TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ - በአላማጣ!

በአላማጣ ከተማ የተከሰተውን 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ' ከትግራይ ቴሌቪዥን በወሰድነው ቪድዮ (33 MB) መመልከት ትችላላችሁ። ግርዶሹ ሲከሰት በአላማጣ ከተማ የነበረውን ክስተት በቪድዮው ላይ ተመልከቱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ' በአላማጣ ከተማ ሲከሰት በከተማው የነበረው ገፅታ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር፤ 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሹ ከ2:00:27 - 2:01:27 ድረስ ነው የቆየው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 63 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,457 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

ቫይረስ የተገኘባቸው 42 ወንድ እና 21 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ14-76 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

31 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣1 ሰው ከትግራይ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

ከዚህ በተጨማሪ በለይቶ በህክምና ማዕክል ውስጠ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አራት (74) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አንድ (91) ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ፣ 16 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1213 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ዕለታዊ መግለጫ በቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) እና በCARD ትብብር የተዘጋጀ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሲዳማ ክልል ፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በትግራይ ክልል ፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ በአማራ ክልል፣ በአፋር ክልል፣ በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ ስለተያዙት ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ከላይ ባሉት ምስሎች ተመልከቱ።

የጋምቤላ ክልል እንዲሁም የሱማሌ ክልል የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት እስካሁን በክልሎቹ ጤና ቢሮዎች ይፋ አልተደረገም።

በሲዳማ ክልል ተብሎ የተገለፀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ናሙና ምርመራው የተደረገው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 3,105 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 31 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የሉም ፣ 2 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የቀሩት 29 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋባቸው 5 ክፍለ ከተሞች የሚከተሉት ናቸው ፦

• አዲስ ከተማ - 690 ሰዎች
• ቦሌ - 450 ሰዎች
• ጉለሌ - 347 ሰዎች
• ልደታ - 319 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራንዮ - 293 ሰዎች

በሌሌች ክፍለ ከተሞች ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ከላይ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀንላችሁ ምስል መመልከት ትችላላችሁ!

አሁንም በከተማው ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑ ሁላችንም 'ከፍተኛ ጥንቃቄ' ማድረግ ይኖርብናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ - ላልይበላ!

በላልይበላ የነበረው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ በቪድዮው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር። ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሹ ከ1:59:38 - 2:00:42 ቆይቷል📹#BeleteAlemayehu

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ሰራዊታችን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገንዘቡን ፣ ህይወቱን ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ነው!" - የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethmagazine @tikvahethmagazine
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ9 ሚሊዮን አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 9,051,949 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 470,822 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 4,842,043 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው 5 ሀገራት ፦

- አሜሪካ 2,356,715 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 122,248 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 980,367 ሰዎች አገግመዋል።

- ብራዚል 1,086,990 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 50,659 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 579,226 ሰዎች አገግመዋል።

- ሩሲያ 584,680 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 8,111 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 339,711 ሰዎች አገግመዋል።

- ህንድ 426,910 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 13,703 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 237,252 ሰዎች አገግመዋል።

- ዩናይትድ ኪንግደም 304,331 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፥ 42,632 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር አልተገለፀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia