TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነሃሴ 11/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1 ፦

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,962 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከደ/ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል)

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦

- 21 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 18 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 12 ከደሴ ከተማ
- 10 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን
- 6 ከደ/ወሎ ዞን
- 5 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 495 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 1 ሰው ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 1 ሰው ከጉባ ወረዳ
- 1 ሰው ከአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት
- 1 ሰው ከአሶሳ ከተማ፣ 2 ሰዎች ከሰዳል ወረዳ፣ 1 ሰው ከካማሽ ከተማ ናቸው።

#Oromia

ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 3,843 ሲሆን 224 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 3,117 በቫይረሱ የተያዙ
- 35 ሞት
- 979 ያገገሙ

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,253 ላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 192 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በትግራይ ፦
- 1,962 በቫይረሱ የተያዙ
- 14 ሞት
- 832 ያገገሙ

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 309 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 35 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

- 35 ጅግጅጋ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,460 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,747 የላብራቶሪ ምርመራ 1,460 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 165 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 31,336 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 544 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 12,524 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 11/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2 ፦

#SNNPRS

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደቡብ ክልል በተደረገው 526 የላብራቶሪ ምርመራ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦

- 9 ከጌዴኦ (ሁሉም ከዲላ ከተማ)
- 3 ከወላይታ (2 ከሁምቦና 1 ወ/ሶዶ)
- 2 ከዳውሮ (ሁለቱም ከተርጫ)
- 1 ከካፋ (ቦንጋ)

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 501 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 63 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ የአንድ (1) ሰው ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 721 በቫይረሱ የተያዙ
- 13 ሞት
- 143 ያገገሙ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 714 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሐረሪ ፦

- 555 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 87 ያገገሙ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 19,881 ደረሱ!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,641 የላብራቶሪ ምርመራ 674 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በ24 ሰዓት የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ከነዚህ መካከል 8 ሰዎች በአስክሬን ላይ ከተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ ሲገኝባቸው 6 ሰዎች ከጤና ተቋም ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ብዛት ሁሉንም ጎረቤት ሀገራት በልጣ #በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ግንቦት 24/2012 ዓ/ም

• ሱዳን - 5,026
• ጅቡቲ - 3,569
• ሱማሊያ - 2,023
• ኬንያ - 2,021
• ኢትዮጵያ - 1,257
• ደ/ሱዳን - 994
• ኤርትራ - 39

ዛሬ ነሃሴ 11/2012 ዓ/ም

• ኢትዮጵያ - 31,336
• ኬንያ - 30,365
• ሱዳን - 12,410
• ጅቡቲ - 5,369
• ሱማሊያ - 3,257
• ደ/ሱዳን - 2,489
• ኤርትራ - 285

በነገራችን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ በኢትዮጵያ የሚደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ከሌሎቹ ሀገራት በእጅጉ ይልቃል።

#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች ማስቀመጥ ተከለከለ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው በኢትዮጵያ ግለሰቦች ወይንም ኩባንያዎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ማስቀመጥ መከልከሉን ይፋ አድርገዋል።

የመንግስትም ሆኑ የግል ባንኮች ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በዶላር መበደር ይችላሉም ተብሏል።

ይህ አሰራር ደግሞ በአገሪቱ የሚስተዋለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል ይረዳል ብለዋል።

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክነት ማደግ የሚችሉበት መመሪያ መውጣቱን ዶክተር ይናገር ይፋ አድርገዋል #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሶሳ ከተማ ሺሻ ሲጠቀሙ እና ሲያስጠቅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአሶሳ ከተማ ሺሻ ሲጠቀሙ እና ሲያስጠቅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡

ነሐሴ 10/2012 ዓ.ም ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ከምሽቱ 4፡00 በአንድ ግለሰብ ድርጅት ቤት ፖሊስ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ግለሰቡ ቤቱን በመዝጋት ሺሻ ሲጠቀሙ የነበሩ 13 ሰዎች በቤቱ ኮርኒስ ያሳደረ ቢሆንም ነሐሴ 11/2012 ዓ/ም ረፋድ 4፡00 ፖሊስ ባደረገው ርብርብ ግለሰቡ እስከነግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኮሮና ወርርሽኝን ለመከላል የወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጣስ ግለሰቡ 13 ግለሰቦችን በአንድ ቤት ሰብስቦ ሲያስጠቅም መገኘቱን ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።

ግለሰቡ በተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት መሰማራቱ የተነገረ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ጭምር በመሰብሰብ ሺሻ ሲያስጠቅም የነበረ፣ ያለንግድ ፍቃድ የተለያዩ የአልኮል መጠጦችን ሲሽጥ እንደ የነበረ እና አደንዛዥ እጽ ሲያስጠቅም እንደነበር መምሪው አሳውቋል።

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተወሰኑ የምግብ ሸቀጦች ሙሉ ለሙሉ ከቀረጥ ነፃ እየገቡ መሆናቸው ተገለጸ!

መንግሥት የሸቀጦችን ዋጋ በማረጋጋት ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በአምስት መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረውን ቀረጥ ሙሉ ለሙሉ ማንሳቱ ገልጿል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሙኒኬሽን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሳወቀው፤ መንግሥት በምግብ ሸቀጦች ላይ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ የዳቦ ስንዴ፣ ሩዝ እና የታሸጉ የሕፃናት ምግቦችን ሙሉ ለሙሉ ከቀረጥና ታክስ ነፃ አድርጓል፡፡

መንግሥት ከእነዚህ ምርቶች ያገኝ የነበረው ገቢ ሙሉ ለሙሉ በመሰረዝ ምግቦቹን ከውጭ ለሚያስገቡ ነጋዴዎች ቀረጥ እና ታክሱን ነፃ አድርጎ ኅብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ማግኘት ያለበትን መሠረታዊ የምግብ ሸቀጥ በቀላሉ እንዲያገኝ እገዛ እያደረገ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#BREAKING

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:-

• ዶ/ር ቀንዓ ያደታ - የመከላከያ ሚኒስትር
• ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ - ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
• ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
• ኢ/ር ታከለ ኡማ - የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር
• አቶ ተስፋዬ ዳባ - ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
• አቶ ዮሐንስ ቧያለው - የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
• አቶ ንጉሡ ጥላሁን - የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
• ኢ/ር እንደአወቅ አብቴ - የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
• አቴ ፍቃዱ ጸጋ - ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
• ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ም/ከንቲባ አድርጎ የሾመው ከተገኙት 85 የምክር ቤት አበላት በ2 ድምጸ ተአቅቦ በ6 ተቃውሞ በ77 ድምጽ ድጋፍ ነው።

የቀድሞ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባለፉት ሁለት አመታት የከተማ አስተዳደሩን በምክትል ከንቲባነት የመሩት ኢንጂነር ታካለ ኡማን የሚተኩ ይሆናል።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤም ቃለ መሀላ የፈጸሙ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩን ላለፉት ሁለት አመታት በምክትል ከንቲባነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ታከለ ኡማም የከተማዉን ቁልፍ አስረክበዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ዣንጥራር አባይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪተቋማት አስተባባሪ ሆነው ተሾሙ!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ዣንጥራር አባይን በም/ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አድርጎ በሙሉ ድምፅ መሾሙን አዲስ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩም የጠየቁትን የዋስትና መብት ጥያቄ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉን ኢብኮ ዘግቧል።

ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበት ወንጀል ሞት ያስከተለና ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ ስለሚችል የዋስትና መብታቸው ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን መርምሮ የዋስትና መብት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። በዚህም ዐቃቤ ሕግ የምስክሮቹን ቃል መዝገብ ግልባጭ በደረሰው በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሠርት ተፈቅዶለታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ በ24 ሰዓት 218 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 1,887 የላብራቶሪ ምርመራ 218 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,180 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ 87 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከኮቪድ-19 አገግመዋል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 919 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ክትባት!

'ኖቫቫክስ' የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ የክትባት ኩባኒያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱን ሁለተኛ ምዕራፍ የሰው ላይ ሙከራ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊጀምር እንደሆነ ቪኦኤ አስነብቧል።

በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ሙከራ ጤናማ የሆኑ 2,665 አዋቂዎች የሚሳተፉበት እንደሚሆን ኩባኒያው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በተጨማሪም ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ነገር ግን በደህና የጤና ሁኔታ ላይ ያሉ 240 ሰዎች ላይ ክትባቱ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚያመጣም ይፈተሻል።

ኖቫቫክስ ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ እና አውስትራሊያ ውስጥም ተመሳሳይ ሙከራዎች እንደሚያደራጅ መግለፁን ከቪኦኤ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia