TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#InjibaraUniversity

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ4 ኮሌጆች ስር በሚገኙ 21 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸው 525 ወንድ እና 432 ሴት በድምሩ 957 ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ (የመጀመሪያ ዙር) ነው ተማሪዎችን ያስመረቀው።

በ2007 የግንባታ መሰረት ድንጋይ የተጣለው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ነው የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረው።

በዛሬው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተማሪ ወላጆች ፣ ቤተሰቦች፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ፣ አርቲስት ታማኝ በየነ፣ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT