TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች።

ዛሬ ምርጫ በሚካሄድባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሯል።

ከተለያዩ ከተሞች የወጡ ፎቶዎችን መመልከት እንደቻልነው ፥ ህዝቡ በለሊት ተነስቶ ድምፁን ለመስጠት ሰልፍ ይዟል።

ወደ በኃላ ምርጫውን ተንቀሳቅሰው ለመመልከት ፍቃድ ያገኙ የቲክቫህ አባላት በየምርጫ ጣብያው በመገኘት ያለውን ሁኔታ በቀጥታ በVoice Chat በቀጥታ ያሳውቃሉ።

Photo Credit : AAPS

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ምርጫ 2013 በሚመልከት የTikvah-Ethiopia አባላት በመልዕክት መቀበያ አድራሻዎች መልዕክታቸውን እያስቀመጡ ነው።

ከለሊት 11:30 ጀምረው ተሰልፈው ምርጫ ጣቢያ ከጥዋት 1 ሰዓት በኃላ የተከፈተበት ቦታ እንዳለ፣ በአዲስ አበባ እና በክልል ባሉ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ለምርጫው ቢገኙም ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸውን አሳውቀዋል።

አባላቶቻችን እስካሁን ባለው የተመለከቱት ችግር ምርጫው ይጀመራል ተብሎ ይፋ በተደረገበት ሰዓት አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው መራጮችን አለማስተናገዳቸውን ነው።

ከዚህ ባለፈ የኮቪድ-19 መከላከያ ፕሮቶኮል ያለማክበር ችግር እንዳለ አንስተዋል።

በፀጥታ እና በሰላም በኩል ግን ሂደቱን በተረጋጋ መንፈስ እየሄደ እንዳለ አባላት እያሳወቁ ነው።

የድምፅ መስጫ ሰዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ እየተከተልን እናሳውቃለን።

Photo Credit : Tikvah Family

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፦

- የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየት ፣
- በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚታይ መደነጋገር፣
- ሰዓት አለማክበር፣
- የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል አለመጠበቅ፣
- ረጃጅም ሰልፎች (በፍጥነት አለመሄድ) ፣
- የሰልፍ ተራ አለመጠበቅ፣
- የምርጫ ቁሳቁስ መቀያየር
- ቀልጥፍ ያለ መስተንግዶ ክፍተት
- መራጮች ምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱበትን መታወቂያ ሳይዙ መሄድ
- "እከሌን ምረጡ" የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከር የመሳሰሉት ችግሮች ከመስተዋላቸው በዘለለ የምርጫ ሂደቱ #በሰላም እየተካሄድ መሆኑን ከአዲስ አበባና ከክልል የምርጫ ጣቢያዎች የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

የ Tikvah - Ethiopia አባላት በተመለከቷቸው የምርጫ ጣቢያዎች እድሜያቸው የገፋ ዜጎች ፣ እናቶች አባቶች ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው ተመልከተዋል። ነፍሠ ጡሮች፣ ልጅ የታቀፉ እናቶች ተሰልፈው ድምፅ ሲሰጡ አስተውለዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በፀጥታ እና በሰላም ረገድ ምንም ጥቆማ ከአባላቶቻችን አልተላከም፤ ሁሉም ሂደት #በተረጋጋ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀውልናል።

Photo Credit : Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
ፎቶ : የኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ መካሄድ ከጀመረ ሰዓታት ተቆጥረዋል፤ አሁንም የድምፅ መስጠት ሂደቱ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ቀጥሏል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#LIVE

ውድ ቤተሰቦቻችን ሁለት በቀጥታ የሚሰራጩ ጉዳዮች ፦

- የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል እስካሁን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት (ከ4:30 ጀምሮ)

- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ከስካይ ላይት ሆቴል ከስፍራው እናሰማችኃለን (ሰዓቱ ሲደርስ እንነግራችኃለን)

@tikvahethiopia
Live stream finished (3 minutes)
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ፦
- ሰሚት 2 የምርጫ ጣቢያ፤
- ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 1፤
- ምሥራቅ በር ምርጫ ጣቢያ፤
- ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 6 እና ምርጫ ጣቢያ 4.1 ተዘዋውረን የምርጫ ሂደቱን ተመልከትናል።

በቀጥታ Voice Chat መከታተል ያልቻላችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የፖሊስ ሪፖርት :

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአገር አቀፍ ደረጃ እስከአሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይ ተመሳሳይ መረጃ ከፌዴራል ፣ ከክልልና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : ይህ አ/አ አያት ዞን ሁለት የሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ነው። መራጩ ዜጋ ከጥዋት ጀምሮ ተሰልፏል፤ ሰልፉ ግን የሚጠበቀውን ያህል ንቅንቅ አላለም።

ሌሎችም ጣቢያዎች ላይ ቀደም ብለን እንዳሳወቅነው ተመሳሳይ ሁኔታ ይታያል፤ ይህ ሁናቴ መራጩን ዜጋ እያሰላቸ ነው #መፍትሄ ይፈልጋል።

(የቲክቫህ አባላት)

@tikvahethiopia