TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

ዛሬ ጥር 11/2013 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ለሚዲያዎች ባሰራጨው መግለጫ : በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እየቀረበ ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የሕክም አቅርቦቶችን የያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ደርሷል ብሏል።

አክሎም በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።

* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ከተራ እና ጥምቀት በሰላም ተከብሯል" - አማራ ክልል ፖሊስ

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መከበሩን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ2013 ዓ.ም ጥምቀት በዓል በትግራይ ማይጨው ከተማ ተከብሯል።

በዓሉ የእምነት አባቶች ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት ነው የተከበረው።

በሌላ በኩል በትግራይ መዲና በመቐለ ቅድስት ማርያም (ማርያም ጉግሳ)፣ በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የ2013 ጥምቀት በዓል ተከብሯል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 3,633 የኮሮና ቫይረስ ላብራቶሪ ምርመራ 181 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት የአራት ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 57 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን 131,727 ሰዎች ኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፥ ከነዚህ መካከል 2,037 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ፥ 116,392 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopia
"...በርካታ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እና ድጋፍ ይሻሉ" - ሚስተር ክሪስ ሚለር (UNHCR)

በአ/አ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ የውጭ ግንኙነት ኦፊሰር ሚስተር ክሪስ ሚለር በትግራይ ክልል እጅግ በርካታ ሰዎች ላለፉት 10 እና 11 ሳምንታት ያለምግብ እና ንፁህ መጠጥ ውሃ ቆይተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይም በትግራይ ሰሜናዊ ክፍል ሁለት ጣቢያዎች እንዲሁም በደቡባዊ ትግራይ ክፍል 2 ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በመንግስት ፍቃድ በደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ጣቢያዎች ከተወሰነ ሳምንት በፊት እርዳታ ማቅረብ ቢችሉም በሰሜናዊው ክፍል ግን እስካሁን ድረስ ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሶ ምንም አይነት እርዳታ ማድረስ አልተቻለም።

በዚህም ሳቢያ በርካታ ሺዎች ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል።

ሚስተር ክሪስ ፥ "መንግስት በትግራይ ክልል ውጊያው ማብቃቱን ቢገልፅም ነገር ግን የሰብዓዊ ቀውሱ አደጋ አሁንም አለ ፤ በርካታ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ይሻሉ ፣ በሰሜን በኩል በሚገኙ ሁለት ጣቢያዎች ችግር አለ፤ መግቢያም የለም። ማንኛውም አይነት አገልግሎት / አቅርቦት ማግኘት ከተቋረጠ 10 ሳምታት ተቆጥሯል" ብለዋል።

ቀጣዩን ያንብቡ :https://telegra.ph/UNHCR-01-19

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...ረሃብ የሚለው ቃል ኢትዮጵያ ውስጥ 77 ላይ አክትሟል" - አቶ ደበበ ዘውዴ

የተመድ የዓለም ምግብ መርሃግብር እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል ብለዋል።

የውጭ ሀገር ሚዲያዎች የዓለም ምግብ ድርጅትና የውጭ እርዳታ ድርጅቶችን ጠቅሰው በትግራይ ክልል የረሃብ አደጋው በህፃናት ላይ የጠና ነው ሲሉ አስነብበዋል።

በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ደበበ ዘውዴ ፥ "የምግብ እህሎች በትግራይ ሆነ በቤኒሻንጉል አካባቢ ለተፈናቃዮች እየደረሰ በመሆኑ በአሁን ሰዓት 'ረሃብ' እየተባለ የሚነገረውም ሆነ ተርቧል የሚባል ሰው የለም" ብለዋል።

ከማንም በላይና በፊት በኢትዮጵያ ላለ ሰው ሰራሽ እንዲሁም የተፈጥሮአዊ አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት ነው ለዜጎቹ የሚጨነቅ ሲሉም ተናግረዋል።

ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ከፍተኛ የድርቅ አደጋዎች እንዲሁም ሰው ሰራሻ አደጋዎች ሲደርሱ ነበር ከማንም ቀድሞ የደረሰው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብለዋል።

መንግስት ያለውን ችግር የሚደብቅበት ነገር እንደሌለው እና ለችግሮች በአስቸኳይ እንደሚደርስ ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት በትግራይ ክልል 485 ሺህ ተፈናቃዮች አሉ ያሉ ሲሆን የምግብ እርዳታ መንግስት በየወሩ እያቀረበ መሆኑን ተግረዋል።

ጥር 3/2013 ላይም ስንዴ፣የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት፣ፓስታ፣ሩዝ፣ መኮሮሪ በድምሩ 80,480 ኩንታል ድጋፍ መላኩን ገልፀዋል።

በተጨማሪ ህፃናት እና አጥቢ እናቶች ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ በማሰብ 438 ካርቶን የዱቄት ወተት፣ 214 ካርቶን ብስኩት ልከናል ብለዋል።

ቀጣዩን ያንብቡ : https://telegra.ph/DW-01-19-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባይደን በዓለ ሲመት ...

ዛሬ ረቡዕ በዋሽንግቶን ዲሲ የአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ይከናወናል።

ሥነ ሥርዓቱ የሚከወነው በቅርቡ በአሜሪካ ም/ቤት ህንጻ ላይ በተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የተፈጸመው የአመጽ ጥቃት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

አሜሪካውያን ከዚህም ለባሰው ነገር ሁሉ የተዘጋጁ ቢሆንም አንድነታቸውን ለመጠበቅ ተስፋ አድርገዋል፡፡ በጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ይህ እምነት በዋናነት እንደሚንጸባርቅም ተነግሯል፡፡

በአገሪቱ እጅግ አስፈላጊ ለሆነውና በየአራት ዓመቱ አንዴ ለሚደረገው የወግ ሥነ ሥርዓት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ተዘጋጅቷል፡፡

ዋሽንግተን ከእርስ በርሱ ጦርነት ወዲህ እንዲህ ዓይነቱን የሠራዊት ብዛት አይታ አታውቅም፡፡

ባለፈው ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህ መካከል የመጭው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት፣ “የተባበረች አሜሪካን” መፍጠር ዋነኛ ግቡ ማድረጉ ቀላል ይሆንለት ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡

ከፖሊስ በተጨማሪ እስከ 25 ሺ የሚደርሱ የብሄራዊ ዘብ ወታደሮች ለጥበቃው ተጠርተዋል፡፡ ~ ቪኦኤ

@tikvahethiopia @tikvahethioiaBOT
የዶናልድ ትራምፕ የስንብት ንግግር ...

(ቢቢሲ - BBC የቀረበ)

ከ12 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ተብለው የሚጠሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው የስንብት ንግግር አድረዋል።

ይህ ንግግራቸው የተሰራጨው በዩትዩብ ነው።

"ለማድረግ ያሰብነውን አድርገናል፣ ከዚያም በላይ ነው ያሳካነው" ብለዋል ትራምፕ በንግግራቸው።

"ከባዱን አውደ ውጊያ ላይ ነበር የተሳተፍኩት፣ ከባድ ፍልሚያ ነው ያደረኩት፤ ምክንያቱም የመረጣችሁኝ ያን እንዳደርግ ስለነበረ" ብለዋል ትራምፕ።

ትራምፕ በዚህ ንግግራቸው በጆ ባይደን መሸነፋቸውን ሙሉ በሙሉ አልተቀበሉትም።

ዶናልድ ትራምፕ በስንብት ንግግራቸው ፥ "በአሜሪካ ታሪክ እጅግ አይበገሬውን ምጣኔ ሀብታዊ ስኬት አስመዝግበናል፤ ይህም በዓለም አንደኛና ትልቁ ነው" ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት የስንብት ንግግር በሚቀጥለው ሕይወታቸው ምን እንደሚያደርጉ ፍንጭ አልሰጡም።

ትራምፕ ፥ "ደጋፊዎቼ ብዙ ናቸው ፤ እኔ ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነኝ" ሲሉ በተደጋጋሚ ቢናገሩም በዚህ ወቅት በአሜሪካ ያላቸው ይሁንታና ተሰሚነት ምጣኔ አሽቆልቁሎ 34 ፐርሰንት መድረሱ ተዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ረቡዕ ማምሻውን (በምሥራቅ አፍሪካ አቆጣጠር)፣ ቀትር ላይ (በምሥራቃዊ አሜሪካ አቆጣጠር) ከዋይት ሐውስ ይወጣሉ። ጆ ባይደን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ትራምፕ አይገኙም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
👍2
#GambelaPoliceCommission

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በ 'ኢታንግ ልዩ ወረዳ: ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ በቀጥጥር ስር ማዋሉ ገለፀ።

ግለሰቡ በቀጥጥር ስር የዋለው ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠረፍ ከሚገኘው ዋንተዋር ወረዳን አቋርጦ ወደ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ጦር መሳሪያዎችን በሸክም ለማስገባት ሲሞክር ነው።

የጦር መሳሪያዎቹ አምስት ታጣፊ እና ሁለት ባለሰደፍ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች መሆናቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በተጠርጣሪነት ተይዞ ተጨማሪ የማጣራት ሥራው እንደተጠናቀቀ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ይላካል ብላል ኮሚሽኑ።

* የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ 352 የክላሽንኮቭ ጠብንጃዎች እና ከ1 ሺህ 870 በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር አውሏል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
''የምርጫ ምልክት''

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገራዊ ምርጫን ለማከናወን ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከጥር 13-24 ድረስ የምርጫ ምልክት ማስገቢያ እና መወሰኛ ሆኖ ተቀምጧል።

በዚህ መሰረት ህጋዊ ምዝገባቸውን ያጠናቀቁ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዲያስመዘግቡ አስታውሷል።

ቦርዱ ለዘንድሮ ምርጫ ለምርጫ ምልክትነት ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ምልክቶችን ያዘጋጀ ሲሆን የፓርቲ ተወካዮች ከተዘጋጁት ምልክቶች ሊወክለኝ ይችላል የሚሉትን መርጠው እንዲያስመዘግቡ ይደረጋል።

በቦርዱ ከተዘጋጀው ምልክት ውስጥ የሚፈልጉትን ምልክት ያላገኙ/ወይም የራሳቸውን ምልክት ማስመዝገብ የሚፈልጉ ፓርቲዎች መስፈርቱን በማሟላት ማቅረብና ማስመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የምርጫ ምልክት መረጣው የሚከናወነው ከጥር 13- 18 ሲሆን ቦርዱ ከ18-24 ባለው ጊዜ ውስጥ የማጣራት እና የመወሰን ተግባራትን የሚያከናውንበት ሆኖ ተቀምጧል።

ይህ የምርጫ ምልክት መረጣ የግል እጩዎችን የማያካትት ሲሆን፣ የግል እጩዎች ምልክታቸው የሚመርጡበት መንገድ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

PHOTO: TIKVAH ETHIOPIA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT