TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#YouTube

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም!

ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው።

እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው።

የቲክቫህ ባለቤቶች ከ895,000 በላይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸውና ማንኛውም ስራ ያለእናተ እውቅና እንደማይሰራ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን።

እስካሁን በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩትዩብ፣ ትዊተር ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረጋግን አይደለም።

ምናልባት ከቴሌግራም ውጭ በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች መንቀሳቀስ እንኳን አስፈላጊ ከሆነ ለእናተ አሳውቀን የምንጀምረው እንጂ ያለእናተ እውቅና የምንሰራው ስራ አይሆንም።

በተረፈ በዩትዩብ ላይ በTIKVAH ስም ሀሰተኛ እንዲሁም ከእኛ ያልሆኑ መልዕክቶችን የሚያሰራጩትን አካላት እነማን እንደሆኑ የማጣራት ስራ እየሰራን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,757 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ አንድ (61) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 43 ወንድ እና 18 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 48 ሰዎች ከአዲስ አበባ (5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 43 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና በዱብቲ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለውና በደሴ ለይቶ ማቆያ ያሉ)፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ያሉ) እንዲሁም 2 ሰዎች ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ሲሆኑ የቡራዩና የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 11

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 5

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 45

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 23 ሰዎች (14 ከአዲስ አበባና 9 ሰዎች ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃምሳ አንድ (151) ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት:-

– ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን፣

– ከ2008 - 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶች እና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈትሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ ተወያይቷል።

የታክስ መሰረትን በማስፋትም በተለይም ማዘጋጃ ቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና የአስራ በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ ተወስኗል።

#MayorOfficeOfAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአራት (4) ተከታታይ ቀናት #ብቻ ሰባ ስምንት (78) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ግንቦት 12/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች
• ግንቦት 13/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 14/2012 ዓ/ም - አስራ ስምንት (18) ሰዎች
• ግንቦት 15/2012 ዓ/ም - አርባ ስምንት (48) ሰዎች

አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዘቸው የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ #የሌላቸው ናቸው።

መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፤ ጥንቃቄ ይደረግ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ፣ በተለይ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ #እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ከክልሎች ደግሞ 'ከጋምቤላ ክልል' ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 48 ሰዎች መካከል በጉለሌ ክ/ከተማ 11 ሰዎች፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 10 ሰዎች ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ 6 ሰዎች ፣ በአራዳ ክ/ከተማ 6 ሰዎች የተቀሩት ታማሚዎች ደግሞ በሌሎች ክፍለ ከተሞች እንደተገኙ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 92 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ ዘጠና ሁለት (92) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውንና ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት አድርጓል።

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 655 ደርሰዋል ፤ ስምንት (8) ሰዎች ሞተዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ስድስት (6) ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#YouTube ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም! ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው። እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው። የቲክቫህ ባለቤቶች…
#YouTube

ዩትዩብ ላይ በTIKVAH-ETH ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት አጠቃላይ መረጃዎችን ከገፁ ላይ አጥፍተውታል ፤ በተጨማሪ ስሙን ከTIKVAH-ETH ወደ "Hagere Ethiopia ሀገሬ ኢትዮጵያ" ቀይረውታል።

በTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ስም የዩትዩብ ገፅ ከፍተው ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩት አካላት ላይ አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም ያሰራጯቸውን ሀሰተስኛና ሰዎችን ሚያሸበሩ መረጃዎች ከገፃቸው ቢያጠፉም በአንድ እና በሁለት ቀን በመቶ ሺ ለሚቆጠር የዩትዩት ተጠቃሚ ደርሰዋል ፤ እኛም እኚህ አካላት ማንነታቸውን እንደደረስንበት #በህግ የምናስጠይቃቸው ይሆናል።

በድጋሚ #ለማስታወስ TIKVAH-ETHIOPIA ዩትዩብ ላይ ምንም አይነት ቻናል #የለውም። አሁንም በቲክቫህ ስም ዩትዩብ ቻናል ከፍተው #ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዒድ ሙባረክ!
عيد مبارك

እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ውድ ቤተሰቦቻችን በዓሉን ስናከብር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምንወስዳቸውን አስፈላጊ #የጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰድን እንዲሆን አደራ ለማለት እንወዳለን!


عيد مبارك
መልካም በዓል ይሁንልን!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 256 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በሱዳን ተጨማሪ 256 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሲያዙ ዘጠኝ (9) ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል 52 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ተገልጿል።

ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,628 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 146 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 424 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውሃን ላብራቶሪ ኮቪድ-19 ከማዕከሉ እንዳልወጣ አስታወቀ!

የቫይረሱ መነሻ ናት በምትባለው የቻይናዋ "ውሃን ከተማ" የሚገኘው በቫይረስ ላይ ምርምር የሚያደርገው ተቋም ዳይሬክተር ሶስት አይነት የኮሮና ቫይረስ አይነቶች በሌሊት ወፍ ላይ በማዕከሉ ውስጥ ቢገኙም፤ በአሁኑ ሰዓት የአለም ስጋት ከሆነው ኮቪድ- 19 ጋር ግን አንድ አይነት አይደለም ብለዋል።

ዳይሬክተሯ ዋንግ ያኒ ከሃገሪቱ ሚዲያ ሲጂቲኤን (CGTN) ጋር ባደረጉት ቃለ - መጠይቅ በአሁኑ ወቅት አለምን ያጥለቀለቀው የኮሮናቫይረስ እርሳቸው ከሚመሩት ተቋም ወጥቷል መባሉን አጣጥለውታል።

"ይሄ የተፈበረከ መረጃ ነው" ያሉት ዳይሬክተሯ "ተቋማቸው ታህሳስ 20፣ 2012 ዓ.ም ያልታወቀ አይነት የሳንባ ምች ናሙና መድረሱን ያስታውሳሉ።

"ናሙናውን ከተመረመረ በኋላ አዲስ አይነት ኮሮና ቫይረስ እንደተያዘ ተረዳን" የሚሉት ዋንግ ያኒ "ከዚያ በፊትም ቫይረሱን በምርምራችን አላገኘነውም። በማዕከላችንም ውስጥ የዚህ አይነት ቫይረስ አልነበረም፤ አሁን ካለውም ጋር አይመሳሰልም" ብለዋል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ብራዚል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በተያዙ ሰዎች ብዛት ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛዋ (2) ሀገር ሆናለች። ባለፉት 24 ሰዓት 16,508 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 965 ሰዎች ሞተዋል።

ሶስቱ (3) ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው ሀገራት ፦

- አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ 1,666,829፣ ሞት 98,683 ፣ ያገገሙ 446,927

- ብራዚል በቫይረሱ የተያዙ 349,113 ፣ ሞት 22,165 ፣ ያገገሙ 142,587

- ሩሲያ በቫይረሱ የተያዙ 344,481 ፣ ሞት 3,541 ፣ ያገገሙ 113,299

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በአለማችን እንዲሁም በሃገራችን በተጋረጠው ወረርሽኝ ምክንያት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ከሌላው ጊዜ በተለየ 'የኢድ ሰላትን' በየቤታችሁ ሆናችሁ በመስገድ ብታከብሩም ሁላችንም ተባብረን የበኩላችንን አስተዋፅኦ ካደረግን በሽታውን ለመቆጣጠርና ወደቀድሞ ህይወታችን ለመመለስ እንደምንችልና እንደወትሮው ተሰባስበንና በጋራ ማዕድ ተቋድሰን እንደምናከብር ተስፋ አለኝ፡፡

በዓሉን በስራ ለምታሳልፉ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ለማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጪዎች ከልቤ እያመሰገንኩኝ ሁላችንም እራሳችንን፣ ቤተሰባችን እና ማህበረሰባችንን የመጠበቅ ሃላፊነት አጠናክረን እንድንቀጥል እጠይቃለሁ::
መልካም የኢድ አል ፈጥር በዓል።

ኢድ ሙባረክ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 88 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,048 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ስምንት (88) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 51 ወንድ እና 37 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ8 እስከ 75 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ሰዎች ከአዲስ አበባ (19 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለውና 53 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 8 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው) ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሲሆን ነዋሪነታቸው አምቦ፣ ቡራዩ፣ ሰንዳፋና ሞጆ ከተሞች ነው)፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት) ፣ እንዲሁም 2 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 13

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 20

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 55

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው (ከኦሮሚያ ክልል) ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 152 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል መረጃና ጥቆማ አገልግሎት እንዲውል ባዘጋጀው ነጻ የጥሪ ማዕከል 6406 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

ለሚፈለገው ዓላማ ብቻ ደውሉ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 3 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል እንዲሁም የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,214 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ51 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 383 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአምስት (5) ተከታታይ ቀናት #ብቻ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ (151) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ግንቦት 12/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች
• ግንቦት 13/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 14/2012 ዓ/ም - አስራ ስምንት (18) ሰዎች
• ግንቦት 15/2012 ዓ/ም - አርባ ስምንት (48) ሰዎች
• ግንቦት 16/2012 ዓ/ም - ሰባ ሶስት (73) ሰዎች

አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዘቸው የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር 'ንክኪ የሌላቸው' ናቸው።

ይህ ከፍተኛ የሆነ ኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም። የክልል ከተሞች ነዋሪዎች የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም #ባለመቋረጡ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

አስገዳጅ ካልሆነ ከቤት አትውጡ!

ከቤት ምትወጡበት አስገዳጅ ምክንያት ካለ ደግሞ ሰዎች ሚሰባሰበሰቡበት ቦታ በፍፁም አትገኙ ፣ ከሰዎች ጋር አትጨባበጡ ፣ በስራ ቦታችሁ ሳትዘናጉ ጥንቃቄ አድርጉ ፣ የእጃችሁን ንፅህና ጠብቁ ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ያድርጉ!

መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፤ ጥንቃቄ ይደረግ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse #DrAbiyAhemed

በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች!

በኮሮና ቫይረስ ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ኢትዮጵያዊት ነብሰ ጡር እናት በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም በሆስፒታሉ ዛሬ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተዋል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች። "በአሁኑ ወቅትም ህጻኑና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ባለው በዚሁ ሆስፒታል ዛሬ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia