TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DonaldTrump

የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድረጊት ጋር በተያያዘ ፣ የአሜሪካ ም/ቤት ፕሬዝዳንቱ በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ፣ ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ያልቻለ ፕሬዝዳንንት ከስልጣኑ ተነስቶ ምክትሉ መሪነቱን እንዲረከብ የሚደነግገውን 25ኛውን ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን በኢምፒችመንት ከስልጣን ለማውረድ ዝግጅት ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የሚካሄድባቸው መሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ትራምፕ ከኋይት ሀውስ ለመውጣት የቀራቸው 1 ሳምንት ቢሆንም ፣ ፕሬዝዳንቱ በኢምፒችመንት እንዲነሱ ባለቀ ሰዓት ሩጫ መጀመሩ ፣ በዋነኛነት ከዚህ በኋላ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይቀርቡ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ (አል ዓይን)

@tikvahethiopiaBOT
አዲስ አበባ ስታዲየም ሊታደስ ነው።

የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት  መፈረሙን አስታወቀ።

ስምምነቱ የተፈረመው የዲዛይን ፣ የማማከርና የቁጥጥር አገልግሎቱን ከሚያከናውነው ዮናስ አባይ አማካሪ አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ ከተባለ ድርጅት ጋር ነው።

የዲዛይን ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ እንደሚያቀርብ ኮሚሽኑ ገልጿል።

የዲዛይን ስራው የካፍ ስታንዳርድን ጠብቆ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBO
ትራምፕ ከዩትዩብ ለ7 ቀን ታገዱ።

ዩቲዩብ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የድርጅቱን ደንብ ጥሰዋል በሚል አግዷቸዋል።

በጉግል የሚተዳደረው ዩቲዩብ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዳዲስ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዳይለጥፉ ወይንም ደግሞ በቀጥታ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዳያጋሩ ለሰባት ቀን ያህል ማገዱን ያስታወቀ ሲሆን፤ እግዱ ከዚህም ረዘም ያለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።

ኩባንያው የዶናልድ ትራምፕን ገጽ፣ የድርጅቱን አመጽን አለማነሳሳት የሚለውን ደንብ ጥሷል ሲል ተናግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ማክሰኞ ማታ በርካታ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያጋሩ ሲሆን የተወሰኑት አሁንም በሰሌዳቸው ላይ ይገኛሉ።

ዩትዩብ ባገዳቸው የዶናልድ ትራምፕ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ውስጥ ምን እንዳሉ የጠቀሰው ነገር የለም።

ይህ ውሳኔ የተሰማው የተለያዩ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዝዳንቱ ከዩቲዩብ እንዲታገዱ የሚጠይቅ ማስታወቂያ ለመልቀቅ ከዛቱ በኋላ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የሱዳን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ።

አንድ የሱዳን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በ 'ጋዳሬፍ ግዛት' ከሚገኘው ዋድ ዛይድ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ ወዲያውኑ ተከስክሶ በእሳት መያያዙን የሱዳን ዜና ወኪልን (ሱና) ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሦስት (3) ግለሰቦች ተርፈዋል።

ሄሊኮፕተሩ በምን ምክንያት ሊከሰከስ እንደቻለ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrLiaTadesse

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራ አለም አቀፍ የንቅናቄ ቡድን ውስጥ በአስተባባሪነት መመረጣቸውን MoH ገለፀ።

የንቅናቄ ቡድኑ በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና የክትባት ትብብር የሚመራ ሲሆን የኮሮናቫረስ ክትባት ለሁሉም ሀገራት በፍትሀዊነት ተደራሽ እንዲሆን የሚሰራ ነው፡፡

በቡድኑ አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ እና የካናዳ የአለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጉልድ ናቸው፡፡

ቡድኑ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የአለማችን ሀገራት ተደራሽ እንደሚሆን ነው ያስታውቀው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘዉዴ የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ።

ፕሬዚዳንቷ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ሰባት የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም ፦

- ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ ቦንሳ

- ጄኔራል አደም ሞሐመድ

- አቶ ሌንጮ አየለ ባቲ

- አቶ ሀደራ አበራ አድማሱ

- አቶ ነቢል ማሀዲ አብዱላሂ እና

- አቶ መላኩ ለገሰ አድማሱን በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሰጥተዋል።

እንዲሁም አቶ እሸቴ ወልደየስን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል። ~ ENA

@tikvahethiopia
ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ተገደሉ።

መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎችም የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳውቋል።

አመራሮቹ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ ተደብቀው እንደነበር እና ከነ ጠባቂዎቻቸው እና ከወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር እንደተደመሰሱ ሀገር መከላከያ ገልጿል።

የተደመሰሱት አመራሮች ፦

1. አቶ ስዩም መስፍን - የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ - የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ - የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ - ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊ እንዲሁም የክልል አመራሮች ፦

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን - ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ - ከመከላከያ የከዱ፤
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ - ከመከላከያ የከዱ፤
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም - የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበሩ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ - የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ~ ኢዜአ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FireAlert

በጦራ ከተማ በተለምዶ "ኑርቴ ነዳጅ" አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ መነሳቱን የከተማዋ ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

እስካሁን ባለው ሂደት እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለና የወራቤ ከተማ እሳት ማጥፊያ መኪና ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱ ታውቋል።

መሰል አደጋዎች በሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

ዝርዝር መረጃ አሰባስበን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tora

በጦራ ከተማ ከንግድ ባንክ በስተደቡብ ኑርቴ ነዳጅ ቤት አካባቢ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋው መንሰኤ ምን እንደሆነ ለግዜው አልታወቀም።

Via Tora Town PR
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ጦራ ከተማ 'ኑርቴ ነዳጅ ቤት' አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደገ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ሙሉበሙ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም።

በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የከተማው ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#MekaneSellam

ዛሬ ከቀኑ 10:00 አካባቢ በደቡብ ወሎ ዞን በመካነ ሠላም ከተማ ድንገት የተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

አደጋው በተለምዶ 'ቦለቄ ሰፈር' እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው የደረሰው።

በጫማ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

አደጋው በህብረተሰቡ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት የአደጋው መንስኤ "ኤሌክትሪክ" መሆኑን ገልጿል ፤ አጠቃላይ የጉዳት መጠኑን እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በሀገራችን ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ወደ 130 ሺህ እየተጠጋ ነው።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፥ የባለፉት 24 ሰዓታት ሪፖርት ይፋ ያደረጉ ሲሆን ፥ ከተደረገው 4,919 ምርመራ 463 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል።

ይህም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎችን ቁጥር 129,455 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ሰዎች ሲሞቱ፥ 305 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ የኮሮና ሟቾች ቁጥር 2,006 ፤ ያገገሙ 114,567 ደርሰዋል።

ዛሬ MoH ወረርሽኙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አሳውቋል።

ከኮሮና ወረርሽኝ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ፤ የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያዎች እንዲሁም የፅኑ ሕሙማን ክፍል አልጋዎች በሙሉ በታማሚዎች ተይዘው ሌሎች ታካሚዎች ለወረፋ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት ከቀድሞ በምን ያህል ልዩነት ይተላለፋል ?

በክትባቱ ላይስ የሚያሳድረው ጫናስ ምን ይመስላል ?

(በዶክተር ያቤፅ ከበደ)

ደቡባዊ ኢንግላንድ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው አዲሱ SARS-CoV-2 ተለዋጭ ዝርያ ከመጀመሪያው ጫና ጋር ሲነፃፀር በ ‹R0› የመባዛት ቁጥር ተብሎ የሚታወቀው ከ 0.4 ወደ 0.7 ነጥብ ከፍ ያለ የመተላለፍ አቅም አለው ሲሉ የእንግሊዝ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል ፡፡

አጥኚው ቡድን አዲሱ ከድሮው አይነት የመከሰት መጠን እንደጨመረ እና የድሮው አይነት ደግሞ የቀነሰባቸው ክልሎች ውስጥ “ትልቅ እና ስታትስቲካሊ ጉልህ መዛባት” እንደተገኘ ይህ ደግሞ የ R0(የብዜት ቁጥር) መጨመርን ያሳያል ፡፡ የR0 ልዩነቱ ከድሮው-ዓይነት ቫይረስ ከ40% -80% ከፍ ያለ ነው ብለው ገምተዋል ፡፡

በቅድሚያ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በመጀመሪያ የመነሻ ግምት ማስተላለፍ መጠን ቢያንስ ከ56% እና እስከ 70% ከፍ ሊል እንደሚችል ይገምታሉ ፡፡

የሲዲሲ ተመራማሪዎች ለጋዜጠኞች እንደገለጹት እንደ "ኮንቫልሰንት ፕላዝማ" (ካገገሙ ሰዎች ተወድዶ ለታማሚ የሚሰጥ) ያሉ አንዳንድ ሕክምናዎች ላይ እንጂ በ COVID-19 ክትባት ውጤታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር አይመስልም ብለዋል፡፡

More : https://telegra.ph/DrYabetse-01-09

@tikvahethiopiaBot
የህክምና ተማሪው የቴክኖሎጂ አሰልጣኝ !

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪ ነው። በቅርቡ አስራ ዘጠኝ (19) ወጣቶችን 'ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ' ላይ ያተኮረ ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በራሱ ጥረት በውጭ ከሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመነጋገር በአከባቢው (አሰላ) የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ (STEM) ማዕከል አቋቁሟል።

ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት መለያ ማሽን፤ የደን ውስጥ ቃጠሎ ማሳወቂያ እና መቆጣጠሪያ፤ የግቢ መብራቶችን በመጠቀም የጸጥታን ሁኔታ መቆጣጠር የሚያስችል እና በረካታ ሥራዎችን ሰርተዋል።

ከወጣት አልዓዛር አለማየሁ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገናል ያንብቡ : telegra.ph/የህክምና-ተማሪው-የቴክኖሎጂ-አሰልጣኝ-01-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia