TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmnestyInternational

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለወራት በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ (በኤርትራና የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች) የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን የዳሰሰበትን የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።

አምነስቲ ከተለያዩ የጤና ተቋማት በሰበሰበው መረጃ መሠረት ከየካቲት እስከ ሚያዚያ ባሉት ወራት ብቻ በጦርነቱ አውድ ውስጥ ብቻ 1288 የሚሆኑ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች የተፈጸመባቸው ተጠቂዎች ወደ ህክምና መስጫ ተቋማት ሄደው ሪፖርት ማድረጋቸውን አመላክቷል።

ለጥናቱ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው 68 የጥቃቱ ሰለባዎች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ጤና ተቋም አለመሄዳቸውን በመጥቀስ ወደ ሕክምና ተቋማት የሄዱ ሰዎች ቁጥር የጥቃቱን ስፋት አያሳይ ሲል አምነስቲ ጠቅሷል።

አምነስቲ ካነጋገራቸው 68 የጥቃቱ ሰለባዎች ውስጥ ብዙሃኑ ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች ተገደው ተደፍረዋል።

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ነፍሰጡርና ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆኑ የተወሰኑት በልጆቻቸው ፊት ተገደው የተደፈሩ መሆናቸውን ሪፖርቱ በዝርዝር አስነብቧል።

አምነስቲ ካነጋገራቸው 68 ሰዎች መካከል 38ቱ ናቸው በቡድን የተደፈሩት።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ያደረገውን ሪፖርት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ አምነስቲ ተፈጽመዋል ስለተባሉ ጾታዊ ጥቃቶች ያወጣው ሪፖርት ተዓማኒነት የለውም ብሎታል።

የአምነስቲ መረጃ አሰባሰብ ዘዴ ተዓማኒነት የሌለው እና ሱዳን በሚገኙ ስደተኛ መጠለያዎች እና ትግራይ ካሉ ሰዎች በርቀት በስልክ ብቻ በተደረጉ ቃለ ምልልሶች ላይ ብቻ የተመሠረተ ሪፖርት ነው ብሏል።

አምነስቲ የኢትዮጵያ መንግሥትን ስም ለማጥፋት ሐሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል በማለትም ሚንስቴሩ ከሷል።

@tikvahethiopia