የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ!
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል።
ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡
ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል https://telegra.ph/MoHEthiopia-06-24
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#COVID19AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 3,203 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 98 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው 11 ሰዎች ፣ 5 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የቀሩት 82 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መንግስት በኮቪድ-19 ዙሪያ እርምጃዎችን እያላላ ነው ?
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት በቅርቡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያው ላይ የተደረጉት ማሻሻያዎች መንግስት በኮቪድ-19 ዙሪያ እርምጃዎችን እያላላ ነው የሚል #የተሳሳተ ግንዛቤ በማህበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ማሻሻያዎቹ የተደረጉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙ #እየጨመረ በመምጣቱ መንግስት ያለውን ውስን ሃብት የት ላይ ማፍሰስ አለበት የሚል ለወረርሽኙ ምላሽ የስትራቴጂክ ለውጥ አስፈላጊ በመሆኑና ይበልጥ ለወረርሽኙ ጠንከር ያለ ምላሽ ለመስጠት የተደረጉ እንጂ እርምጃዎችን የማላለት እቅድ እንደሌለ አስገንዝበዋል።

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ 100 ቀናቶች!
#EPHI እና #MoHEthiopia ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ላለፉት 100 ቀናት (ከመጋቢት 4-ሰኔ 14) መጠነ ሰፊ የሆኑና በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።
የተሰሩ ስራዎችን እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦
- 216,328 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)
- 4,532 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)
- ንክኪ ያላቸው 31,573 ሰዎች ተለይተው 708 ሰዎች የኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል
- ለ764,948 ተጓዦች ልየታ እና ክትትል ተደርጓል (ከጥር 15 ጀምሮ)
- 32 ሚሊዮን ሰዎች በቤት ለቤት ዳሰሳ ታይተዋል
- 13,859 የማከምያ አልጋዎች ተዘጋጅተዋል
- ከ4,500 በላይ ተጨማሪ የጤና ባለሞያዎች ተቀጥረዋል፤ 12,000 በጎ-ፍቃደኞች ተሰማርተዋል
- 513 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግል መከላከያ ቁሳቁሶች (PPE) በሃገሪቱ ተሰራጭተዋል

#DrLaiaTadesse
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ወደ ኮቪድ- 19 ሕክምና ማዕከል በመቀየር 300 ቀላል ምልክት የሚያሳዩ እና ምንም ምልክት የሌላቸው ነገር ግን በቤታቸው ለመቆየት አመቺ ሁኔታ የሌላቸውን ታካሚዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል። ሚኒስትሯ ስራው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሳካ ላደረጉት 'የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል' ቡድን ምስጋና አቅርበዋል።

በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የሟቾች ቁጥር ከ900 አለፈ!
በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 27,628 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ906 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 11,436 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 27,628 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ906 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 11,436 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ በአፍሪካ!
በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ክትባት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊካሄድ እንደሆነ ይፋ ተደረገ።
ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው ሲል #BBC አስነብቧል።
ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን የኮሮናቫይረስን የሚያስከትለውን ሳርስ-ኮቪ-2 የተባለውን ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው።
በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ይህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ የዊትስ ዩኒቨርስቲ ከዩናይትድ ኪንግደሙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እና ኦክስፎርድ ጀነር ኢነስቲቲዩት ከተባሉ ተቋማት ጋር የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

#DrLiaTadesse
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,775 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንድ እና 138 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ3 ወር - 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 184 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።
160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ሰዎች ተመላሾች እና በማቆያ የነበሩ) ፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (11 ከጤና ተቋም እና 19 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች 1,412 ደረሱ!
በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከሐረሪ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 1 ትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,412 ደርሷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#COVID19Ethiopia
- በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1 ሰው ከሸበዲኖ፣ 1 ሰው ከዳሌ፣ 1 ሰው ለዳራራ ፣ 1 ሰው ከአርቤጎና ነው።
- በኦሮሚያ ክልል 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ከሰበታ ፣ 1 ሰው ከሰንዳፋና 1 ሰው ከጉጂ ናቸው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ንክኪ ያላቸው ናቸው።
- በትግራይ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው።
- በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ከባህር ዳር ናቸው ፤ ሁለቱም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።
- በአፋር ክልል 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 72 ደረሰዋል።
- በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።
- በሐረሪ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ግለሰቡ የሱማሌ ክልል ነዋሪ ሲሆን ለህክምና ሐረር መጥቶ ናሙና የተወሰደለት ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ባሉት ምስሎች ታገኛላችሁ!