TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ የኬሚካል ርጭት ተጀምሯል ?

(በኤልያስ መሰረት)

EBC : "መንግሥት በደቡባዊ ትግራይ እና በምሥራቅ አማራ የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል እርጭት ማካሄድ ጀመረ"

የትግራይ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ : "ይህ ፍፁም ውሸት ነው ፤ ለምን እንደዛ እንደሚሉ አይገባኝም።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት !

አሮጌው 100 ብር ኖት ከአዲሱ 10 ብር ኖት ጋር በቀለም ተመሳሳይነት እያጭበረበሩ ያሉ አካላት ስለመኖራቸው ብሄራዊ ባንክ መረጃ እንዳለው ገልፆ ፣ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ በኖቶቹ ለውጥ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ግንዛቤ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል አዲሱን 100 ብር ኖት በአሮጌው 130 ብር ኖትና ከዚያ በላይ የሚሸጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን በመረጃ እንደተደረሰበት ብሄራዊ ባንክ ገልጿል ፤ ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

#ሼር #SHARE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች !

የጤና ሚኒስቴር ከጥቅምት 09-13/2013 የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

• የፈተናው ፕሮግራም
• ቦታ እና ሰዓት ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ማንኛዉም ተፈታኝ ወደ ፈተና ቦታ ሲመጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (mask) እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ይዞ መምጣት የሚኖርበት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከምዕራብ ሃረርጌ የቲክቫህ አባላት ፦

"ምዕራብ ሀረርጌ ፤ ጭሮ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በከፍተኛ ሁኔታ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ህዝቡ ርብርብ ቢያደርግም ምንም መቆጣጠር አልተቻለም።

የሚመለከታቸው አካላት መንጋው አሁን ካለው በላይ እጅግ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ እገዛ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19

ባለፈው ሳምንት ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር የተገናኙ 2 የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኮሮና ስጋት ራሳቸውን ማግለላቸውን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ድረገፅ አስነበበ።

ባለስልጣናቱ ራሳቸውን ያገለሉት አብረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ የልዑካን ቡድን አባላት መካከል አንዱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

ከትናንት ጀምሮ ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለጹት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የጸጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል እና የህብረቱ የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ሌናርቺች ናቸው።

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መስከረም 28/2013 ዓ/ም ከጠ/ሚ አቢይ አህመድ ጋር የተገናኙት ባለስልጣናቱ ፤ በማግስቱ ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋርም ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠያና ቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያን እንዲሁም የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት ዝግጅት በተመለከተ ተቋማት የደርሱበትን ደረጃ ሊገመግም ነው።

በዚህ መድረክ ፦

• የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች
• የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚታ ሰብሳቢዎች
• የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
• በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ቁልፍ ሚኒ ያላቸው መንግስታዊ ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ።

ከጥቅምት 6 እስከ 8 በሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው መድረክ ላይ ፦

- ኮቪድ-19 በመከላከልና ሰላማዊ የመማር ማስተማርን በማረጋገጥ ላይ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ሚና ፤

- በኮቪድ-19 ወቅት ትምህርትና ስልጠና ለማቀጠል የሚወሰዱ ክልከላዎች እና እርምጃዎች ፤

እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና እንደገና ለማስጀመር ተቋማት የደረሱበትን ደረጃ በመገምገም ላይ የሚገኘው ግብረኃይል ሪፖርት መሰረት ወይይት ተደርጎ ውሳኔና ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በሰሜን ወሎ ዞን ከ18 ሺህ ሄክታር በላይ በጤፍ ፣ ማሽላና ማሾ የተሸፈነ ማሳ በአንበጣ መንጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙን ዞኑ ለetv አስታውቋል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በሰው ኃይልና በአውሮፕላን ርጭት እየተካሄደ ቢሆንም አንበጣው በብዛት በመፈልፈሉ እና በተደጋጋሚ በመከሠቱ ጉዳቱ እየከፋ መምጣቱን ዞኑ ገልጿል።

የአንበጣ መንጋው ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ህብረተሰቡ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ አርሶ አደሮችን እየደገፉ ነው።

በደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ34 ሺህ በላይ ዜጎች ለችግር እንደሚዳረጉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

- የመምህራን እጥረትን ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም /በፊት የማስተማር ልምድ ያላቸው እና አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

- ተመራቂዎች በመምህርነት ስራ የመቀጠል ፍላጎት ካላቸው በቀጣይ ቅጥር በሚካሄድበት ጊዜ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

- የመማር ማስተማር ሂደቱን በፈረቃ ለማስቀጠል የተያዘው እቅድ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡

- ጥሪ የተደረገላቸው መምህራን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ እንጂ ቅጥር የሚፈፅሙ አይደሉም።

- መደበኛ አስተማሪዎች ከዚህ ቀደም ከሚያስተምሩት ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ አምስት ክፍለ ጊዜ በበጎ ፈቃድ እንዲያስተምሩ የሚደረግ ይሆናል።

- የመማሪያ ክፍል እጥረትን ለማስወገድ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎችን፣ የቀበሌ ፅህፈት ቤቶችን እና የሃይማኖት ተቋማት አገልግሎሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ችሎት !

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት 4ቱ ተጠርጣሪዎች ፦

- ጥላሁን ያሚ፣
- ከበደ ገመቹ፣
- አብዲ አለማየሁ እንዲሁም ላምሮት ከማል እያንዳንዳቸው "ወንጀሉን አልፈጸምንም፤ ጥፋትም የለንም" በማለት ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ይህን ያሉት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕግ እና ጸረ ሽብር ችሎት ዛሬ ረቡዕ በቀረቡበት ወቅት ነው።

የተከሳሾች ጠበቃ ተከሳሾቹ የክስ መከላከያ እንደሌላቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ዐቃቤ ሕግ ፖሊስ መስክሮችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጠ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ግን ዐቃቤ ሕግ ራሱ መስክሮቹን ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ አዟል።

በዚሁ መሠረት ከኅዳር 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም ምስክሮቹን ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሰጥቷል።

Via BBC
@tikvahethiopiaBot
#ATTENTION📣

በምዕራብ ሀረርጌ ውስጥ ወጥ የሆነ ትልቅ የማሽላ ምርት የሚገኘው ከጉባ ቆርቻ ወረዳ ፣ ኦዳ አነኒ የሚባል ቀበሌ ነው።

ዘንድሮ ጥሩ ዝናብ አግኝተው ትልቅ ምርት ይጠብቁ ነበር ፤ ነገር ግን የአምበጣ መንጋ መጥቶ ወሮባቸዋል፤ ይኸው ሁኔታ እጅግ ሀዘን ውስጥ ከቷቸዋል።

የመንጋው እዛው ወረዳ ላይ የተለያዩ ቀበሌዎችንም ወሯል ፣ ኦዳ ዲማ ፣ እና ወደ ቆላማው ያሉትን ቀበሌዎች እጅጉን ጎድቷቸዋል።

በአጠቃላይ በወረዳው የሚገኙ አስራ አራት ቀበሌዎች እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የሚጮህላቸው አክቲቪስትም ሆነ ሚድያ ስለሌላቸው እጅጉን ችላ ተብለዋል። የሚመለከተው አካል ሁሉ አስፈላጊውን ማድረግ ይኖርበታል።

እዮብ ወንዱ
ጥቅምት 4/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ የኬሚካል ርጭት ተካሂዷል ?

በግብርና ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ ለማ ፦

"የአንበጣ መንጋውን ለመዋጋት ሚኒስቴሩ አውሮፕላኖችን ጨምሮ የአንበጣ መከላከያ መሳሪያዎችን ቢያዘጋጅም የትግራይ ክልል ግብርና ቢሮም ይሁን እስከ ወረዳ ያሉት መዋቅሮች የአንበጣውን መገኛ አሳውቆ እርጭት እንዲደረግ የፍቃደኝነት ችግር ስላለ እስካሁን ርጭት አልተካሄደም።

አሁንም ቢሆን ከክልሉ ወረዳዎች ጋር በስልክ እየተገናኘም ነው ፤ የአንበጣ መንጋው የተከሰተበትን ቦታ ለይተው የሚያሳወቁ ከሆነ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ማድረግ ይቻላል።

የገበሬዎች ምርት ከፖለቲካ የተለየ ነገር ነው ፤ ፋይዳውን አይተው ፤ ለሕብረተሰቡ አስበው መረጃውን የሚሰጡ ከሆነ የፌደራል መንግሥት የኬሚካል ርጭቱን ለማካሄድ ዝግጅቱም ሆነ ፍላጎቱ አለው።"

-

በትግራይ ክልል የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ የተምች መከላከልና ቁጥጥር፣ የዕፅዋት ኳራንታይን ዳይሬክተር አቶ መብራህቶም ገብረኪዳን ፦

"የግብርና ሚንስቴር በአውሮፕላን አማካኝነት የኬሚካል እርጭት ለማካሄድ እንደሚረዱን ገልጸውልናል።

አውሮፕላን እንዲልኩና የሚረጭበት አካባቢ እንድናሳውቃቸው በነገሩን መሠረት ስምምነት ላይ ደርሰናል፤ ቢሆንም ግን እምነት የለንም።

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከዚህ ቀደም በአውሮፕላን የኬሚካል እርጭት እናካሂዳለን ተብሎ ከግብርና ሚንስቴር እንድንዘጋጅ ተነግሮን ብንጠብቅም ዋጃ አጠገብ ድንበር ላይ ረጭተው ተምልሰዋል።

አውሮፕላን የትም ቦታ ኬሚካል አይረጭም። ለምሳሌ በመንደር ውስጥ ፣ ውሃ ላይ እንዲሁም ተራራማና ሸለቆ ውስጥ መርጨት የለበትም ወይም ለመርጨት አይመቸውም።

ግብር ሚኒስቴር ቢያግዘን ጥሩ ነው ካልሆነም በራሳችን እንሰራዋለን።" (BBC)

@tikvahethiopiaBOT
የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ጥሪ ፦

(በአብመድ)

ዛሬ በአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የበርሃ አንበጣ መንጋ የመከላከል እንቅስቃሴውን በቦታው በመገኘት ተከታትሏል።

ልዑኩ ከአርሶ አደሮች እና ባለሙያዎች ጋርም ተነጋግሯል።

ልዑኩ የበርሃ አንበጣ መንጋው የተከሰተባቸው የራያ ቆቦ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች 41 አዲስ ዓለም እና 06 መንደፈራ ተገኝቶ የመከላከል ሥራውን ምልከታ አካሂዷል፡፡

በቀበሌዎቹ አንበጣው በጤፍና ማሽላ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

አርሶ አደሮች ኅብረተሰቡን ያሳተፈ መከላከል ሥራ ቢጠናከር የተሻለ እንደሆነ የመፍትሔ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

የፀጥታ አካላት ፣ ተማሪዎች ፣ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶች እንዲሳተፉና የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ እንዲተባበሯቸው ማስተባበር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ👏

የአርሶ አደሩን ህይወት መታደግ የራስን ህይወት መታደግ ነው !

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ፣ ሰራተኞች ፣ መምህራን እንዲሁም የደብረ ብርሃን ወጣቶች ትላንት በቀወት ወረዳ የደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎችን በመሰብሰብ የአንበጣ መንጋ የሚያደርሰውን ጉዳት የመከላከል ሥራ አከናውነዋል።

የአርሶ አደሩ ህይወት አደጋ ላይ ነው ማለት የከተማው ነዋሪ የመኖር ህልውና አደጋ ላይ እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው ሲሉ የዘመቻው አስተባባሪ ዶ/ር ታምራት ቸሩ ተናግረዋል።

ዘመቻው በአጭር ጊዜ የታቀደ ቢሆንም ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። በቀጣይም ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖሊስ መወሰዱ ተሰማ !

ዛሬ 8:00 አካባቢ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ፖሊሶች ' ፍትህ መፅሄት ' የሚገኝበት ቢሮ በመገኘት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በወቅቱ ቢሮ ስላልነበር ካለበት በስልክ በመጥራት ይዘውት እንደሄዱ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በፍትሕ መጽሔት ላይ ' አባ ብላ ገመዳ ' በሚል ርዕስ በተጻፈ ጹሑፍ ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ለብሮድካስት ባለስልጣን የቅሬታ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጋዜጠኛ ተመስገን ታስሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገባ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል !

ታሪኩ ደሳለኝ ተከታዩን ብሏል ፦

"ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰሩን በር ላይ ያሉት ፖሊሶች ነግረውናል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቢሮ መወሰዱን እንደሰማን ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያመራን ሲሆን እዛ በር ላይ ያሉት ፖሊሶች ተመስገንና የመፅሔቱ አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤ ተይዘው መግባታቸውን ገልፀውልናል።

ከዚያ ውጪ ምንም ዓይነት መረጃን ያላገኘን ሲሆን ምናልባት ምግብና ልብስ ካመጣን ለማስገባት እንደሚተባበሩን ነግረውናል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia