢብራሒም ሞዓሊሙ ምርጫው መራዘሙን ለፍራንስ 24 ቢያረጋግጡም ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
ባለፈው ሳምንት አል-ሸባብ ምርጫው እንዳይካሔድ ለሶማሊያ መንግሥት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።
ከወራት በፊት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድና የአምስቱ የሶማሊያ ግዛቶች መሪዎች በምርጫው አካሔድ ላይ ባለመስማማታቸው አገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ቀውስ ውስጥ ገብታ ነበር።
ጉዳዩ የጸጥታ ቀውስ የፈጠረ ሲሆን ከወራት ውዝግብ በኋላ ፖለቲከኞቹ ምርጫው በሚካሔድበት መርሐ-ግብር ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።
ይሁንና ከጁባላንድ ውጪ ሌሎቹ ግዛቶች ምርጫ ለማካሔድ ዝግጁ እንዳልሆኑ ፍራንስ 24 ዘግቧል።
መረጃውን ያዘጋጀው ዶቼ ቨለ ነው።

#Amhara
የአማራ ክልል ህዝብ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው የመንግስት አካል እንዲወስድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ።
አቶ አገኘው ይህን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት ዛሬ ለአማራ ክልል ህዝብ የክተት አዋጅ ባወጁበት ወቅት ነው።
ኅብረተሰቡ መረጃ እንደሚያስፈልገው እናውቃለን ያሉት አቶ አገኘሁ ፥ ነገር ግን ሁሉም የጦርነት መረጃ አይሰጥም ብለዋል። "በዚህ በኩል እያጠቃን ነው፤ በዚህ በኩን እየተጠቃን ነው ፤ በዚህ በኩል እንዲህ አይነት ወታደራዊ መሬት ይዘናል ተብሎ መረጃ አይሰጥም" ሲሉ አስገንዝበዋል።
አንዳንዱ #በፌስቡክ ጦርነት ሊመራ ይፈልጋል ይህ ተገቢ አይደለም መታረም አለበት ብለዋል።
አስፈላጊው መረጃ በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ይሰጣል ያሉ ሲሆን ህዝቡ መረጃዎችን ከትክክለኛው አካል መውሰድ እንደሚገባው አሳስበዋል።
ትግራይ ክልልን በሚያዋስኑት የአማራ ክልል እና በአፋር ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች ቢኖሩም መሬት ላይ ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ፍፁም አዳጋች ሆኗል።
ትክክለኛ መረጃ ባለመኖሩም ህዝቡ ለፕሮፖጋንዳ እና ለሀሰተኛ መረጃዎች ፣ እንዲሁም ለአክቲቪስቶች ያልተጨበጠ ወሬ እንዲጋለጥ ማድረጉን በርካቶች እያነሱ ነው።

#ምርጫ2013
በምርጫ ላይ 2013 በምርጫ አስፈፃሚነት ሀገራቸውን ያገለገሉ ዜጎች ክፍያ እንደዘገየባቸው ጠቁመዋል።
የምርጫ አስፈፃሚዎች " ክፍያ ዘገየብን ፤ ለመዘግየቱ ምክንያት ምንድነው ? መቼ ነውስ ክፍያው የሚፈፀምልን ?" ሲሉ ጥያቄያቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ምላሽ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽ አማካሪ የሆኑት ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ክፍያው የዘገየው ፥
- ንብረት ርክክብ መጠናቀቅ ስላለበት፣
- የበጀት መዝጊያ ስለሆነም መልሶ መከፈት ስላለበት፣
- የመጨረሻው ክፍያ ስለሆነ
- በድምፅ መስጫ ቀን ሰው ስለተጨመረ ቁጥሩ ብዙ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ወ/ሪት ሶሊያና ፥ የምርጫ አስፈፃሚዎች ክፍያ እንደተለመደው እንደሚከፈል የገለፁልን ሲሆን መታገስ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

#Tokyo2020
ታዳጊዋ ለሀገሯ ወርቅ አስገኘች !
የ13 ዓመቷ ጃፓናዊት የ #SkateBoard ተወዳዳሪ ሞሚጂ ኒሺያ ለሀገሯ ጃፓን በውድድር ዘርፉ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝታለች።
ሞሚጂ ኒሺያ በ ታሪክ ለ ሀገሯ ወርቅ ያስገኘች በ እድሜ ትንሿ ተወዳዳሪም ለመሆን በቅታለች ።
@tikvahethsport