TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...የውሸት መረጃ ነው፤ የኢትዮጵያ መከላከያ አንዳችም የአፀፋ እርምጃ አልወሰደም" - አቶ ተስፋሁን ሲሳይ

ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "የኢትዮጵያ መከላከያ በሱዳን ኃይሎች የተያዘውን ቦታ አስለቀቅ፤ ሱዳኖቹም አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል" የሚሉ የተለያዩ ወሬዎች ሲሰራጩ ነበር።

የምዕራብ ጎንደር ዞን የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋሁን ሲሳይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚወራው #ሀሰት መሆኑ ለቢቢሲ ሬድዮ የትላንት ስርጭት ተናገረዋል።

የሱዳን ኃይል ከዚህ ቀደም የያዘውን አካባቢዎች አሁንም ለቆ አልወጣም ብለዋል።

አቶ ተስፋሁን፥ "አሁን ባለው ሁኔታ ምንም አይነት ግጭት የለም፤ አሁንም ቦታዎቹን እነሱ እንደያዙት ነው ያለው፤ የተለየ የተደረገ እንቅስቃሴ የለም በኢትዮጵያ በኩል" ሲሉ ተደምጠዋል።

በአካባቢው የመከላከያ እና ሌሎችም የፀጥታ ኃይሎች ስለመኖራቸው እና የወሰዱት የአፀፋ እርምጃ/ቦታዎቹን ለማስለቀቅ ያደረጉት ጥረት እንዳለ የተጠየቁት ኃላፊው ፦ በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች መኖራቸውን ገልፀው እስካሁን ቦታውን ለማስለቀቅ ያደረጉት ጥረት እንደሌለ /የአፀፋ እርምጃም እንዳልተወሰደ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጦር እርምጃ ወስዶ የሱዳን ኃይል የያዘውን ቦታ ለቆ ወጥቷል ተብሎ የሚወራውን ጉዳይም አቶ ተስፋሁን ፥ "ይሄ የውሸት መረጃ ነው፤ የኢትዮጵያ መከላከያ አንዳችም የአፀፋ እርምጃ አልወሰደም፤ያደረገውም ነገር የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ አንድ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት ፥ አሁንም የተያዘው መሬት በሱዳን እጅ እንዳለ ገልፀዋል። "እስካሁን መፍትሄ ሳይገኝ ክረምት ገብቷል፤ ለማረስም አይታሰብም፤ ተስፋ ቆርጠን ያለን የሌለን ንብረት አጥተን ነው ቁጭ ብለን ያለነው" ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/BBC-05-08

@tikvahethiopia
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።

ዋቸሞ ዩንቨርስቲ በሆሳዕና እና በዱራሜ ካምፓሶች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 398 ተማሪዎች በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ እያስመረቀ ነው።

ዛሬ እየተመረቁ ካሉ ተማሪዎች ውስጥ 23ቱ በሁለተኛ እና ቀሪዎቹ በአንደኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ ተከታታይ መርሀ ግብር ፦ በማህበራዊ ሳይንስ ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በግብርና ዘርፎች ነው የሰለጠኑት።

እንደ ኢዜአ መረጃ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የፀጥታ ኃይሎች ምረቃ :

* ፌዴራል ፖሊስ !

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ ምልምል የፖሊስ አባላት አስመርቋል።

በጦላይ ወታደራዊ ማስልጠኛ ማዕከል ሰልጥነው በዛሬ እለት ለምርቃት የበቁት 6 ሺህ 431 ምልምል ፖሊሶች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል 792ቱ የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ታውቋል።

* የአማራ ክልል ፖሊስ !

የአማራ ክልል ፖሊስ ያሰለጠናቸውን የልዩ ኀይል አባላትን፣ 5ኛ ዙር የመካከለኛ አመራር ኮርስ እና የወንጀል ክትትል ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ደብረ ማርቆስ በሚገኘው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ አስመርቋል።

በምረቃው አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የፀጥታ አመራሮች ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፌልትንማን ከኤርትራ ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ። በጁፍሪ ፌልትማን የሚመራው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ኤርትራ አስመራ ገብቷል። የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ልዑኩን በደንደን የእንግዳ መቀበያ ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን እንዳስረዱ የኢንፎርሜሽን…
#Update

ፌልትማን ከሌተናንት ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር በካርቱም ተወያዩ።

የአሜሪካ መልዕክተኛው ፊልትማን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ታዛቢነት የሚካሔደው የህዳሴ ግድብ ድርድር መቀጠል እንዳለበት በአፅንዖት ገልጸዋል፡፡

አል-ቡርሃን በበኩላቸው የዓባይ ውሃ ምንጭ በሆነችው ኢትዮጵያ እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች መካከል ያለው ልዩነት በድርድር መፈታት እንዳለበት ሱዳን እንደምታምን ገልጸዋል፡፡

የአልቡርሃን ንግግር ሀገራቸው ወደ አፍሪካ ሕብረት መራሹ ድርድር ልትመለስ እንደምትችል አመላካች ነው፡፡

በሦስቱ ሀገራት መካከል ትብብር እንደሚያስፈልግም ነው አል ቡርሃን የተናገሩት፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት እና የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ፌሊክስ አንቶይን ቺሲኬዲ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ሱዳን ገብተዋል ፡፡

ፕሬዝደንቱ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሉዓላዊነት ሌተናንት ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል ፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ ኢትዮጵያ ላይ ይወድቅ ይሆን ? ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል።

5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት አስታውቋል።

ኢንስትቲዩቱ እንዳስታወቀው በመሬት ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅበት ጊዜ 90 ደቂቃ ሲሆን ፍጥነቱም በስዓት 28 ሺህ ኪ.ሜ ይደርሳል ነው ያለው።

እንቅስቃሴው መደበኛ ያልሆነ ሲሆን ከፍታው ከምድር ዝቅ ሲል እስከ 170 ኪ.ሜ. ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 370 ኪ.ሜ. ይደርሳል ተብሏል።

ሎንግ ማርች ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል ?

በኢትዮጵያ ላይ ስብርባሪው የማረፍ እድል አለው የለውም የሚለውን እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው ሮኬቱ መሽከርከሩን አቁሞ ወደ ከባቢ አየር መግባት እና ወደ መሬት መምዘግዘግ ከጀመረበት ቅጽበት አንስቶ ነው፡፡

ከዚህ ጊዜ እንስቶ ስብርባሪው ወደ መሬት ለመድረስ የሰዓታት ጊዜ ስለሚኖረው ቦታው እንደታወቀ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል።

ባሉበት አካባቢ ስብርባሪው እንደሚደርስ ከታወቁ በእግርም ሆነ በተሽከርካሪ የሚደረግ እንቅስቃሴን መገደብ፤ ጠንካራ ከለሳ ወይም የላይ ሽፋን ባለው ስፍራ ስር መሆን፣ ድንገት ስራ ላይ ከሆኑ ሔልሜት ማድረግ እና የመሳሰሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ ይገባል ሲል ነው ኢንስትቲዩቱ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ https://telegra.ph/Fana-Broadcasting-Corporate-05-08

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጠ !

ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ ከፍተኛ አቤቱታ የቀረበበት በሶማሌ ክልል እየተከናወነ ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

በሂደቱ ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቲታዎችን አውርበዋል።

ቅሬታ ያቀረቡት ኦብነግ፣ ነጻነት እና እኩልነት፣ ኢዜማ እና የግል እጩ ተወዳዳሪ፣ ሲሆኑ ህጋዊ ያልሆነ የምዝገባ ሂደትን የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲታዩ ነበር።

ቦርዱ በሚዲያ ሞኒተሪንግ ክፍሉ ተሰበስቦ ቀርቦለት ምስሎቹን እና ቪዲዮዎች መመልከቱን ገልጿል።

ቦርዱ ያሉትን ሁኔታዎች በመመርመር በሱማሌ ክልል የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት ምዝገባ እንዲቆም ወስኗል።

* የምርጫ ቦርድ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ምን ያህል መራጮች ተመዘገቡ ?

እስከሚያዚያ 29/2013 ዓ.ም ድረስ 31,724,947 መራጮች በ43,017 የምርጫ ጣቢያዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

• ኦሮሚያ - 14,301,855
• አማራ - 5,205,011
• ሶማሌ - 3,844,129
• ደቡብ - 3,496,892
• አፋር - 1,712,991
• ሲዳማ - 1,329,490
• አዲስ አበባ - 1,212,073
• ጋምቤላ - 272,810
• ድሬዳዋ - 177,519
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 155,913
• ሐረሪ - 16,264

እስካሁን ባለው ከተመዝጋቢዎቹ መካከል 54% ወንዶች ሲሆኑ 46 % ሴቶች ናቸው።

ምንጭ ፦ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት መገለጫ ሲዳሰስ !

[በጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ/DW]

የመግለጫው ዋነኛ ጉዳዮች የነበሩት፦

- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር
- የሱዳን ወረራ እና ያልተገባ ጫና
- 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ

የታላቁ የህዳሴ ግድብን ግንባታ በተመለከተ ግብፅ በውሃ ላይ ምንም አበርክቶ ሳይኖራት እያሳደረች ያለው ጫና ተገቢነት እንደሌለው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አሁንም ድርድሩን በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ማስቀጠል እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

አምባሳደር ዲና የሁለተኛው ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ግብፅና ሱዳን በሙሌቱ ላይ ስምምነት ካልደረሱ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁ አምባሳደሩ ተከታዩን ምላሽ ነው የሰጡት፦

"በ3ቱ ሀገሮች በ2015 በሱዳን ካርቱም በተፈራረሙት የመርሆች መግለጫ መሰረት የግድቡ ሙሌት የግድቡ የስራ ሂደት አካል ነው። ስለዚህ የውሃ ሙሌቱ የግድቡ አካል ነው። ግድብ ከገነባህ ውሃ መሙላትህ እርግጥ ነው፤ ያ ነው ሊሆን የሚችለው ፤ በመጀመሪያው ዙር የግድቡ ሙሌት የሆነውም ይኸው ነው። አሁንም ተስፋ የምናደርገው በአሞላሉ እና በሂደቱ ላይ እንደምንስማማ ነው።"

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብን አስመልክቶ ሱዳን ከሰሞኑ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ላይ የባለቤትነት ጥያቄን ማንሳቷን አውግዘዋል።

በተለይ የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ አስፈፃሚነት ውስጥ መግባቱን አሳይቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩ አሁንም #በሰላም እንዲፈታ ግፊት ማድረጓን ቀጥላለች ብለዋል።

ምርጫ 2013 በተመለከተ አምባሳደር ዲና ፥ ከትላንት ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መስማማቱን አሳውቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/MFA-Ethiopia-05-08

@tikvahethiopia
'ከሟቾቹ መካከል 14ቱ ከኦሮሚያ ክልል ናቸው'

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ31 ዜጎቿ ህይወት በኮቪድ-19 ያለፈ ሲሆን ከሟቾች ውስጥ 14ቱ ከኦሮሚያ ሪፖርት የተደረጉ መሆኑን ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦ ባለፉት 24 ሰዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው 5,393 የላብራቶሪ ምርመራ 637 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 262,217 አድርሶታል።

ትላንት 1,444 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 208,314 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 50 ሺህ 030 ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ፤ 749 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮቪድ-19 ክትባትን በተመለከት ፦ ክትባት የወሰዱ ዜጎች 1,290,828 መድረሳቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
'የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን ተከታተሉ'

ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትላትን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity እንዳሳወቀው የዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች በምን መልኩ በምርጫ ይሳተፉ ? በሚለው ላይ እስካሁን በሚኒስቴሩ ደረጃ ምንም የተወሰነ ውሳኔ የለም።

ነገር ግን የተለያዩ ኒቨርሲቲዎች በውስጥ ማስታወቂያ ከምርጫው በፊት 1 ሳምንት ከምርጫው በኃላ 1 ሳምንት ተማሪዎቻቸውን እንደሚበቱ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ሌሎች ደግሞ በውስጥ ማስታወቂያቸው "ከምርጫው በፊት ተማሪዎች ይበተናሉ" ስለሚባለው ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደለ እንዲሁም የሚናፈሰው መረጃም ውሸት እንደሆነ በመግለፅ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያሳበቡ ይገኛሉ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆናችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ተማሪዎች በምን መልኩ ነው በምርጫው የሚሳተፉት ? ለሚለው ጉዳይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ መረጃ ሲላክልን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

እስከዚያው ግን በተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች ላይ ሆነ የፌስቡክ ገፆች ላይ የሚወጡትን የተለያዩ መረጃዎች በመቀባበል ሳትረበሹ #በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን እየቀጠላችሁ ይፋዊ የሆነውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ትጠብቁ ዘንድ አደራ እንላለን።

አዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመዳቢ ተማሪዎች በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት በጠየቅ እናሳውቃለን። በተጨማሪም የ2013 ሀገር አቀፍ ፈተና ሂደትን ከትምህርት ሚኒስቴር ጠይቀን እናሳውቃለን።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሉበርካታ የተጣረሱ መረጃዎች እንዳትደናገሩ።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity