TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምክንያት አልሆንም!

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከልና በልዩ ትኩረት በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል የማህበረሰብ ንቅናቄ እና ምርመራ (ማንም) ዘመቻ፡ 'ምክንያት አልሆንም' በሚል መሪ ቃል ይፋ አድርገዋል፡፡

የዘመቻው ዋነኛ አላማ ማንኛውም ሰው ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ላለመሆን ራሱን የሚከላከልበት ፣ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡን እንዲሁም አካባቢውን የሚጠብቅበት እና በተሰማራበት ሙያ ሁሉ ሃላፊነት በመውሰድ በእኔነት ስሜት ለራሱ ቃል የሚገባበት ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ሽማግሌ ልኳል ?

ከሰሞኑን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በፌደራል መንግስቱና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ህወሓት ለሽምግልና በዶ/ር አዲስአለም ባሌማ የተመራ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ልኳል ተብሎ ሲነገር ነበር።

በዚህ ጉዳይ የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም '#አባይ' ከተባለ ሚዲያ ስለጉዳዩ እውነትነት ጥያቄ ቀርቦላቸው 'ሲናፈስ የነበረው ነጭ ውሸት ነው፣ ህወሓት ሽማግሌ አላከም፣ ሊልክም አይችልም' ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ወ/ሮ ኪሪያ ህወሓት አሁንም ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ነገር ግን አሁን ያለው ችግር ሀገራዊ ስለሆነ ጉዳዩን የህወሓት እና የብልፅግና ፓርቲ ብቻ አድርጎ መወሰድ እንደሌለበት ፤ ሁሉንም ወገን ያካተት፣ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ ከተዘጋጀ ፓርቲው እንደማንኛው ፓርቲ ለመሳተፍ ዝግጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ኪሪያ 'በህወሓት እና በብልፅግና ፓርቲ መካከል ብቻ የሚደረግ የውይይት መድረክ ሊሆን አይችልም ፤ ከዚህ ቀደም ወደ መቐለ መጥተው ለነበሩት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የተሰጠው ሀሳብም ይኸው ነው ፤ አሁንም የያዝነው አቋም ይህ ነው' ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጆሃንስበርግ አቅራቢያ የሚገኘው የወል መቃብር!

የኮሮና ቫይረስ በሽታ/ኮቪድ-19 ከተስፋፋባቸው የዓለማችን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት።

ከቪኦኤ እንደተገኘው መረጃ የሀገሪቱ ባለሥልጣናቱ የወል የቀብር ስፍራ አዘጋጅተዋል። እስካሁን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ከ9,900 በላይ ሰዎች ሞተዋል።

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱ የወል መቃብር ሥፍራ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጆሃንስበርግ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ነው።

በደቡብ አፍሪካ እስከዛሬ 545,476 ሰዎች በኮሮና ቫይስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከ394,000 በላይ ሰዎች አገገመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከ1,900 አለፉ!

በኦሮሚያ ክልል ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት በእጅጉ እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 2,139 የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 111 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከአንድ መቶ አስራ አንዱ (111) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል ሰላሳ ሁለቱ (32) ሰዎች ነቀምቴ ከተማ ናቸው።

በአጠቃላይ በክልሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,932 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ የትዊተር ገፅ!

ትዊተር ላይ የምታዘወትሩ የቲክቫህ አባላት የኢትዮጵያን ሀገር አቀፍና የክልል የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ከታች ባለውን ሊንክ ማግኘት ትችላላሁ።

TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia):
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ22 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 10,919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 292 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,253 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 390 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,707 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት!

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 71,297 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ ሀገራት የ1,780 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 36,080 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የትዊተር ገፅ አማራጭ!

ምንም እንኳን ከ8 ዓመት በፊት የትዊተር ገፁ የተከፈተ ቢሆንም አክቲቭ ሳይሆን እስከዛሬ ቆይቷል።

ከዛሬ ጀምሮ ለመላው የቲክቫህ አባላት ትዊተር ላይ አማራጭ የመረጃና የሀሳብ መለዋወጫ ሆኖ ቀርቧል።

በተለይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦቻችሁ ለመስጠትና እርስ በእርስ ፍፁም መከባበር በተሞላበት መልኩ ለመነጋገር የትዊተር ገፁን እንደ አማራጭ ተጠቀሙት።

የትዊተር ተጠቃሚዎች ገፁን TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia): ታገኛላችሁ!
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ የምርመራ አቅምን ለማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ከፍቶ ትናንት ስራ ማስጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

ዩኒቨርሲቲው በጎባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለማስጀመር እንዲቻል የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያውን በድጋፍ ያገኘው ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

አገልግሎት መስጠት የጀመረው የምርመራ መሳሪያ በቀን እስከ አራት መቶ ናሙና የመመርመር አቅም አለው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአማራ ክልል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከ700 ሲያልፉ፤ በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ከ2,000 አልፈዋል!

አማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 2,542 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 4 ከደሴ ፣ 3 ከባህር ዳር ፣ 6 ከደ/ወሎ ዞን ፣ 4 ከሰ/ሸዋ ዞን፣ 5 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን፣ 1 ከአዊ ብ/ሰብ ዞን፣ 1 ከሰ/ወሎ ዞን ይገኙበታል።

በአጠቃላይ በአማራ ክልል አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 703 ደርሰዋል፤ 489 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 7 ሰዎች ህወታቸው አልፏል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 2,010 ደርሰዋል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ከ976 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከሰባ ስምንቱ (78) መካከል 36 ሰዎች ከምስራቅ ሸዋ፣ 11 ሰዎች ከቡራዩ ፣ 8 ሰዎች ከለገጣፎ ፣ 8 ሰዎች ከነቀምቴ፣ 4 ሰዎች ከዱከም ፣ 3 ሰዎች ከሆለታ ይገኙበታል።

ትዊተር የምትጠቀሙ TIKVAH-ETHIOPIA : https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia):

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግስታቸው 100,000 መመርመሪያ ኪቶችን በዛሬው ዕለት መረከቡን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፉን ላደረጉ የኢትዮጵያ አጋሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት በቪድዮ እና በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ አሳውቀዋል።

በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ መንገዶች ተዘግተው እንደነበረ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው በመግባት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠርና፣ መንገዶችን ለመክፈት እየሞከረ እንደሆነ ሰምተናል።

በድምፅ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት በከተማይቱ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሆነም ገልፀዋል።

የከተማይቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት እንደሚናገሩት መነሻው በስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ተሳታፊዎች መታሰራቸው በመሰማቱ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,035 የላብራቶሪ ምርመራ 565 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 499 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,818 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 407 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,206 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት በቪድዮ እና በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ አሳውቀዋል። በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ መንገዶች ተዘግተው እንደነበረ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው በመግባት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠርና፣ መንገዶችን ለመክፈት እየሞከረ እንደሆነ ሰምተናል። በድምፅ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት በከተማይቱ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ…
#UPDATE

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸውን አል ዓይን አረጋግጧል፤ አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ከነበሩበት የተያዙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በከተማው ሁከት መከሰቱም ገልጿል።

የዞኑ አመራሮች ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከፌዴራል እና ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

የዞኑ ክልል የመሆን ጥያቄ በደቡብ ክልል መንግስት ተገቢው ምላሽ አልተሰጠውም በሚል ተቃውሞ በክልሉ ምክር ቤት የዞኑ ተወካዮች ራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት ራሳቸውን ካገለሉ ከ6 በላይ ሳምንታት ተቆጥረዋል።

የዞኑ ተወካዮች ወደ ም/ቤት እንዲመለሱ በክልሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስካሁን አልተቀበሉም። የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በራሱ ጊዜ ዞኑን በክልል ለማደራጀት ወስኖ ይህን ስራ የሚያስፈጽም ምክር ቤት ማቋቋሙ ይታወሳል።

Via AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia