ድምፃችን ለግድባችን!
ዛሬ ከ10:00 ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ዜጎች በያሉበት ሆነው ድምፃቸውን ባማረ እና በደመቀ መልኩ በጋራ አሰምተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የነበረው ድባብ እጅግ የሚያምር ነበር።
ለህዳሴ ግድባችን ድምፃችሁ ስታሰሙና ድስታችሁ ስትገልፁ የነበራችሁ ኢትዮጵያውያን በርካታ ፎቶዎችና ቪድዮዎችን አጋርታችሁናል እናመሰግናለን።
በዚህ የደስታ መግለጫ ስነ ስርዓት ወቅት በአንዳንድ ቦታዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ሊያባብስ የሚችል የመሰባሰብና ደስታን ጥንቃቄ ሳያደርጉ የመግለፅ ሁኔታ በእጅጉ ታይቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ከነገ ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩ በማህበራዊ ሚዲያው እየተነገረ ይገኛል፡፡
በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ፓሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ "ህዝባችን በልማት ሥራ ላይ ይገኛል የሚዘጋም መንገድ የለም" ሲል ገልጿል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ፓሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ "ህዝባችን በልማት ሥራ ላይ ይገኛል የሚዘጋም መንገድ የለም" ሲል ገልጿል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የ28 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,607 የላብራቶሪ ምርመራ 707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 406 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 18,706 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 310 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 7,601 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,607 የላብራቶሪ ምርመራ 707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 406 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 18,706 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 310 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 7,601 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Telegram!
ከዚህ ቀደም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETHIOPIA @tikvahethiopia) ይፋዊ ገፅ ላይ ተነስቶ የነበረው ፐብሊክ ሊንክ ቴሌግራም ወደቦታው እንዲመለስ አድርጓል ፤ በቀጣይ በቲክቫህ ስም የተከፈቱና ሀሰተኛ መረጃዎች የሚያሰራጩ ገፆችን ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ እንሰራለን።
በድጋሚ የቴሌግራም አስተባባሪዎችን እናመሰግናለን!

አጫጭር መረጃዎች ፦
- ትላንት በሀገራችን በኮቪድ-19 ህይወታቸው ካለፈ 28 ሰዎች መካከል ሃያ ስድስቱ (26) ከአ/አ ከተማ ናቸው። 24 በአስክሬን ምርመራ እና 2 ከጤና ተቋም እንደሆኑ ተገልጿል።
- በኦሮሚያ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,425 ደርሰዋል፤ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 21 ነው።
- በደቡብ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 201 ደረሱ ፤ እስካሁን የ3 ሰው ህይወት አልፏል፤ 52 ሰዎች አገግመዋል።
- በትግራይ ክልል አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 836 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 489 ሰዎች አገግመዋል።
- በአማራ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 565 ደርሰዋል፤ 6 ሞት ሲመዘገብ 446 ሰዎች አገግመዋል።
- በቤኒሻንጉል ክልል በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 213 ደርሰዋል ፤ ስልሳ ሁለቱ (62) ከበሽታው አገግመዋል።
- በሲዳማ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 224 ደርሰዋል፤ ትላንት ብቻ 40 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ሃያ ሁለቱ (22) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።
- በአፋር ክልል እስከዛሬ 284 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፥ ከነዚህ መካከል 117 ሰዎች አገግመዋል።
- በሱማሌ ክልል አጠቃላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 705 ደርሰዋል፤ 406 ሲያገግሙ 18 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ለሚመለከተው አካል! ለኮቪድ-19 ፈጣን ምላሽ በኮንትራት ተቀጥረው እየሰሩ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የተላከ መልዕክት ፦ "ለህዝባችን ስንል ነፍሳችን ሁሉ ከመስጠት ወደኃላ ሳንል ፣ ቀንና ሌሊት ፣ ሰንበትን ጨምሮ የዓመት በዓላት ለህዝባችን ስንል እየሰራን ነዉ። ሞትን እየተጋፈጥን ቢሆንም ስራዉን በአግባቡ እየሰራን እንገኛለን። ነገር ግን ከ70% በላይ ስራ የሚሰራዉ ኮንትራት ተቀጣሪ ሆኖ ሳለ የተጋላጭነት…
ቅሬታ ላቀረቡ የጤና ባለሞያዎች የተሰጠ ምላሽ!
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኮንትራት ሰራተኞች የተጋላጭነት ክፍያ የዘገየው ሰፊ በጀት የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ስለነበር መሆኑን ለአሶሼትድፕሬስ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልፀዋል።
ዶክተር ሊያ ፥ "ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የሁለት ወራት ክፍያ ተጀምሯል ፣ ወደፊትም ይቀጥላል። ስራው አንድ ስለሆነ የተጋላጭነት ክፍያው ከቋሚ ሰራተኞች ጋር እኩል ይሆናል። ጊዜያዊ መኖርያም አቅም በፈቀደ መጠን ለሁሉም ይሰጣል" ብለዋል።
የራስ መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በተመለከተ ለተነሳው ቅሬታም ዶክተር ሊያ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል : "ለቋሚዎች ሰጥተን ለኮንትራት ሰራተኞች የምንከለክልበት አሰራር የለንም። ያለንን ለሁሉም እኩል እናዳርሳለን ፣ ግን እጥረት ስላለብን የምናቀርበው በቂ አይደለም"

በሱማሊያ ዓለም አቀፍ በረራዎች ዳግም ተጀመሩ!
በሱማሊያ ኮቪድ-19 ለመቆጣጣር ታሳቢ በማድረግ ከ 4 ወር ከ15 ቀን በፊት ቆመው የነበሩት ዓለም አቀፍ በረራዎች ከዛሬ ጀምሮ ዳግም ጀምረዋል።
ከዚህ ቀደም ብሎ ከባለፈው ሰኔ 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ የሀገር ውስጥ በረራዎች ተጀምረው እንደነበር ይታወሳል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ኮቪድ-19 ለመቆጣጣር ታሳቢ በማድረግ ከ 4 ወር ከ15 ቀን በፊት ቆመው የነበሩት ዓለም አቀፍ በረራዎች ከዛሬ ጀምሮ ዳግም ጀምረዋል።
ከዚህ ቀደም ብሎ ከባለፈው ሰኔ 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ የሀገር ውስጥ በረራዎች ተጀምረው እንደነበር ይታወሳል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች ሊከፈቱ ነው!
የሱማሊያ መንግስት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ከመጭው ነሃሴ 9/2012 ዓ/ም ጀምሮ ዳግም እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሱማሊያ መንግስት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ከመጭው ነሃሴ 9/2012 ዓ/ም ጀምሮ ዳግም እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር!
ከነሃሴ ወር መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ #የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ለማድረግ ወላጆችን እያስገደዱ መሆኑንና ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።
የትምህርት ሚኒስቴር የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ መጨረሻ በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንማይቻልና ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።
የምዝገባው ግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተደረገው የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆችና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

#ATTENTION
ኢትዮጵያ ውስጥ የሟቾ ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,907 የላብራቶሪ ምርመራ 583 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ26 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 330 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 19,289 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 336 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 7,931 ናቸው።
ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሪቱ ውስጥ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠው 583 ሰዎች ውስጥ 386 ከአዲስ አበባ ናቸው ፤ እንዲሁም ህይወታቸው ካለፈ 26 ሰዎች 23 ከአ/አ ሲሆኑ 21 ከአስክሬን ምርመራ እና 2 ከጤና ተቋም ናቸው።

በድሬዳዋ ሃያ አንድ (21) የጤና ባለሙያዎች በሥራቸው ላይ ሳሉ በኮሮና መያዛቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ አስታውቋል።
በድሬዳዋ በኮሮና ከተያዙ መካከል 23 ታራሚዎች እና 24 የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል።
የዘጠኝ (9) አመት አዳጊን ጨምሮ ለስደት ወደ ጅቡቲ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

- በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 218 ደረሱ፤ ትላንት 79 ሰዎች ተመርምረው 5 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በኦሮሚያ ባለፉት 24 ሰዓት 81 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል 29 ሰዎች ከቦረና ናቸው። በክልሉ ትላንት የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።
- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 15 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ከነዚህ ውስጥ 11 ሰዎች ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ባቲ ከተማ ናቸው።
- በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ፤ 8 ሰዎች አገግመዋል። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ 841 ያገገሙ 497 ደርሰዋል።
- በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 37 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 162 ደርሷል።
- በሱማሌ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 707 ደርሰዋል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 2 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አይደሉም።
- በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 14 ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን አምስቱ (5) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።
- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 9 ሲሆኑ 3 ከኮንሶ፣ 3 ከደ/ኦሞ፣ 2 ከወላይታና 1 ከስልጤ ዞን ናቸው። በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ 210 ደርሰዋል።

የኦሮሚያ ውሎ!
በማህበራዊ ሚዲያ ከዛሬ ጀምሮ መንገድ እንደሚዘጋ እና እንቅስቃሴ እንደማይኖር ጥሪ ሲደረግ ነበር።
ዛሬ ከሀዋሳ/ሞጆ/አዳማ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ አድርገናል ያሉ የቲክቫህ አባላት መንገዱ ክፍት እንደነበርና በሰላም ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልፀዋል።
አንድ የመቂ ከተማ ነዋሪ ለ BBC እንደተናገረው ዛሬ የሰኞ ገበያ እንደነበር፣ መኪናም ሲንቀሳቀስ እንደነበር፣ የፀጥታ ኃይሎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ነገር ግን ከትንንሽ መኪናዎች ውጭ ሀገር አቋራጭ የጭነት መኪናዎች እምብዛም እየታዩ እንዳልነበር ገልጿል።
በሌላ በኩል አንድ የመተሃራ ነዋሪ ለ BBC እንደተናገረው በመተሃራና ፈንታሌ ወረዳ መኪና የሚያልፍበት መንገድ አልነበረም፤ ከተማ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ባጃጆች ውጭ ምንም እንቅስቃሴ አልነበረም፤ ከጅቡቲ የሚመጣው ዋናው መንገድና ከአ/አ ወደ መተሃራ የሚያስገባው መንገድ ዝግ ነበር ብሏል።
የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጅብሪል መሃመድ የዛሬው የክልሉ ውሎ ከቀድሞው የተለየ እንዳልነበረ ተናገረዋል።
ወደ ሰሜን የሚሄደው ፣ ወደ ምዕራብ የሚሄደው ፣ ወደ ደቡብና ምስራቅ የሚሄደው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳልተቋረጠና የንግድ እንቅስቃሴ ወደወትሮው እንደነበር ገልፀዋል።
አቶ ጅብሪል 'በሳይኮሎጂ ምክንያት ቀድሞ ከነበረው ልምድ አንፃር ከቀጠና ቀጠና የመቀዛቀዝ ነገር ሊኖር ይችላል' ብለዋል ፤ ከዚህ ውጭ ግን በየትኛውም ቀበሌ ፣ ወረዳ ፣ ከክልል ክልል መኪና ሳይጓጓዝ ፣ ከከተማ ከተማ እንቅስቃሴ ሳይደረግ የዋለበት አንድም ከተማ ይቅርና የገጠር ቀበሌ እንዳልነበር አስረግጠው ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ቲክቫህ አባላት እናተም የተመለከታችሁትን እና ያያችሁትን ማጋራት ትችላላችሁ @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia

እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ከኮቪድ-19 እንጠብቅ!
አስከፊውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመግታት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ #ዋነኛው የመከላከያ መንገድ ነው።
የበሽታው ስርጭት ፦
- ሠዎች እርስ በእርስ ባላቸው ቅርበት
- አብረው በሚያሳልፋበት ጊዜ
- በሚያደርጉት የሰው ንክኪ ቁጥር ይወሰናል።
#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አስከፊውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመግታት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ #ዋነኛው የመከላከያ መንገድ ነው።
የበሽታው ስርጭት ፦
- ሠዎች እርስ በእርስ ባላቸው ቅርበት
- አብረው በሚያሳልፋበት ጊዜ
- በሚያደርጉት የሰው ንክኪ ቁጥር ይወሰናል።
#CARD #TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
ኮቪድ-19 በወለጋ እና አምቦ!
በኮቪድ-19 ተይዘው በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ላይ ከነበሩ ሰማንያ ስምንት (88) የኮሮና ቫይረስ ህሙማን ሰባቱ (7) አገግመው መውጣታቸውን ሆስፒታሉ ለቪኦኤ አስታውቋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በጉደር የመጀመሪያ ሆስፒታል ውስጥ ከነበሩ ሰላሳ ስምንት (38) የኮቪድ-19 ተጋላጮች አሥራ ሦስቱ (13) እንዳገገሙ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ገልጿል።
በኮቪድ-19 ተይዘው ከነበሩና አገግመው ከወጡት መካከል በኅብረተሰቡ ውስጥ ይታያል የሚሉት “መዘናጋት ካልተወገደ ወረርሽኙ ብዙ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል” ብለዋል - #ቪኦኤ

ጤና ይስጥልን!
ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም ነው። የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚሰሙ መረጃዎች እየተለዋወጥን እንቆያለን።
እኛ ከሀገራችን ከ10ሩ ክልሎች እና 2ቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከውጭ ሀገራት የምንሰማቸውን ጉዳዮችን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እያሰባሰብን እናስቀምጣል።
እናተም እንደከዚህ ቀደሙ በየአካባቢያችሁ ያሉ ጉዳዮችን በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ለሚገኙ የቲክቫህ አባላት በማስረጃ ፣ በፎቶ፣ በቪድዮ እያስደገፋችሁ መረጃዎቻችሁን ፣ ቅሬታችሁን ፣ ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
ስፖርታዊ ጉድዮች ላይ ተሳትፎ ለማድረግ እና መረጃዎችን እርስ በእርስ መለዋወጥ የምትፈልጉ የቲክቫህ ኢትጵያ አባላት ደግሞ @tikvahethsport መቀላቀል ትችላላችሁ።
መልካም ቀን ይሁንልን!
ሐምሌ 28/2012 ዓ/ም

የዕለቱ መልዕክት ከዶክተር ኃይለልዑል መኮንን!
በዓለማችን ብሎም በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ባልተጠበቀ ሁኔታ እያሻቀበ እና በአሳሳቢነቱ እየቀጠለ ይገኛል።
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ አሀዝ መጨመሩን ተከትሎ በህዝቡ ዘንድ ትኩረት ማጣቱ የማይካድ ሀቅ ነው።
በደጉ ጊዜ ማለትም ከወራት በፊት በቀን ውስጥ በቁጥር ከ 10 ሰዎች በታች በቫይረሱ ሲለከፉ ፤ አንድ ወይም ሁለት የሞት ዜናዎች በ 24 ሰዓታት ውስጥ ሲመዘገብ የነበረን ጥንቃቄ እና ፍርሃት አሁን ላይ በአንድ ቀን ብቻ 700 እና 1000 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከመጤፍ አለመቁጠራችን አሳሳቢ እንዲሁም አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ እንዳለን ያሳያል።
መንግስት፣ የሚዲያአካላት፣ ህብረተሰቡ፣ እያንዳንዱ ሰዉ እንደግለሰብ ትኩረታችንን ከበሽታው ላይ አንስተን ወደ ቀድሞው ህይወታችን ተመልሰናል።
ቸልተኝነት ፣ መዘናጋት እንዲሁም የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ነገን እንዳናስብ እና የዛሬን ብቻ እንድንኖር አስገድዶናል። ለነገ ፈጣሪ ያዉቃል ማለቱ ብልህነት ቢሆንም የዛሬ ሰዉ ብቻ መሆንም የራስን ሀላፊነት መሸሽ ነዉ።
ይሄ በሽታ ቀስ በቀስ የምንወዳቸውን እና የምናዉቃቸዉን ወገኖቻችንን ሳያሳጣን መጠንቅ እና ማስተዋሉ ብልህነት ነዉ።
ቤታችን እስኪንኳኳና የምንወዳቸውን ሰዎች እስኪነጥቀን አንጠብቅ ፤ ካለተጠነቀቅን የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሁላችንም ቤት መንኳኳቱ አይቀሬ ነዉ። ስለዚህ የዛሬ ጥንቃቄ ለነገ ህልውናችን ዋስትና ነውና እንጠንቀቅ ፤ እናስተውል።
ትላንት ፣ ዛሬም ምናልባት ወደፊትም መፍትሔዉ መጠንቀቅ ብቻ ነዉ። ነገን ስናስብ ዛሬን በመጠንቀቅ እና በማስተዋል ይሁን።

#GERD
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ህዝቡ 13 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማስታወቁን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ዘንድሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከ745 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡም ተሰምቷል።
ከ13 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ውስጥ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከዲያስፖራ የተገኘ ሲሆን ቀሪው ከሀገር ውስጥ በስጦታ፣ በቦንድ ግዥና በ8100 አጭር መልዕክት የተገኘ ነው።

#COVID19
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሚገኝበት አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱትን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ለሰራተኞቹና ለተገልጋዮች በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቷል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በሶስቱም (3) ካምፓሶች (ገንደባ ፣ ኦቶና እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓሶች) ወደ ግቢ የሚገቡ ሰራተኞችም ሆኑ ማንኛውም ተገልጋዬች የአፍና የአፍንጫ ጭንብል (mask) ሳያደርጉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባትም ሆነ መውጣት እንደማይችሉ ገልጿል።
እንዲሁም ማንኛውም የተቋሙ ሰራተኛም ሆነ ተገልጋይ በመግቢው አካባቢዎች በሚገኙ የንጽህና መጠበቂያዎች እጁን ሳይታጠብ አገልግሎት መስጠት/ማግኘት አይችልም ተብሏል።
ከዚህ ተጨማሪም ማንኛውም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛም ሆነ ተገልጋይ በፍተሻ ጣቢያዎች በሙቀት መለኪያ መሳሪያ ሙቀቱን ሳይለካ ወደ ግቢ መግባት እንደማይችል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ አሳስበዋል።