' የካራማራው ጀግና '
የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ከባሕር ዳር ጋምቢ ሆስፒታል ወደ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው።
የካራማራው ጀግና ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ግንቦት 08/2013ዓ.ም በደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
አስከሬናቸው በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፍትሃት ተደርጎለት ዛሬ ወደ ደብረታቦር ይሸኛል።
ነገ በደብረታቦር አጅባር ሜዳ የጀግና አሸኛኘት ከተደረገላቸው በኋላ ነው ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀመው። (አሚኮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
' የካራማራው ጀግና ' የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ከባሕር ዳር ጋምቢ ሆስፒታል ወደ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው። የካራማራው ጀግና ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ግንቦት 08/2013ዓ.ም በደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል። አስከሬናቸው በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፍትሃት…
ብ/ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ተሰማ ፦
- በድሮው አስተዳደራዊ አወቃቀር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጥር 28 /1933 ዓ/ም ነበር የተወለዱት።
- እስከ ጄነራልነይ ማዕረግ ያደረሳቸውን ህይወታቸውን በውትድርና የጀመሩት በ1960 ዓ/ም ነበር።
- በሶማሊያ ወረራ ወቅት የ69ኛውን ሚሊሻ ብርጌድ በማሰልጠን በግንባርም አዋጊ ሆነው በመምራት ታላላቅ ጀብዶችን ለሀገራቸው የፈፀሙ ነበሩ።
- መስከረም 1970 ዓ/ም ላይ በድሬዳዋ ግንባር ወደውጊያ የገቡ ሲሆን ካራማራ፣ ጅግጅጋ፣ ደጋሀቡር እና ቀብሪደሃር (መጋቢት 1/1970) ከሶማሊያ ጦር ወረራ ነፃ አውጥተው በመቆጣጠር የምስራቁን ግንባር ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ ያደረገውን ብርጌድ መርተዋል።
- ከወታደራዊ ስራቸው ተጨማሪ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክ/ሀገሮችን አስተዳድረዋል።
- የፌዴራል መንግስት ተቋማትን መርተዋል።
- ለሀገራዊ አገልግሎታቸው የህበረተሰባዊ ኢትዮጵያ ታላቅ የክብር ኮከብ ኒሻን እና የየካቲት 66 አብዮት ኒሻን እና ሌሎች ሽልማቶችን አግኝተዋል።
- ባለትዳር እና የ7 ልጆች አባት ነበሩ።
#አሚኮ

#Update
ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ነው።
በመድረኩ ላይ ትላንት የተጠናቀቀውን የመራጮች ምዝገባ በተመለከተ ጊዜያዊ መረጃ ተሰጥቷል።
በዚህ መሰረት ፦
- እስከ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ያ36 ሚሊዮን 245 ሺህ 444 ሰዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።
- ምርጫ ካርድ ከወሰዱት ውስጥ 16.6 ሚሊዮኑ ሴት ፤ 19.5 ሚሊዮኑ ወንድ ናቸው፡፡
- 50 ሚሊዬን ዜጎች ካርድ ሊወስዱ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር፡፡ አሁን ያለው ካርድ የወሰዱ ዜጎች ቁጥሩ የግምቱን 78 በመቶ ይሸፍናል።
- ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ከተገመተው በላይ የመራጮች ካርድ የተወሰደባቸው ናቸው።
- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንጻራዊነት ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ የተከናወነበት ክልል ነው።
በዝርዝር ስንመለከተው ፦
• በአዲስ አበባ ከ1.4 ሚሊዬን፣
• በአፋር ከ1.7 ሚሊዬን፣
• በአማራ ከ5.9 ሚሊዬን፣
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ174 ሺ፣
• በጋምቤላ ከ326 ሺ፣
• በኦሮሚያ ከ15.9 ሚሊዬን፣
• በሃረር ከ135 ሺ፣
• በድሬዳዋ ከ177 ሺ፣
• በደቡብ ብ/ብ/ህ ከ4.8 ሚሊዬን፣
• በሲዳማ ከ1.5 ሚሊዬን እና በሶማሌ ከ3.9 ሚሊዬን በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸውን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። (አል ዓይን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#BREAKING
6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው።
ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር።
የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል።
ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም ፓርቲዎችን መጠየቁን አል ዓይን ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#BREAKING 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው። ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር። የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል። ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም…
የድምፅ መስጫ ቀን ማራዘም ያስፈለገው ለምንድነው ?
ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቀን ሊራዘም እንደሚችል አስታውቋል።
ቦርዱ የምርጫው ጊዜ ቀድም ብሎ ከተያዘለት ጊዜ እስከ 3 ሳምንት በሚደርስ ጊዜ ነው እንደሚራዘም የገለፀው።
ምክንያት ብሎ ያቀረበው ፦
- የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት የወሰደው ጊዜ በመኖሩ ፤ ውጭ ሀገር የሚታተመው ወረቀት የሚገባበት ጊዜ ሂደቱን ሊያጓትት ስለሚችል (በመጪው 15 ቀን መጨረሻ ነው ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው)
- የመራጮች ምዝገባ የወሰደው ተጨማሪ ጊዜ በመኖሩ
- ለቁሳቁስ ማጓጓዣ በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልግ
- በአንድ ምርጫ ጣቢያ 3 የነበሩትን የምርጫ አስፈፃሚዎች መጨመር ስለሚያስፈልግ ለነሱ ስልጠና መስጠት ጊዜ ስለሚወስድ ይህን ለማስተካከል ነው የምርጫው ጊዜ እንዲራዘም ያለው።
ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ምክክር አሁንም የቀጠለ ሲሆን የሚደረስበትን ድምዳሜ ተከታትለን እናሳውቃለን።

የድሬዳዋ እና አዲስ አበባን ጨምሮ 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በአንድ ቀን እንዲካሄድ ተወሰነ።
ይህ ውሳኔ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ላይ ነው የተወሰነው።
በውሳኔው መሰረትም ከአሁን ቀደም ተለይቶ እንዲካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የነበረው የድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ምርጫ በአንድ ቀን ይካሄዳል መባሉን አል ዓይን ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የድሬዳዋ እና አዲስ አበባን ጨምሮ 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በአንድ ቀን እንዲካሄድ ተወሰነ።
ይህ ውሳኔ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ላይ ነው የተወሰነው።
በውሳኔው መሰረትም ከአሁን ቀደም ተለይቶ እንዲካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የነበረው የድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ምርጫ በአንድ ቀን ይካሄዳል መባሉን አል ዓይን ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የድሬዳዋ እና አዲስ አበባን ጨምሮ 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በአንድ ቀን እንዲካሄድ ተወሰነ። ይህ ውሳኔ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያካሄደ በሚገኘው የምክክር መድረክ ላይ ነው የተወሰነው። በውሳኔው መሰረትም ከአሁን ቀደም ተለይቶ እንዲካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የነበረው የድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ምርጫ በአንድ ቀን ይካሄዳል መባሉን አል ዓይን ዘግቧል። @tikvahethiopia…
"...ድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን የተወሰነው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበ ጥያቄ ነው" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
የ6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ በሁሉም አካባቢዎች በአንድ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በተመለከተ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው መድረክ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቀደም ሲል የአገራዊ ምርጫው የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ቀን 2013 እንደሚሆን የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት እንደነበር አስታውሰዋል።
ነገግ ግን ቦርዱ የድምጽ መስጫው ቀን በመላ አገሪቱ በተመሳሳይ ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን በይፋ አሳውቀዋል።
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፥ የድምጽ አሰጣጡ በተመሳሳይ ቀን እንዲሆን ከውሳኔ የተደረሰው ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና ከፓርቲዎች በቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑን አስረድተዋል።
#ENA

#NewsAlert
እስራኤል በጋዛ ከተማ የሚገኝ የአልጀዚራ ቢሮን ጨምሮ ሌሎችም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ያሉበትን ህንፃ በአየር ጥቃት ወደፍርስራሽነት እንደምትቀይረው አስጠንቅቃለች።
እስራኤል የአየር ጥቃቱን የምትፈፅመው በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሲሆን ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ቀደም ብላ መልዕክት አስተላልፋለች።
በሌላ መረጃ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈፀመች ባለው ጥቃት የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 140 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 39 ህፃናት ይገኙበታል፤ ቁስለኞች ከ950 በልጠዋል።
እንደUN ሪፖርት በጋዛ 10 ሺ የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤልን የአየር ድብደባ ሽሽት ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።
ሀማስ ወደ እስራኤል የሚያስወነጭፋቸው ሮኬቶች የቀጠሉ ሲሆን ዛሬ በማዕከላይ እስራኤል 'ራማት ጋን' አንድ እስራኤላዊ ገድሏል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
* Update
የአልጀዚራ፣ AP እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚገኙበትን ግዙፍ ህንፃ እስራኤል በአየር ጥቃት ወደፍርስራሽነት ቀይራዋለች።
የሀገሪቱ ጦር ቀድም ብሎ በ1 ሰዓት ውስጥ ጥቃት እንደሚፈፅም በመግለፅ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ አስጠንቅቆ ነበር።
በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል የተነሳው ግጭት ከዕለት ወደዕለት እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ጋዛ ውስጥ እስራኤል በምትፈፅመው ጥቃት 140 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል ፤ ሀማስም ወደ እስራኤል ትልልቅ ከተሞች ሮኬት በማስወንጨፍ እስራኤላውያን ገድሏል።
አሁንም ግጭቱ እንዲበርድ ዓለም አቀፍ ጥሪዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤልና በፍልስጥኤም ግጭት ላይ ነገ ለውይይት ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

* Djibouti
ለ5ኛ ጊዜ የጅቡቲን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 98% የመራጮች ድምፅ በማግኘት እንዳሸነፋ የተነገረላቸው ኢስማኤል ኦመር ጌሌህ በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል።
በበዓለ ሲመታቸው ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሱማሊያ ጠ/ሚ ሙሀመድ ሁሴን ሮቤሌን ጭምሮ ሎሎችም ተገኝነት ነበር።
በሌላ መረጃ ፦
ለፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ በዓለ ሲመት ጅቡቲ ሄደው የነበሩት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደኢትዮጵያ ተመልሰው በአፋር ክልል የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፍተዋል።
ጠ/ሚስትሩ ፓርኩን በመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ፥ "አሁን ባለው ፕሮፖጋንዳ እና የሚዲያ ዘመቻ ሳንበረከክ የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ የኢትዮጵያን ከፍታ እውን በማድረግ ለዓለም እናሳየለን " ሲሉ ተደምጠዋል።
የሠመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በታቀደው እና ለሌሎችም ሞዴል በሚሆን መንገድ እንደተከናወነ ገልፀዋል።
ይህም "ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የምንፈልገውን መስራት እንደምንችል ማሳያ ነው" ብለዋል፡፡
በቀጣይም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ብልጽግና ማንም አያስቆመውም ያሉ ሲሆን አንዳንድ ሀገራት በሀገሪቱ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ይሞክራሉ፤ ነገር ግን ይህ ታሪክን አለማወቅ ነው" ሲሉ መደመጣቸውን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን (etv) የተገኘው መረጃ ያሳያል።

* Update የአልጀዚራ፣ AP እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚገኙበትን ግዙፍ ህንፃ እስራኤል በአየር ጥቃት ወደፍርስራሽነት ቀይራዋለች። የሀገሪቱ ጦር ቀድም ብሎ በ1 ሰዓት ውስጥ ጥቃት እንደሚፈፅም በመግለፅ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ አስጠንቅቆ ነበር። በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል የተነሳው ግጭት ከዕለት ወደዕለት እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ጋዛ ውስጥ እስራኤል በምትፈፅመው ጥቃት 140 ፍልስጥኤማውያን…
AP እና አልጀዚራ ስለጥቃቱ ምን አሉ ?
የአሶሼትድ ፕሬስ ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌሪ ፕሩይት ባወጡት መግለጫ ፥ የእስራኤል ጦር የAP ቢሮ እና ሌሎች የሚዲያ ተቋማት ያሉበትን ህንፃ እንደሚያወድም በሰሙ ጊዜ እጅግ እንደደነገጡ ገልፀዋል።
አክለውም ለረጅም ጊዜ የቢሯችንን እና የጋዜጠኞቻችን መገኛ ያውቃሉ ፤ ህንፃው እንደሚመታ ቀድሞ ማስጠንቀቂያ ደርሶናል ብለዋል።
በወቅቱ ህንፃ ውስጥ በርካታ ጋዜጠኞች እና ፍሪላንሰሮች ነበሩ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ግን ቀድመን አስወጥተናቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ጋር በመሆን ከእስራኤል መንግስት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አሳውቀዋል።
በዛሬው ክስተት ምክንያት ዓለም በትንሹም ቢሆን በጋዛ እየሆነ ስላለው ነገር ያውቃል ብለዋል የAP ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚው።
የአልጀዚራ ሚዲያ ኔትወርክ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሞስጠፋ ሶዋግ ጥቃቱን “አረመኔያዊ” ሲሉ ገልጸው እስራኤል ተጠያቂ መሆን አለባት ብለዋል።
አክለው ፥ “የዚህ አስከፊ ወንጀል ዓላማ ሚዲያዎችን ዝም በማሰኘት በጋዛ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን እልቂት እና ስቃይ መደበቅ ነው” ብለዋል።
የእስራኤል ጦር ግን "ሚዲያዎችን ዝም" ለማሰኘት ነው በሚል የቀረበውን ክስ አጣጥሎታል ፤ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው ሚዲያዎች የጥቃቱ ኢላማ አልነበሩም ብሏል።
ህንፃውን ሊያወድመው እንደሆነ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ፤ ሲቪል ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ጊዜ ሰጥቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።
ህንፃው የሃማስ ወታደራዊ መረጃዎችና ንብረት የሚገኙበት ነበር ብሏል።
ህንፃው ውስጥ የሲቪል ሚዲያ ቢሮዎች ያሉበት ቢሆንም ሀማስ ይህን እንደመሸሸጊያ ሲጠቀምበት እንደነበር አስረድቷል።