TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መስከረም 17/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ህንድ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1,124 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ ፤ 89,010 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 737 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ ፣ 43,206 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ብራዚል ውስጥ 732 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 25,536 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል ሜክሲኮ (405) ፣ አርጀንቲና (335) እንዲሁም ኢራን (172) ይገኙበታል።

- በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 998,745 ፤ በቫይረሱ የተያዙ 33,058,423 እንዲሁም ያገገሙ 24,409,745 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለኮቪድ-19 የሚሰጠው ትኩረት መቀነስ አሳሳቢ ነው!

(በዶክተር መክብብ ካሳ)

የዓለም ጤና ድርጅት እንደተነበየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል የሁለት ሚሊየን ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ይችላል፡፡

በሀገራችን የበሽታው አሳሳቢነት ጨመረ እንጂ አልቀነሰም፤ በየቀኑ የበርካታ ዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከተሉትን አራት መንገዶች ሀገራት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡

1. የቫይረሱን ስርጭት ሊያባብሱ የሚችሉ ኘሮግራሞችን መገደብ፡፡
2. በቀላሉ ሊጎዱ ለሚችሉ ዜጎች ትኩረት መስጠት፡፡
3. ማህበረሰብን ስለ ወረርሽኙ ማስተማርና ማንቃት፡፡
4. Test,Treat,Trace (መመርመር፣ የታመሙት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣ እና ንክኪ ያላቸውን መለየትና መመርመር ናቸው፡፡)

የሚደረገው ምርመራ መቀነስ ፣ ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች ለይቶ የመመርመር ስራ መቀነስ ፣ አርአያ መሆን የሚችሉ ታዋቂ ግለሰቦች የመንግስት እና የግል ተቋማት ተወካዮች የሚያሳዩት ቸልተኝነት እና የሚድያው መሰላቸት ተደማምሮ ወረርሽኙን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳንችል የብዙዎችንም ልፋት መና እንዲቀር ያደርጋል፡፡

ትንፋሽ አጥሯቸው የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን እናስባቸው ፤ የእኛ ቸልተኝነት ለራሳችንም ለሌሎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል ፤ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 75 የሕክምና ዶክተሮች ጨምሮ 1,732 ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይ በክብር እንግድነት ተገኝተው እንደነበር ከዩኒቨርሲቲው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,631
በበሽታው የተያዙ - 632
ህይወታቸው ያለፈ - 5
ከበሽታው ያገገሙ - 334

መስከረም 17/2013 ዓ/ም
(ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን አልፏል።

በመላው ዓለም በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ከተያዙት 33 ,212 ,069 ሰዎች መካከል የ 1, 000,588 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ጥንቃቄ አይለየን😷

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 18/2013 ዓ/ም

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ህንድ ውስጥ ተጨማሪ የ1,040 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 82,767 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ሜክሲኮ በ24 ሰዓት 399 ሰዎችን አጥታለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች 76,243 ደርሰዋል።

- ግሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ስደተኛ የኮቪድ-19 ሟች ተመዝግቧል፤ ሟቹ 61 ዓመት ወንድ ሲሆን ከማልካሳ የስደተኞች መጠለያ ነው ፤ ህይወቱ ያለፈው በአቴንስ ሆስፒታል እንደሆነ ተገልጿል።

- አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 1,467,555 ደርሷል፤ ከነዚህ ውስጥ የ35,215 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1,213,045 ሰዎች አገግሟል።

- የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በኬንያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመለሱበትን ቀን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስለል ?

#WolitaSodoUniversity

- ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ከንክኪ ዉጪ የሆነ የእጅ መታጠቢያ ተማሪዎች በብዛት በሚገኙበት አከባቢ ለማኖር ተዘጋጅቷል። የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዝር ፣ ሳሙና እና ዉኃ ተደራሽ የማድረግ ሥራም ይሰራል።

- የካፌ ዝግጅትን በተመለከተ ሁለቱም የተማሪዎች መመግቢያ አዳራሾች ጥገና እና በዘመናዊ ማሽን እየተተካ ነዉ፡፡

- ዶርምን በተመለከተ ካራኒታይን የሆኑ መኝታ ቤቶች የዲስ ኢንፌክት ስራ ከዛሬ ጅምሮ ይካሄዳል፡፡ የዶርምና አከባቢም ፅዳት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

- ከኮሮና ጋር በተያያዘ ጥግግትን ከመቀነስ አንፃር በአንድ ዶርም 3 ተማሪ የመመደብ ስራ ለመስራት ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

- አካዳሚክ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁሉም መምህራን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካዳሚክ ዘርፉም ልዩ ትኩርት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።

#AmboUniversity

- አምቦ ዩኒቨርሲቲው ካለው 4 ካምፓሶች አሁን ላይ የሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ (አዋሮ) በካሯንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

- አምቦ ዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ከጀመረ የቆየ ሲሆን ግቢዎችን ዲስኢንፌክት የማድረግ ሥራም ይሰራል ተብሏል፡፡

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለባቸው እና በቸልተኝነት ኃላፊነት በአግባቡ ባልተወጡ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ የክልሉ መንግስት ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጿል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው 45 አመራሮች ውስጥ አንድ የአመራር ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ከኃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ከመካከላቸው 10ሩ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ እና ምርመራ እንዲጣራባቸው ተደርጓል።

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከእስር ቤት ሊያመልጥ የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአንኮበር ወረዳ አንኮበር ፖሊስ ጣቢያ ሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተጣራበት የሚገኘው ደስታ አለሙ የተባለው ግለሰብ ከእስር ቤት ግድግዳ ፈርፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር ጥበቃ ላይ በነበሩ የፖሊስ ኦፊሰሮች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተጠርጣሪው በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3፡30 ላይ ድርጊቱን መፈፀሙንና በዚህ ላይም የምርመራ ፋይል ተከፍቶ መዝገቡ እየታየ መሆኑን የአንኮበር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Ankober Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገፁ የቦርዱ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ 40 ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተማሪዎች መገኘታቸው ተገለፀ!

በዚህም የተነሳ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሲጀመር በሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ራሳቸውን አግልለው ይቆያሉ ተብሏል።

#1

ዩኒቨርስቲ ኦፍ አብሪስቲዊዝ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት በሚል የገጽ ለገጽ ትምህርትን አስቀርቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ተማሪዎች ለገና እረፍት ወደ ቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

#2

ስኮትላንድ ውስጥ ተማሪዎች ለገና እረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የገጽ ለገጽ ትምህርት እንደሚኖር ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም ፤ አሁን ግን በወረርሽኙ ምክንያት ተቋማት ትምህርት በኢንተርኔት አማካይነት ወደ መስጠት አዘንብለዋል።

#3

በማንችስተር ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ለ14 ቀናት በኢንተርኔት አማካኝነት እንደሚማሩ ተገልጿል።

127 ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው ሲረጋገጥ 1,700 ተማሪዎች ደግሞ ለ2 ሳምንት ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ተደርጓል።

#4

በግላስኮ ዩኒቨርስቲ 172 ተማሪዎች ኮሮና ሲገኝባቸው 600 ተማሪዎች ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ተወስኗል።

#5

- በኩዊንስ ዩኒቨርስቲ ቤልፋስት ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በመረጋጋጡ የተወሰኑ ተማሪዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ተደርጓል።

በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ቅይጥ በሆነ ስልት እንደሚያስተምሩ ታውቋል። ይህም በኢንተርኔትና በገጽ ለገጽ የሚሰጥ ትምህረትን ጎን ለጎን መስጠትን ያካትታል ተብሏል።

ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,747 የላብራቶሪ ምርመራ 612 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 390 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 73,944 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,177 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,753 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መስከረም 18/2013 ዓ/ም አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦ - ባለፉት 24 ሰዓት ህንድ ውስጥ ተጨማሪ የ1,040 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 82,767 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል። - ሜክሲኮ በ24 ሰዓት 399 ሰዎችን አጥታለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች 76,243 ደርሰዋል። - ግሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ስደተኛ የኮቪድ-19 ሟች ተመዝግቧል፤ ሟቹ 61…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የትምህርት ተቋማት እደገና የሚከፈቱት የሁሉም ልጆቻችን ደህንነት ማረጋገጥ ስንችል ብቻ ነው" - ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፥ "የትምህርት ተቋማት እንደገና መከፈት ያለባቸው የሁሉም ልጆቻችንን ደህንነት ማረጋገጥ ስንችል ብቻ ነው" ብለዋል።

ፕሬዘዳንት ኡሀሩ ኬንያታ አሁን ትኩረት ልናደርግ የሚገባው 'መቼ ትምህርት ቤቶች ይከፈቱ ?' በሚለው ላይ ሳይሆን 'እንዴት የልጆቻችን ጤና ፣ ህይወት እና ደህንነት ተጠብቆ ትምህርት ተቋማት ይከፈቱ በሚለው ላይ መሆን አለበት' ብለዋል።

ዛሬ ፕዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የትምህርት ተቋማት መከፈቻ ጊዜን ያሳውቃሉ ተብሎ በጠበቅም ይህ ሳይሆን ቀርቷል።

በነገራችን ላይ የኬንያ ትምህርት ሚኒስቴር ከትላንት ጀምሮ መምህራን በየትምህርት ቤታቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳውቆ ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀነኒሳ በቀለ ለንደን ከትሟል!

ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የለንደን ማራቶን ውድድር ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ለንደን መከተሙ እና ወደ ተዘጋጀለት ሆቴል መግባቱን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል። 

@tikvahethsport @tikvahethiopia
ነገ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች !

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ ፡-

• በመሳለምያ ፣ በእሳት አደጋ ፣ በሳንባ ነቀርሳ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ፣ በታይዋን ፣ በሆላንድ ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ፡-

• በሃና ማርያም ፣ በሃይሌ ጋርመንት ፣ በቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም ፣ በማንጎ ሰፈር ፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም ፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ፤ ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ የኢ/ኤ/አ አሳስቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia