TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ…
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ!

የአማራ ክልል 'የምዕራብ ጎንደር ዞን' ማህበራዊ ልማት መምሪያ በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር #አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ቫይረስ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችል አስታውቋል።

የአማራ ክልል ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100 እስከ 150 ሰዎች ድንበር #አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።

ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም።

የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል።

በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ችግሩ 'ከአቅም በላይ' እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ #ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ከሱዳንና ከጅቡቲ አካባቢዎች ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከፌደራል መንግስት ጋር በጋራ የምንፈታው ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 105,100 ደረሱ። ከነዚህ መካከል 3,185 ሰዎች ሲሞቱ 42,643 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 20,185፣ ሞት 397 ፣ ያገገሙ 10,104

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 15,786 ፣ ሞት 707 ፣ ያገገሙ 4,374

- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 7,918 ፣ ሞት 582 ፣ ያገገሙ 4,256

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ኮሮና ቫይረስ ጠፍቷል፤ ውጡና ጨፍሩ' - ፖል ማኮንዳ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የታንዛኒያው ነባር ፖለቲከኛ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጠፍቷል' ማለታቸውን ተከትሎ ከሃገሬው ሰው ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው። ፖለቲከኛው ይባስ ብለው ታንዛኒያውያን እሁድ ዕለት ወደ አደባባይ ወጥታችሁ የኮሮና ቫይረስ መጥፋትን አክብሩ ብለዋል።

የዳሬሳላም ኮሚሽነር ፖል ማኮንዳ የታንዛኒያ ዜጎች አዲስ ልብስ ገዝተው ደስታቸውን ቢገልፁ በበሽታው ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ይደግፋሉ ብለዋል።

ታንዛኒያ ወስጥ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስለመጥፋቱ ምንም #ማረጋገጫ የለም። የታንዛኒያ ጤና ሚኒስቴር ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መግለጫ ከሰጠ አንድ (1) ወር አልፎታል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ስፔን ሪፖርት ያደረገችው 688 ሞት!

ከባለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ ስፔን ሪፖርት እያደረገችው ያለው ከ100 በታች የሟቾች ቁጥር በብዙሃን ላይ ትልቅ ተስፋን አሳድሯል።

ዛሬ ግን ሪፖርት በተደረገው የ688 የሟቾች ቁጥር እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ ? በሚል ብዙ ሰዎችን አስደንግጧል።

በስፔን በ24 ሰዓት የሞቱ ሰዎች 56 ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከካታላን ሪፖርት ያልተደረገ 632 የሟቾች ቁጥር ነበር። ይህ በመደመሩና ሪፖርት በመደረጉ ነው ቁጥሩ ከፍ ያለው።

በአጠቃላይ በስፔን 281,904 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ መካከል 28,628 ሰዎች ሞተዋል። 196,958 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ስንል እንጠንቀቅ!

(በዶክተር ፅዮን ፍሬው - ከኒው ዮርክ ሆስፒታል)

በልጅነታችን ግዜ በኤች አይ ቪ ማስታወቃያውች “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ይል ነበር። አሁንም በበሽታው የተጠቃው ሰው እየጨመረ ሲመጣ ከመደንገጥ #መጠንቀቅ

አንዳንዶቻችን ቢይዘኝም አይገለኝም የሚለውን አስተሳሰብ ትተን ለኛ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን ማሰብ አለብን። በተለይም ለእናት ለአባት እና ለአያቶቻችን የሞት መንስኤ ላለመሆን።

አሁን ደሞ በኒው ዮርክ አንዳንድ ህፃናት ልጆች ላይ የሚያመጣው የከፋ ህመም እያየን ነው። ለነሱም ስንል እንጠንቀቅ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 235 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በሱዳን ተጨማሪ 235 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ አስራ ስድስት (16) ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል 63 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ተገልጿል።

ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3378 (ካርቱም ግዛት 2748) የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 137 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 372 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UhuruKenyatta

በኬንያ ተጨማሪ ሰላሳ አንድ (31) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናገርዋል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,192 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#LatinAmerica

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ላቲን አሜሪካ አዲሷ የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ወረርሽኝ #ማዕከል መሆኗን አሳውቋል - #AFP

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብራዚል!

ብራዚል ከአሜሪካ እና ከሩሲያ ቀጥላ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ታማሚ የተመዘገበባት ሀገር ሆናለች። በአጠቃላይ በሀገሪቱ 332,882 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ሶስቱ (3) ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው ሀገራት ፦

- አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ 1,645,353 ፣ ሞት 97,655 ፣ ያገገሙ 403,228

- ሩሲያ በቫይረሱ የተያዙ 335,882 ፣ ሞት 3,388 ፣ ያገገሙ 107,936

- ብራዚል በቫይረሱ የተያዙ 332,382 ፣ ሞት 21,116 ፣ ያገገሙ 135,430

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#YouTube

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም!

ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው።

እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው።

የቲክቫህ ባለቤቶች ከ895,000 በላይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸውና ማንኛውም ስራ ያለእናተ እውቅና እንደማይሰራ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን።

እስካሁን በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩትዩብ፣ ትዊተር ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረጋግን አይደለም።

ምናልባት ከቴሌግራም ውጭ በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች መንቀሳቀስ እንኳን አስፈላጊ ከሆነ ለእናተ አሳውቀን የምንጀምረው እንጂ ያለእናተ እውቅና የምንሰራው ስራ አይሆንም።

በተረፈ በዩትዩብ ላይ በTIKVAH ስም ሀሰተኛ እንዲሁም ከእኛ ያልሆኑ መልዕክቶችን የሚያሰራጩትን አካላት እነማን እንደሆኑ የማጣራት ስራ እየሰራን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,757 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ አንድ (61) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 43 ወንድ እና 18 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 48 ሰዎች ከአዲስ አበባ (5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 43 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና በዱብቲ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለውና በደሴ ለይቶ ማቆያ ያሉ)፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ያሉ) እንዲሁም 2 ሰዎች ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ሲሆኑ የቡራዩና የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 11

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 5

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 45

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 23 ሰዎች (14 ከአዲስ አበባና 9 ሰዎች ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃምሳ አንድ (151) ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት:-

– ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን፣

– ከ2008 - 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶች እና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈትሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ ተወያይቷል።

የታክስ መሰረትን በማስፋትም በተለይም ማዘጋጃ ቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና የአስራ በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ ተወስኗል።

#MayorOfficeOfAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ስርጭት በአዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአራት (4) ተከታታይ ቀናት #ብቻ ሰባ ስምንት (78) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ግንቦት 12/2012 ዓ/ም - ዘጠኝ (9) ሰዎች
• ግንቦት 13/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 14/2012 ዓ/ም - አስራ ስምንት (18) ሰዎች
• ግንቦት 15/2012 ዓ/ም - አርባ ስምንት (48) ሰዎች

አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዘቸው የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ #የሌላቸው ናቸው።

መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፤ ጥንቃቄ ይደረግ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ፣ በተለይ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ #እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ከክልሎች ደግሞ 'ከጋምቤላ ክልል' ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 48 ሰዎች መካከል በጉለሌ ክ/ከተማ 11 ሰዎች፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 10 ሰዎች ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ 6 ሰዎች ፣ በአራዳ ክ/ከተማ 6 ሰዎች የተቀሩት ታማሚዎች ደግሞ በሌሎች ክፍለ ከተሞች እንደተገኙ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 92 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ ዘጠና ሁለት (92) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውንና ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውን ሪፖርት አድርጓል።

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 655 ደርሰዋል ፤ ስምንት (8) ሰዎች ሞተዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ስድስት (6) ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#YouTube ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም! ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው። እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው። የቲክቫህ ባለቤቶች…
#YouTube

ዩትዩብ ላይ በTIKVAH-ETH ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት አጠቃላይ መረጃዎችን ከገፁ ላይ አጥፍተውታል ፤ በተጨማሪ ስሙን ከTIKVAH-ETH ወደ "Hagere Ethiopia ሀገሬ ኢትዮጵያ" ቀይረውታል።

በTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ስም የዩትዩብ ገፅ ከፍተው ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩት አካላት ላይ አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም ያሰራጯቸውን ሀሰተስኛና ሰዎችን ሚያሸበሩ መረጃዎች ከገፃቸው ቢያጠፉም በአንድ እና በሁለት ቀን በመቶ ሺ ለሚቆጠር የዩትዩት ተጠቃሚ ደርሰዋል ፤ እኛም እኚህ አካላት ማንነታቸውን እንደደረስንበት #በህግ የምናስጠይቃቸው ይሆናል።

በድጋሚ #ለማስታወስ TIKVAH-ETHIOPIA ዩትዩብ ላይ ምንም አይነት ቻናል #የለውም። አሁንም በቲክቫህ ስም ዩትዩብ ቻናል ከፍተው #ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዒድ ሙባረክ!
عيد مبارك

እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ውድ ቤተሰቦቻችን በዓሉን ስናከብር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምንወስዳቸውን አስፈላጊ #የጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰድን እንዲሆን አደራ ለማለት እንወዳለን!


عيد مبارك
መልካም በዓል ይሁንልን!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 256 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በሱዳን ተጨማሪ 256 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሲያዙ ዘጠኝ (9) ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል 52 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ተገልጿል።

ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,628 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 146 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 424 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia