TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው። የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት…
#Ethiopia

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ጸድቋል።

ስለ አዋጁ ...

➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ 

➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።

➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።

➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።

➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም  ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።

ስለ አዋጁ ምን ጥያቄ ተነሳ ?

አንድ የምክር ቤት አባል ፦

" የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉት በዓላት ለምን አልተካተተም ? ለምን ታስቦ ከሚውል ውስጥ ተካተተ ? ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች !! ታስቦ ይውላል እና ተከብሮ ይውላል የሚለው የተለያየ አጀንዳ አለው " የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር።

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበር እና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡

" ኢኮኖሚያችንስ ? " ሲሉ የጠየቁት ወ/ሮ ወርቀሰሙ " ሁል ጊዜ ስራ እየዘጋን ፤ በዓል እያከበርን መዋል በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ጫና አለ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ታስቦ የሚውል በተለያዩ ነገሮች ደምቆ የሚውል ሊሆን ይችላል በሚል ነው በታሳቢነት እንዲቀጥል የተደረገው " ሲሉ አስረድተዋል።

#ShegerFM #TikvahEthiopia #HoPR

@tikvahethiopia
#Sudan #Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በቀን የምትወስደው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋዋት ወደ 50 ሜጋዋት መውረዱን ገለጸ።

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትወስደው የኤሌክትሩክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱን ተነግሯል፡፡

ሱዳን #ጦርነት_ውስጥ_ከመግባቷ_በፊት ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን እስከ 200 ሜጋዋት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 50 ሜጋዋት እና ከዚያ በታች ሆኗል ሲል አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ለሱዳን የሚቀርበው ኃይል ከመውረዱም በላይ " ለተጠቀሙት የኤሌክትሪክ ኃይል እየከፈሉ አይደለም " ብሏል።

በታሰረው ውል መሰረት #ለተጠቀሙበት_ካልከፈሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ግንኙነቱ እንዳይሻክር ኢትዮጵያ ይህንን አላደረገችም ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ከጅቡቲ እና ከኬኒያ የኃይል ትስስር ያላት ሲሆን በቀን እስከ ሁለት ቴራ ዋት ሀወር ለሶስቱ ሀገራት ኃይል እንምድታቀርብ ተነግሯል።

ጅቡቲ የምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚሄድ ሲሆን ኬኒያም ከምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል 10 ከመቶ ከኢትዮጵያ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡

#ShegerFM

#Sudan #Ethiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ በ4 ተቃውሞ በ6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

አዋጁ ፤ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም ድረስ እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺ ሰዎችን እንደማያካትት ተሰምቷል።
 
ከምክር ቤት አባላት ምን ተጠየቀ ? ምን ምላሽ ተሰጠ ?

Q. ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ?
 
Q. ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል ?

Q. አንዳንድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም። ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ?


ሌላው ፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋት ተነስቷል።
 
በተ/ም/ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፥ ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ብለዋል።

አዲሱ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
በክልሎች ያለው በጀት ጉድለት እንዳለ ሆኖ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ እንደሆነ ተመላክቷል።

በክልሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያ ታሳቢ ይሆናል።
 
ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘም ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል ፤ " ውሳኔውን ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው " ብለዋል።

#ShegerFM
#HoPR
 
@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የቀበሌና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ  4,000 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር ካሳ እና 100 ሄክታር  ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ ፦

➡️ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣

➡️10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች

➡️ 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች  መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ  እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500  የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በ8 ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር  ቦታ ለማልማት ተቅዷል ብለዋል።

የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የትኞቹ ናቸው ?

1. ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት 1000 ሄክታር ቦታ ስፋት እና 40.4 ኪሎሜትር ርዝመት ፤

2. ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ የኮሪደር ልማት 128.7 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 7.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤

3. ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል የኮሪደር ልማት 146 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 10.8 ኪሎሜትር ርዝመት፤

4. ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት 565 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 15.9 ኪሎሜትር ርዝመት፤

5. አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ ኮሪደር ልማት 16.58 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 3.1 ኪሎሜትር ርዝመት

6. አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል የኮሪደር ልማት 314 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 13.19 ኪሎሜትር ርዝመት

7. የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት 372.5 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 20 ኪሎሜትር ርዝመት፤

8. እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት 274 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 21.5 ኪሎሜትር ርዝመት፤

በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል።

#AddisAbaba #ShegerFM

@tikvahethiopia