TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'ከሟቾቹ መካከል 14ቱ ከኦሮሚያ ክልል ናቸው'

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ31 ዜጎቿ ህይወት በኮቪድ-19 ያለፈ ሲሆን ከሟቾች ውስጥ 14ቱ ከኦሮሚያ ሪፖርት የተደረጉ መሆኑን ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦ ባለፉት 24 ሰዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው 5,393 የላብራቶሪ ምርመራ 637 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 262,217 አድርሶታል።

ትላንት 1,444 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 208,314 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 50 ሺህ 030 ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ፤ 749 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮቪድ-19 ክትባትን በተመለከት ፦ ክትባት የወሰዱ ዜጎች 1,290,828 መድረሳቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
'የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን ተከታተሉ'

ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትላትን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity እንዳሳወቀው የዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች በምን መልኩ በምርጫ ይሳተፉ ? በሚለው ላይ እስካሁን በሚኒስቴሩ ደረጃ ምንም የተወሰነ ውሳኔ የለም።

ነገር ግን የተለያዩ ኒቨርሲቲዎች በውስጥ ማስታወቂያ ከምርጫው በፊት 1 ሳምንት ከምርጫው በኃላ 1 ሳምንት ተማሪዎቻቸውን እንደሚበቱ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ሌሎች ደግሞ በውስጥ ማስታወቂያቸው "ከምርጫው በፊት ተማሪዎች ይበተናሉ" ስለሚባለው ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደለ እንዲሁም የሚናፈሰው መረጃም ውሸት እንደሆነ በመግለፅ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያሳበቡ ይገኛሉ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆናችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ተማሪዎች በምን መልኩ ነው በምርጫው የሚሳተፉት ? ለሚለው ጉዳይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ መረጃ ሲላክልን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

እስከዚያው ግን በተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች ላይ ሆነ የፌስቡክ ገፆች ላይ የሚወጡትን የተለያዩ መረጃዎች በመቀባበል ሳትረበሹ #በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን እየቀጠላችሁ ይፋዊ የሆነውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ትጠብቁ ዘንድ አደራ እንላለን።

አዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመዳቢ ተማሪዎች በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት በጠየቅ እናሳውቃለን። በተጨማሪም የ2013 ሀገር አቀፍ ፈተና ሂደትን ከትምህርት ሚኒስቴር ጠይቀን እናሳውቃለን።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሉበርካታ የተጣረሱ መረጃዎች እንዳትደናገሩ።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
በአ/አ በአንድ ግለሠብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተደበቀ ከ4 ሺ በላይ የተለያዩ ጥይቶች እና አንድ ሽጉጥ ተያዘ !

ዛሬ ምሽት የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በአንድ ግለሠብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተደበቁ ከ4 ሺህ በላይ የተለያዩ ጥይቶች እና አንድ ሽጉጥ ተይዟል።

ፖሊስ እንዳለው የተደበቀው ጥይት እና ሽጉጥ የተያዘው በህዝብ ጥቆማ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅንጅት በተሰራ ስራ ነው።

የከተማዋን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ እኩይ አላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የጦር መሳሪያዎችን በህገ ወጥ መንገድ ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ በህዝብ ጥቆማ እና በፀጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሚገኙ ፖሊስ ያስታወሰ ሲሆን ለዚሁ ሀገርን የማፍረስ አላማ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጠርጣሪ ነው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጎፋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተያዘው ሲል አሳውቋል።

ግለሰቡ በመኖሪያ ቤቱ ደብቆ ያስቀመጣቸው ፦
- 3007 የማካሮቭ ሽጉጥ፣
- 1320 የብሬን፣
- 05 የክላሽንኮቭ በአጠቃላይ 4 ሺህ 332 ጥይቶች እንዲሁም አንድ የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በተጨማሪም ባዶ የጥይት ማሸጊያ ሳጥኖች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል ገልጿል።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብሏል።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አጠራጣሪ የሆነ ነገር ሲያጋጥመው በመረጃ የስልክ ቁጥሮች 0111110111 ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ደውሎ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ቻይናው ሮኬት ማርች 5B"

ቻይና ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ስብርባሪዎች በሕንድ ውቂያኖስ ላይ ማረፋቸውን አስታውቃለች።

የሮኬቱ አብዛኛዎቹ ክፍሎች ወደ ምድር በሚምዘገዘጉበት ወቅት ተቃጥለው አየር ላይ የቀሩ ሲሆን አንዳንድ ስብርባሪዎች ግን በታሰበው ቦታ ላይ ማረፋቸውን የቻይና ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ማርች 5ቢ ምንድነው ?

'ማርች 5ቢ' ለሮኬቱ የተሰጠው ስያሜ ነው። ሮኬቱ ባሳለፍነው ወር መገባደጃ ላይ ነበር ቻይና በሕዋ ላይ ለመስራት ላሰበችው ማዕከል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ይዞ የተወነጨፈው።

18 ሺህ ኪሎ ግራም ይመዝናል። በአስርት ዓመታት ውስጥ ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደ ምድር የሚወድቅ ግዙፍ ቁስ ነው ተብሎ ነበር።

የዚህ ሮኬት ስብርባሪ አካላት ደግሞ በትክክል መቼ እና የት እንደሚወድቁ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም መባሉ ስጋት ፈጥሮ ነበር።

ቻይና እየተወቀሰች ነው ፤ ለምን ?

ቻይና እየተወቀሰች የሚገኘው የሮኬቱን ስብርባሪዎች መውደቂያ ቦታ እና ትክክለኛ ሰአት መቆጣጠር አለመቻሏ ግድየለሽነቷን የሚያሳይ ነው በሚል ነው።

አገሪቱ ግን ስብርባሪዎቹ ዓለማቀፍ የውሃ ክልል ውስጥ እንደሚወድቅ አውቅ ነበር ብላለች።

ቻይና ለምንድነው የራሷን ከህዋ ጣቢያ ምትገነባው ?

በአሁኑ ጊዜ በህዋ ምህዋር ላይ የሚገኘው ብቸኛው ዓለም አቀፍ የህዋ ምርምር ጣቢያ፣ በእንግዝኛ ምሕጻሩ አይኤስኤስ (ISS) ነው።

ቻይና በዚህ ጣቢያ ውስጥ አልታቀፈችም።

ለዚህም ነው ቻይና በአውሮፓውያኑ 2022 የራሷ የህዋ ጣቢያ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየሰራች የምትገኘው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፀጥታ ኃይሎች ምረቃ : * ፌዴራል ፖሊስ ! ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ ምልምል የፖሊስ አባላት አስመርቋል። በጦላይ ወታደራዊ ማስልጠኛ ማዕከል ሰልጥነው በዛሬ እለት ለምርቃት የበቁት 6 ሺህ 431 ምልምል ፖሊሶች ናቸው። ከእነዚህ መካከል 792ቱ የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ታውቋል። * የአማራ ክልል ፖሊስ ! የአማራ ክልል…
የቀጠለው የፀጥታ ኃይሎች ምረቃ ፦

ዛሬ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይል ፖሊሶችን አስመርቋል፡፡

በተጨማሪ የልዩ ኃይል ፖሊሶች መኪና አሽከርካሪዎችም ተመርቀዋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የደቡብ ሱዳን ፓርላማ ተበተነ !

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሀገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት (ፓርላማ) እና የክልል ምክር ቤቶች እንዲበተኑ ወስነዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ውሳኔውን ያሳለፉት እ.ኤ.አ. በ2018 በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሠረት ፣ የሀገሪቱ መንግስት ተቃዋሚዎች የተካተቱበት አዲስ ፓርላማ እንደገና እንዲዋቀር ለማድረግ ነው፡፡

የሀገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እንዲበተኑ የሚደነግገው የፕሬዝደንቱ ውሳኔ የተነገረው ቅዳሜ ምሽት ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን በተላለፈው ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ ነው፡፡

በመንግስት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ በይፋ ከጁባ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት የብሔራዊው ፓርላማ አባላት እና የክልሎች ምክር ቤት አባላት የአገልግሎት ጊዜ አብቅቷል፡፡

በ2018ቱ የሰላም ስምምነት የተሳተፉ ፓርቲዎች 400 አባላት የነበሩት ብሔራዊ ፓርላማው 550 አባላትን እንዲያካትት የተስማሙ ሲሆን በሳልቫ ኪር የሚመራው መንግስት 332 አባላት ሲኖሩት ፣ በሪክ ማቻር የሚመራው የታጠቀ የተቃዋሚ ቡድን ደግሞ 128 አባላት ይኖሩታል፡፡ ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ በ 50 አባላት ይወከላሉ፡፡

ፓርቲዎቹ በተጨማሪም የክልሎች ምክር ቤቶች በሰላም ስምምነቱ ለእያንዳንዱ ፓርቲ በተመደበው መጠን የሚከፋፈሉ 100 አባላትን እንዲያካትቱም ተስማምተዋል፡፡

እስካሁን የክልል ም/ቤት አባላት 50 የነበሩ ሲሆን በአዲሱ ስምምነት መሠረት የአባላቱ ቁጥር በእጥፍ አድጓል፡፡

የመንግስት የስራ አስፈፃሚ አካል ባለፈው ዓመት መመስረቱን ተከትሎ ሁለቱ ምክር ቤቶች ተበትነው እንደአዲስ መዋቀር የነበረባቸው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
'ኢፍጣር'

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ "መስቀል አደባባይ" በዓይነቱ ትልቅ የተባለ የኢፍጣር ዝግጅት ለማዘጋጀት የተለያዩ ስራዎች ባለፉት ቀናት ሲሰራ ቆይቷል።

ነገር ግን ይህን ታላቅ ነው የተባለው የኢፍጣር ፕሮግራም አልጋ በአልጋ ሆኖ ሊሳካ አልቻለም።

ህዝቡ ለኢፍጣር ወደ አካባቢው ቢሄድም የፀጥታ ኃይሎች እንዲመለሱ አድርገዋል። የአስለቃሽ ጭስም መተኮሱን በስፍራው የነበሩ አባላት ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ እጅግ በርካታ ነገር እየተባለ ቢሆንም አዘጋጆቹ ግን በመንግስት አካል ተገደው እንደሰረዙት ገልፀዋል።

የዛሬውን ፕሮግራም አዘጋጅተው የነበረው ሀላል ፕሮሞሽን ፣ ከነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን ነበር።

“ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል ከተዘጋጀው ፕሮግራም ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ለዝግጅቱ ህጋዊ ፍቃድ ከሚመለከተው አካል አግኝቶ እንቅስቃሴ መጀመሩ አስታውሰዋል።

ሆኖም ከመንግስት አካላት ዘንድ የዝግጅት ቦታውን እንዲቀየር የተጠየቀ ሲሆን ይህም ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት በማስረዳት ንግግር ሲደረግ ነበር።

ነገር ግን መንግስት በአቋሙ በመፅናቱ አዘጋጆቹም እንደተለዋጭ የተሰጠው ቦታ ላይ ፕሮግራሙን ማከናወን የማንችሉ መሆኑን በመግለፅ ዝግጅቱን ለመሰረዝ ተገደዋል።

ምንም እንኳን ዝግጅቱ ቢሰረዝ በርካቶችም ቀድሞ ወደተዘጋጀው ቦታ ለመሄድ ሞክረው ነበር። የፀጥታ ኃይሎች በየአካባቢው ሆነው ክልክላ ተፈፅሟል።

በዛሬው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ በታዳሚነት እንድንገኝ እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጥሪ ካርድ ተዘጋጅቶልን የነበረ ቢሆንም ፕሮግራሙን ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሰረዙን ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-09

@tikvahethiopia
"..ይህን ታሪካዊ ክስተት እንዲደናቀፍ እጅ የነበራቸው ሁሉ ተጠያቂ ሲሆኑ ማየት እንሻለን" - ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የዛሬው የአፍጥር ታዳሚ ቁጥር 100 ሽ እንደሚደርስ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ገልፀዋል።

ኡስታዝ ያሲን በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ፥ "ይህ ህዝብ ባሰበው እና በታቀደው መልኩ በሰላም አፍጥሮ፣ ለሀገሩ ሰላም ፀልዮ ፣ ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር ማዕድ ተካፍሎ ቢጠናቀቅ ለኢትዮጰያ ደማቅ ታሪክ ይሆን ነበር" ብለዋል።

ይህን ታሪካዊ ክስተት እንዲደናቀፍ እጅ የነበራቸው ሁሉ ተጠያቂ ሲሆኑ ማየት እንሻለን ሲሉም ገልፀዋል።

በ Hayat Regency በኩል ከነበረው በርካታ ምዕመናን ጋር አብረው እንዳፈጠሩ ተገለፁት ኡስታዝ ያሲን ፥ ምእመኑ ከእሳቸው ጋር አብሮ ሰግዶ በሰላም መለያየቱን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia