TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ አስታውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ም/አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ተከታዩን ብለዋል ፦

- በ488 የክስ መዝገብ 5 ሺህ 728 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶባችዋል።

- 3 ሺህ 377 ተከሳሾች በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር የሚወድቅ ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠያቂነታቸው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን፤ 2 ሺህ 351 ተከሳሾች ደግሞ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር ይሆናል።

- በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾች በ114 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደግሞ በ374 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- የክስ መዝገብ ከተከፈተባቸው መካከል 63 ግለሰቦች በሀረር በፈረሱ ሃውልቶች ምክንያት በሽብር ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚሆኑ ናቸው።

- በኦሮሚያ ክልል ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኃላ በተከሰተው ሁከት 167 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፣ 360 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ ከ4 ቢሊየን 673 መቶ ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ማድረሱ በምርመራ ተጣርቷል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም - መስከረም 8/2013 ብቻ እስከ 150 ሰዎች መገደላቸውን 3 ፓርቲዎች አሳውቀዋል!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱት ፦

- የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ)
- የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ነፃነትና ንቅናቄ ለሰላም እና ዴሞክራሲ ድርጅት

ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 8/2013 ዓ/ም ድረስ በጉባ፣ ወንበራና ቡለን ወረዳዎች በታጣቂዎች እና በፀጥታ አካላት በተወሰዱ እርምጃዎች እስከ 150 ሰዎች መሞታቸውን ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው በጥናት ማረጋገጣቸውን ለ 'አዲስ ማለዳ' ጋዜጣ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ላይ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ የደረሰው ማለዳ 12:00 እንደሆነ በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ለአብመድ አሳውቋል። የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ስለጉዳዩ #ለአብመድ (AMMA) ተከታዩን ብለዋል ፦ - ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ…
#UPDATE

ትላንት በተደረገ ግምገማ የዳንጉር ወረዳ የሠላም ግንባታና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመከላከያ ሠራዊት የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥና የዞኑ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና አስታወቁ።

የፅህፈት ቤት ኃላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት በንገዝ ቀበሌ ጥቃት ሊከሰት ይችላል የሚያስብሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን የተመለከተው የቀበሌው ሊቀ-መንበር ለጽህፈት ቤቱ መረጃ ቢያሳውቅም ፣ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን ችላ በማለቱና ለጸጥታ ኃይሉ በወቅቱ መረጃ አለማድረሱን ተክትሎ ተገቢው ጥንቃቄ ሳይደረግ ጉዳት በመድረሱ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ ፤ እንኳን አደረሰን !

በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የይቅርታ ይሆን ዘንድ እንመኛለን !

መልካም በዓል !
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ30 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,679 የላብራቶሪ ምርመራ 527 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 166 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 72,700 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,165 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,029 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 17/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ህንድ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1,124 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ ፤ 89,010 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 737 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ ፣ 43,206 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ብራዚል ውስጥ 732 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 25,536 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል ሜክሲኮ (405) ፣ አርጀንቲና (335) እንዲሁም ኢራን (172) ይገኙበታል።

- በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 998,745 ፤ በቫይረሱ የተያዙ 33,058,423 እንዲሁም ያገገሙ 24,409,745 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለኮቪድ-19 የሚሰጠው ትኩረት መቀነስ አሳሳቢ ነው!

(በዶክተር መክብብ ካሳ)

የዓለም ጤና ድርጅት እንደተነበየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል የሁለት ሚሊየን ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ይችላል፡፡

በሀገራችን የበሽታው አሳሳቢነት ጨመረ እንጂ አልቀነሰም፤ በየቀኑ የበርካታ ዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከተሉትን አራት መንገዶች ሀገራት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡

1. የቫይረሱን ስርጭት ሊያባብሱ የሚችሉ ኘሮግራሞችን መገደብ፡፡
2. በቀላሉ ሊጎዱ ለሚችሉ ዜጎች ትኩረት መስጠት፡፡
3. ማህበረሰብን ስለ ወረርሽኙ ማስተማርና ማንቃት፡፡
4. Test,Treat,Trace (መመርመር፣ የታመሙት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣ እና ንክኪ ያላቸውን መለየትና መመርመር ናቸው፡፡)

የሚደረገው ምርመራ መቀነስ ፣ ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች ለይቶ የመመርመር ስራ መቀነስ ፣ አርአያ መሆን የሚችሉ ታዋቂ ግለሰቦች የመንግስት እና የግል ተቋማት ተወካዮች የሚያሳዩት ቸልተኝነት እና የሚድያው መሰላቸት ተደማምሮ ወረርሽኙን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳንችል የብዙዎችንም ልፋት መና እንዲቀር ያደርጋል፡፡

ትንፋሽ አጥሯቸው የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን እናስባቸው ፤ የእኛ ቸልተኝነት ለራሳችንም ለሌሎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል ፤ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 75 የሕክምና ዶክተሮች ጨምሮ 1,732 ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይ በክብር እንግድነት ተገኝተው እንደነበር ከዩኒቨርሲቲው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,631
በበሽታው የተያዙ - 632
ህይወታቸው ያለፈ - 5
ከበሽታው ያገገሙ - 334

መስከረም 17/2013 ዓ/ም
(ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን አልፏል።

በመላው ዓለም በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ከተያዙት 33 ,212 ,069 ሰዎች መካከል የ 1, 000,588 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ጥንቃቄ አይለየን😷

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 18/2013 ዓ/ም

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ህንድ ውስጥ ተጨማሪ የ1,040 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 82,767 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ሜክሲኮ በ24 ሰዓት 399 ሰዎችን አጥታለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች 76,243 ደርሰዋል።

- ግሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ስደተኛ የኮቪድ-19 ሟች ተመዝግቧል፤ ሟቹ 61 ዓመት ወንድ ሲሆን ከማልካሳ የስደተኞች መጠለያ ነው ፤ ህይወቱ ያለፈው በአቴንስ ሆስፒታል እንደሆነ ተገልጿል።

- አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 1,467,555 ደርሷል፤ ከነዚህ ውስጥ የ35,215 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1,213,045 ሰዎች አገግሟል።

- የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በኬንያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመለሱበትን ቀን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስለል ?

#WolitaSodoUniversity

- ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ከንክኪ ዉጪ የሆነ የእጅ መታጠቢያ ተማሪዎች በብዛት በሚገኙበት አከባቢ ለማኖር ተዘጋጅቷል። የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዝር ፣ ሳሙና እና ዉኃ ተደራሽ የማድረግ ሥራም ይሰራል።

- የካፌ ዝግጅትን በተመለከተ ሁለቱም የተማሪዎች መመግቢያ አዳራሾች ጥገና እና በዘመናዊ ማሽን እየተተካ ነዉ፡፡

- ዶርምን በተመለከተ ካራኒታይን የሆኑ መኝታ ቤቶች የዲስ ኢንፌክት ስራ ከዛሬ ጅምሮ ይካሄዳል፡፡ የዶርምና አከባቢም ፅዳት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

- ከኮሮና ጋር በተያያዘ ጥግግትን ከመቀነስ አንፃር በአንድ ዶርም 3 ተማሪ የመመደብ ስራ ለመስራት ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

- አካዳሚክ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁሉም መምህራን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካዳሚክ ዘርፉም ልዩ ትኩርት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።

#AmboUniversity

- አምቦ ዩኒቨርሲቲው ካለው 4 ካምፓሶች አሁን ላይ የሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ (አዋሮ) በካሯንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

- አምቦ ዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ከጀመረ የቆየ ሲሆን ግቢዎችን ዲስኢንፌክት የማድረግ ሥራም ይሰራል ተብሏል፡፡

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለባቸው እና በቸልተኝነት ኃላፊነት በአግባቡ ባልተወጡ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ የክልሉ መንግስት ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጿል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው 45 አመራሮች ውስጥ አንድ የአመራር ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ከኃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ከመካከላቸው 10ሩ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ እና ምርመራ እንዲጣራባቸው ተደርጓል።

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከእስር ቤት ሊያመልጥ የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአንኮበር ወረዳ አንኮበር ፖሊስ ጣቢያ ሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተጣራበት የሚገኘው ደስታ አለሙ የተባለው ግለሰብ ከእስር ቤት ግድግዳ ፈርፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር ጥበቃ ላይ በነበሩ የፖሊስ ኦፊሰሮች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተጠርጣሪው በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3፡30 ላይ ድርጊቱን መፈፀሙንና በዚህ ላይም የምርመራ ፋይል ተከፍቶ መዝገቡ እየታየ መሆኑን የአንኮበር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Ankober Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገፁ የቦርዱ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia