#UPDATE
ወደ መቐለ እንዳይሄዱ ከታገዱት ሰዎች መካከል ' የአውሎ ሚዲያ ' ጋዜጠኞች ይገኙበት እንደነበር የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው አረጋግጦልናል።
ጋዜጠኞቹ ወደ መቐለ ሊጓዙ የነበሩት ጳጉሜ 4 የሚደረገውን ክልላዊ ምርጫ ለመዘገብ ነበር።
ወደ መቐለ ከተማ እንዳሄዱ ከማገድ በተጨማሪ ጋዜጠኞቹ ተይዘው እቃዎቻቸው ተወስዶ አሁን እንደተለቀቁ የአውሎ ዋና አዘጋጅ ገልፆልናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #3 በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ መደረጉን ኤፍቢሲ ዘግቧል። ማሻሻያው ፦ - ሚኒባስ ፣ የአንበሳ አውቶብስ ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ ተወስኗል። - የሚኒባስ ታክሲዎች ከኋላ ባለው መቀመጫ ከ2 ሰው በላይ መጫን አይችሉም። - ባለ ሶስት እና ባለ…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #4
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን የቤት መኪኖች እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች በወንበር ልክ እንዲጭኑ መወሰኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን የቤት መኪኖች እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች በወንበር ልክ እንዲጭኑ መወሰኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእነ አቶ ጀዋር መሃመድ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ!
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በዛሬው ዕለት የእነ አቶ ጀዋር መሃመድን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡
አቶ ጀዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አስር (10) ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ሕግ መስከረም 8 በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰርት ችሎቱ ውሳኔ ማሳለፉን ኢብኮ ዘግቧል።
በተጨማሪ ፍርድ ቤት ከአስራ አንደኛ እስከ አስራ አራተኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በ5 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርትባቸው ትእዛዝ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትሯ ስጦታ ተበረከተላቸው!
ኔቶር ኢቨንትና ፕሮሞሽን እና አዱሊያን ማስታወቂያ ከዋልታ ቲቪ ጋር በመተባበር 'ክብር ለጤና ባለሞያዎቻችን' በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የአዲስ አመት ዝግጅት ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ስጦታ ተበረከተላቸው።
ስጦታውን ያበረከተው የከበሩ ማዕድናት አቅራቢዎች ማህበር ሲሆን ማህበሩን በመወከል የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ሳሙኤል ግዛዉ ስጦታውን ለዶ/ር ሊያ አበርክተዋል።
ለዶ/ር ሊያ የተበረከተላቸው ስጦታ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነት ያለቸዉ ኤመራልድ እና ሞንጋናይዝ የተባሉ የከበሩ ማዕድናት እንደሆኑም አዘጋጆቹ አሳውቀውናል።
በፕሮግራሙ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ፣ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ጨምሮ ሌሌች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተው ነበር።
ዝግጅቱ ለአዲስ አመት ዋዜማ በዋልታ ቲሌቪዥን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ እንደሚተላልፈ ተገልጾልናል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለ2 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የኦፕሬተርነት ፍቃድ ወስደው እንዲሰሩ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለተመረጡት ኩባንያዎች የሚተላለፍ ሲሆን 5 በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ይሸጣል።
የ5 በመቶ አክስዮን ሽያጭም በጥቂት ግለሰቦች የሚያዝ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ አቅሙ በፈቀደ መጠን የሚሳተፍበት መሆኑ ታውቋል።
የማሻሻያ ስራዎቹን በተመለከተ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የባለድርሻ አካላት ወይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለተመረጡት ኩባንያዎች የሚተላለፍ ሲሆን 5 በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ይሸጣል።
የ5 በመቶ አክስዮን ሽያጭም በጥቂት ግለሰቦች የሚያዝ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ አቅሙ በፈቀደ መጠን የሚሳተፍበት መሆኑ ታውቋል።
የማሻሻያ ስራዎቹን በተመለከተ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የባለድርሻ አካላት ወይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፓኪስታን ትምህርት ቤቶች ሊከፈቱ ነው!
በፓኪስታን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተዘጉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሊከፈቱ እንደሆነ ተሰምቷል።
የሀገሪቱ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮቪድ-19 የሚያዙ እንዲሁም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በመቀነሱ መሆኑ ተነግሯል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፓኪስታን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተዘጉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሊከፈቱ እንደሆነ ተሰምቷል።
የሀገሪቱ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮቪድ-19 የሚያዙ እንዲሁም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በመቀነሱ መሆኑ ተነግሯል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 684 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 690 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት፦
- 9 ከመንጌ ወረዳ
- 5 ከሸርቆሌ ወረዳ
- 4 ከሆሞሻ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ወረዳ
- 9 ከበሎ (ምዥጋ ወረዳ)
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 521 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,947 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከደ/ብርሃን የኮሮና ህክምና ማዕከል)
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 20 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 14 ከሰ/ወሎ ዞን
- 14 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,367 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 346 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 212 ከምስራቅ ሸዋ
- 31 ከምዕራብ ወለጋ
- 28 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 14 ከጅማ ከተማ
- 12 ከሰበታ ከተማ
- 9 ከአርሲ ዞን ይገኙበታል።
@tikvahethiopiaBOT

#COVID19Ethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 482 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59,648 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 933 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 21,789 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 482 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59,648 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 933 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 21,789 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,356 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ቫይረሱ የተያዙት፦
- ከወላይታ ዞን 17 (7 ከሶዶ ዙሪያ፣ 7 ከዱጉና ፋንጎ፣ 1 ከሶዶ፣ 1 ዳሞት ሶሬ እና 1 ከቦሎሶ ሶሬ) ፣
- ከደቡብ ኦሞ ዞን 12 ( 6 ከሳላማጎ እና 6 ከማሌ)፣
- ከቤንች ሸኮ ዞን 8 (8ቱም ከሚዛን ከተማ )፣
- ከሃዲያ ዞን 7(3 ከጊምቢቹ፣ 3 ከምስራቅ ባደዋቾ እና 1 ከሾኔ)፣
- ከደራሼ ልዩ ወረዳ 4፣
- ከጋሞ ዞን 3 (1 ከአርባምንጭ ፣ 1 ከዲታ እና 1 ከጨንቻ)፣
- ከዳውሮ ዞን 3 (3ቱም ከማረቃ)፣
- ከጉራጌ ዞን 3 (3ቱም ከምሁር አክሊል)፣
- ከአሌ ልዩ ወረዳ 2፣
- ከስልጤ ዞን 2 (1 ከጦራ እና 1 ከወራቤ ከተማ)፣
- ከጌዴኦ ዞን 2 (1 ከጨለለቅቱ እና 1 ከወናጎ)፣
- ከቡርጂ ልዩ ወረዳ 1፣
- ከከምባታ ጠምባሮ ዞን 1 ( ከዱራሜ ከተማ)፣
- ከሃላባ ዞን 1 (ዌራዲጆ) ናቸው።
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 195 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 26 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Tigray
በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 107 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ሰማንያ ሰባት ሰዎች ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

በኢትዮጵያ ትምህርት ለማስጀመር ጥናት ተደረገ!
ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያጋልጥ በማይችል እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲሱ ዓመት ለማስጀመር ጥናት መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር በመመጠንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ትምህርት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ጥናት ተደርጓል።
የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ባለፈው የመማር ማስተማር ሂደት በአማካይ ከ60 እስከ 80 ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ይማሩ የነበረበት ሁኔታ አስታውሰዋል።
በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት በቅድመ መደበኛ 14 በመቶ የሚሆኑትን ትምህርት ቤቶች ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ብቻ በአንድ ክፍል እንዲያስተምሩና አንድ ተማሪ በአንድ ዴስክ ብቻ እንዲቀመጥ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።
አቶ ሚሊዮን እንዳሉት ቀሪዎቹ 80 በመቶ ተማሪዎች በፈረቃ እንዲማሩና 6 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤት በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር ታቅዷል።
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 24 በመቶ ወይም ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች በአንድ ከፍል ውስጥ እንዲማሩ ፣ 56 በመቶ በፈረቃ እንዲሁም 20 በመቶ ተጨማሪ ክፍል በመገንባት እንዲማሩ ተወስኗል።
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 19 በመቶ ተማሪዎች ወይም ከ20 እስከ 25 የሚሆኑት በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲማሩ እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በፈረቃ የሚማሩ ይሆናል።
ሌሎች 31 በመቶ ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባትና አማራጭ ማህበራዊ ተቋማትን በመጠቀም ለማስተማር መታቀዱንም አመልክተዋል https://telegra.ph/ENA-09-07
@tikvahethiopiaBOT @TikvaahEthiopia

ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ ወቀት አንድ ላይ ሊከፈቱ እንደማይችሉና ደረጃ በደረጃ የመክፈት ሂደት እንደሚኖር ለኢዜአ ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የትምህርት አጀማመሩ ከክልል ክልል እና ከዞን ዞን ሊለያይ እንደሚችልም አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑ የገለፀ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ትምህርት ቤቶችን #እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የትምህርት አጀማመሩ ከክልል ክልል እና ከዞን ዞን ሊለያይ እንደሚችልም አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑ የገለፀ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ትምህርት ቤቶችን #እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ ኮቪድ-19 የሚሰራጭበት ፍጥነት!
በአዲስ አበባ ከተማ ከነሃሴ (1 እስከ 30) በአጠቃላይ 18,801 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 446 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ወቅት ህይወታቸው አልፏል።
ነሃሴ ወር የነበረው ስርጭት (በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች) ከሃምሌ ወር ጋር ሲነፃፀር በ9,384 ወይም 99.6% ጭማሪ አሳይቷል፤ ይህም የቫይረሱ ስርጭት በእጥፍ መጨመሩን ያሳያል።
የሞት መጠንን ስንመለከት በነሃሴ ወር 446 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በሀምሌ ወር ደግሞ 191 ሰዎች ነበር ህይወታቸው ያለፈው። ይህም ከሁለት እጥፍ በላይ የነሃሴ ወር ሞት መጠን ጭማሪ ማሳየቱን መረዳት ይቻላል።
በሽታው በነሃሴ ወር ብቻ የመግደል ምጣኔው ባለፉት 5 ወራት ከገደለው በሶስት ሳምንት ብቻ በእጥፍ ማደጉን መገንዘብ ይቻላል። በአንፃሩ የከተማው ነዋሪ የሚታየው ጥንቀቄ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከበሽታው ስርጭት እና የመግደል ምጣኔ በተቃራኒው በመቀነስ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት ይስተዋላል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስሩም ክፍለ ከተሞች በተደረገ ከቤት ውጭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የመጠቀም የዳሰሳ ጥናት በጥናቱ ከተካተቱት 14,836 ሰዎች ውስጥ 11,119 ሰዎች ይኸውም 74.9% የሚሆኑት ብቻ በአግባቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተጠቀሙ ናቸው።
በማህበረሰቡ ውስጥ በተለይ አፍ እና አፍንጫን በአግባቡ ከመሸፈን ፣ ርቀትን ከመጠበቅ እንዲሁም እጅን በአግባቡ እና በየጊዜው ከመታጠብ አንፃር ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ!
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ የወንጀል ችሎት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።
ፖሊስ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና ከእስር ቢፈቱ መረጃ ያጠፉብኛል ቢልም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አልተቀበለውም።
ፖሊስ ከአራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች መካከል በበላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ላይ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ሲሆን በዋነኛነት ከኢመድኤ / INSA ፣ ከሆስፒታል እና ከብሮድካስት ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመጣ ጠቅሶ ከእስር ከወጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለሆኑ መረጃ ያጠፉብኛል ብሏል።
ይሁንና ፍርድ ቤቱ መረጃ ይመጣባቸዋል ከሚባሉት ተቋማት መረጃ ማጥፋት ሆነ ማዛባት እንደማይቻል ገልፆ የእስር ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ፖሊስ መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሎታል።
ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን

CONGRATULATIONS!
ዛሬ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 659 ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ተማሪዎች በእፅዋት ሳይንስ ፤ በኢኮኖሚክስ እና በሌሎች የተለያዩ የትምህርት መሰኮች የሰለጠኑ 515 ወንድ እና 144 ሴቶች በድምሩ 659 ተማሪዎች ናቸው።
በሌላ በኩል ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 3 ስፔሻሊስት ዶክተሮችን ፣ 47 የህክምና ዶክቴሮችን ፣ 486 የድህረ ምረቃ እና 543 ተከታታይ ተማሪዎች በአጠቃላይ 1ሺህ 79 ተማሪዎችን አስመርቃል።