TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* ሪፖርት

ከህዳር 5 እስከ ህዳር 9 #በማይካይድራ ፣ በዳንሻ ፣ በአብርሃጅራ ፣ በሳንጃ፣ በሁመራ እና በጎንደር ከተማ ተዘዋውሮ ምርመራ ማድረጉን ኢሰመኮ አሳውቋል።

ኢሰመኮ አደረኩት ባለው "ምርመራ" የሰደረሰበትን ግኝት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

* የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethioiaBOT
አጫጭር መረጃዎች ፦

- መንግሥት የተሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካት የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው ብሏል ፤ በህወኃት ተጽዕኖ እጅ ለመስጠት ያልቻሉ በያሉበት ትጥቅ ፈተው የህወሓት መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡና መከላከያ እስከሚደርስላቸው እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

- ዶ/ር ደብረፅዮን መቐለ በመከላከያ ቀለበት ውስጥ ነች/ተከባለች የሚለውን መረጃ እስካሁን እንዲህ ያለ ነገር የለም ሲሉ ለሮይተርስ በፅሁፍ መልዕክት አሳውቀዋል።

- UNHCR በትግራይ ክልል ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎች ከ40,000 ማለፋቸውን ገልጿል።

- በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የአላማጣ ከተማና ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአካባቢውን ሰላም ና ጸጥታ ያስከብራል፤ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ ያደርጋል ተብሏል። የራያ አላማጣን 15 የገጠር ቀበሌዎች እና የአላማጣ ከተማን 4 ቀበሌዎች በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ 114 ሰዎች ተመርጠው ስራ ጀምረዋል።

- የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት ትግራይ ዉስጥ ስለሚደረገዉ ዉጊያ ማምሻዉን ይነጋገራል። ይህ ቀጠሮ የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ በመንፈጋቸዉ ምክንያት ተሰርዞ ነበር። የአዉሮጳ ሀገራት ዉይይቱ እንዲደረግ ግፊት በማድረጋቸዉ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ይነጋገራል።

- በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የእስር ትእዛዝ ያወጣባቸው ሰዎች 167 ደርሰዋል። ከእነዚህ መካከል በቁጥጥር ሥር የዋሉ አሉ። በሌላ በኩል ከሀገር ውጪ ያሉ ተጠርጣሪዎችን ካሉበት ሀገር ተላልፈው እንዲሰጡ መንግሥት መጠየቁ ተገልጿል።

ህዳር 15/2013 ዓ/ም
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,091
• በበሽታው የተያዙ - 388
• ህይወታቸው ያለፈ - 10
• ከበሽታው ያገገሙ - 179

አጠቃላይ 106,591 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,661 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 66,018 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

334 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ/ም ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia

በህግ የሚፈለጉት የህወሓት አባላት በሰላማዊ ሁኔታ እጃቸውን እንዲሰጡ የተሰጠው የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል።

ይህንን ተከትሎም ዓለም አቀፍ የመብት ቡድኖች እና ተቋማት የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው እየተማፀኑ ነው።

ሁለቱም ኃይሎች ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠይቋል።

ወታደራዊ ባልሆኑ መሰረተ ልማቶች እና በሰላማዊ ሰዎች እና ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚቻለውን ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ሰላማዊ ህዝብ ከሚበዛባቸው ሰፈሮች የወታደራዊ ቁሳቁሶችን ክምችት እንዲያስወግዱ እንዲሁም የወታደሮች እንቅስቃሴ በሰላማዊ ነዋሪዎች መኖሪያ አካባቢ እንዳይሆን ጠይቋል።

በተጨማሪ ተዋጊዎች ሰላማዊ ዜጎችን ጋሻ ከማድረግ እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች አስፈላጊው ከለላ እና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጫጭር መረጃዎች ፦ - መንግሥት የተሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካት የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ ነው ብሏል ፤ በህወኃት ተጽዕኖ እጅ ለመስጠት ያልቻሉ በያሉበት ትጥቅ ፈተው የህወሓት መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡና መከላከያ እስከሚደርስላቸው እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል። - ዶ/ር ደብረፅዮን መቐለ በመከላከያ ቀለበት ውስጥ ነች/ተከባለች የሚለውን መረጃ…
#UPDATE

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለምክክር በZoom ተቀምጦ ነበር። ነገር ግን ስብሰባውን የአፍሪካ አገራት ባለመደገፋቸው #ያለመፍትሄ ተጥናቅቋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ የፈረንሳይ ፣ እንግሊዝ ፣ ቤልጂየም ፣ ጀርመን እና የኢስቶንያ ዲፕሎማቶች አሜሪካንን በመደገፍ ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን SBS ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት 'የውስጥ ጉዳይ' ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መንግስት የሰጠው የ72 ሰዓታት ጊዜ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ይገኛል።

የህወሓት አባላት ግን ይህንን ጥሪ አልተቀበሉትም ፤ ይልቁንም መንግስት ሽንፈት ስለደረሰበት ለመሸፋፈን የተጠቀመው ነው ብለውታል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ትላንት በሰጠው መግለጫ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትዕዛዝ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

መቐለ ከተማን የከበበው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ ለ3ኛውና ለመጨረሻው ምዕራፍ በተጠንቀቅ ቆሞ ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ተገልጿል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን በ50 ኪሎ ሜትር ውስጥ መክበቡ ተገልጿል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ትላንት ለሮይተርስ በፅሁፍ እንዳሉት "መቐለ ተከቧል የሚባለው እስካሁን እንዲህ ያለ ነገር የለም" ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በመቐለ ከተማ ይኖራል በተባለው ኦፕሬሽን ንፁሃን እንዳይጎዱ ወታደራዊ ያልሆኑ መሰረት ልማቶች እንዳይጠቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የተለያዩ ተቋማት እየተማፀኑ ነው።

ተመድ መንግስት ያስቀመጠው የ72 ሰዓት ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በመቐለ ሊከሰት የሚችለው ሁኔታ ከወዲሁ እንዳሳሰበው አሳውቋል ፤ ድርጅቱ "የጦር ወንጅል" እንዳይፈፀምም ስጋት እንዳለው ገልጿል።

ዶ/ር አብይ ከሁለት ቀን በፊት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ "በመቐለ የሚኖረው የህግ ማስከበር እርምጃችን ጉዳትን እጅግ በቀነሰ መልኩ መከናወን እንዳለበት እናምናለን፣ ስለዚህም መቐለ ከተማን ከከፋ ጉዳት ታድገን ዘመቻውን በድል የምናከናውንበትን መንገድ እንደምንከተል ለመግለፅ እወዳለሁ" ብለዋል።

ጠ/ሚሩ የመቐለ ነዋሪዎች ከሰራዊቱ ጎን በመቆም በህግ የሚፈለጉትን አካላት ለፍርድ በማቅረብ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል ፤ ለጥቂት ሰዎች ሲባል አንድም ሰው መሞት ፣ ንብረትም መውደም የለበትም ብለዋል።

(ቲክቫህ)
@tikvahethiopiaBOT