TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሱዳን ተጨማሪ 100 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 100 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 9 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

ከካርቱም ግዛት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 8 ሰዎች ከሰሜናዊ ኮርዶፋ እንደሁም የተቀሩት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መያዛቸዉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 778 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 45 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 70 ሰዎች ማገገማቸዉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ በአንድ ቀን 79 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 79 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 835 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስራ አራት (14) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት (3) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰላሳ አምስት (35) ደርሷል።

በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 38 ከፍ ብሏል ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

የአዳማ ጀነራል ሆስፒታል እና የህክምና ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ባለቤት የሆኑት አቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል፡፡

አቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ ብዙዎች በማይደፍሩት የጤና ዘርፍ ላይ ኃብታቸውን አውጥተው በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሚባለውን ሆስፒታል ሰርተው ለህብረተሰቡ እስካሁን ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

"በኤካ ኮተቤ የኮሮና ህክምና ማዕከል በመገኘት ባደረግነው ጉብኝት የአገልግሎት አሰጣጡ በእጅጉ መሻሻሉን ማየት ችለናል። በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ያገገሙ ህመምተኞችን ማግኘቴና ባገኙት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን መስማቴ አስደሳች ነበር።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ185 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 25,613 ደርሷል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ71,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.2 ሚሊዮን በልጧል።

- በኳታር በአንድ ቀን 951 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል (እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው) ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከ17,000 በላይ ሆኗል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 1,075 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ የ236 ሰዎች ሞትም ተመዝግቧል።

- በኢራን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ወደ 100,000 እየተጠጋ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ1,323 ሰዎች ኬዝ በመመዝገቡ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 99,970 ደርሷል።

- በፈረንሳይ በአንድ ቀን የ330 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል ፤ ከሚያዚያ 21 በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

- በUK በአንድ ቀን 693 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 29,427 ደርሷል፤ UK ጣልያንን በመብለጥ ከአውሮፓ ቀዳሚዋ ሆናለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE (ሀላባ ዞን አስተዳደር) በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸው ግለሰቦችን በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡ በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 25/2012 ዓ/ም) በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንኪኪ እንደነበራቸው የተጠረጠሩ እስካሁን 40 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ…
#UPDATE

(ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር)

በሞያሌ የአስገዳጅ ማቆያ የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎለት #ፖዘቲቭ መሆኑ የተረጋገጠና ከእሱ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 7 ተጠርጣሪዎች ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የተደረገ መሆኑ ይታወሳል።

ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የ3ቱ የምርመራ ውጤት #ኔጌቲቭ ሆኗል። የተጠርጣሪዎቹ የናሙና ውጤት በአሁኑ ምርመራ ኔጌቲቭ ቢሆንም የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን ዝቅተኛውን ስታንዳርድ 14 ቀን መጠበቁ የግድ በመሆኑ 14 ቀን እስኪሆናቸው ድረስ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ይቆያሉ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የከተማው ነዋሪ በዚህ መልካም ዜና #ሳይዘናጋ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ ኃላፊነት በተሞላ መልኩ የመከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ ተጨማሪ 4 ሰዎች አገግሙ!

በኤርትራ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 4 ሰዎች ከኮቪድ-19 ማገገማቸው ተገልጿል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 30 ደርሷል። በሀገሪቱ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች 39 ናቸው።

ምንጭ፦ የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,120 ፣ ሞት 2 ፣ ያገገሙ 745

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 535 ፣ ሞት 24 ፣ ያገገሙ 182

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 835 ፣ ሞት 38 ፣ ያገገሙ 75

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 778 ፣ ሞት 45 ፣ ያገገሙ 70

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 145 ፣ ሞት 4 ፣ ያገገሙ 91

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 52 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 30

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ)

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ የኒቨርሲቲ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከነበሩትት ውስጥ ለ83 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ነፃ በመሆናቸው ወደ መጡበት አከባቢ መመለሳቸውን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገልጿል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 263 ሰዎች በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአስገዳጅ ማቆያ ገብተው እንደነበር ነው የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ያስታወቀው።

በዩኒቨርሲቲው አስገዳጅ ማቆያ ከነበሩት ውስጥ 87 ሴቶች ፣ 176 ወንዶች ፣ 30 ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናት እና 1 ነፍሰ-ጡር እናት ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 150 ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ 133 ደግሞ ሱዳናውያን መሆናቸው ተገልጿል።

በአስገዳጅ ማቆያ ከነበሩትት ውስጥ ለ83 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ በመሆናቸው ወደ መጡበት አከባቢ መመለሳቸውን ቢሮ አስታውቋል።

እስከ ትናትና 12:00 ሰዓት ባለዉ መረጃ በአስገዳጅ ማቆያው ያሉ 91 ኢትዮጵያውያን እና 90 ሱዳናውያን ስሆን የ63 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ወደ ኢትዮጵያ የህብረሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ለመላክ መዝጋጅቱን የቢሮው የህብረሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የሱማሌ ክልል ሞያሌ ወረዳ ሰራተኞች ተመርመሮ ኮሮና ቫይረስ እንደያዘው የታወቀን ግለሰብ ከለይቶ ማቆያ መልቀቃቸው አግባብ አይደለም ሲሉ የቦረና ዞን የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ተችተዋል።

ግለሰቡ የምርመራ ውጤቱ ከተላከበት ሳይመለስ ተለቋል ሲሉ የቦረና ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሮባ ዴንጌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የሱማሌ ክልል የሞያሌ ወረዳ የጤና ክትትል ኃላፊ ግለሰቡ የተለቀቀው #በስህተት ነው ሲሉ ምላሻቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ልጆቹ በስህተት ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም!" - አቶ አይዛክ ሀሰን (የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ)

(በአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

ከሞያሌ ለይቶ ማቆያ የተለቀቀው ግለሰብ ከወር በፊት ነበር ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው። በቦረና ዞን የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ባልደረባ አቶ አብዱዋ ዋቆ ግለሰቡን ከሌሎች 40 ሰዎች ጋር ወደ ለይቶ ማቆያ ያስገቡት የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ናቸው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ያኔ ከገቡት 40 ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ ቢሆንም የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ውጤቱ ሳይመለስ ሰዎቹን ለሳምንታት አቆይተዋቸው አርብ ዕለት ወደ ሀዋሳ እንደመለሷቸው ተናግረዋል።

የቦረና ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሮባ ዴንጌ ሰዎቹ የተሳፈሩባቸው የህዝብ አውቶብሶች መለየታቸው፤ ያቤሎ ሲደርሱ ያረፉበት ሆቴል ፀረ ተባይ መድሃኒት መረጨቱን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አቶ ሮባ በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ወደ #ሀዋሳ ያመሩት 40 ሰዎች፣ በዞኑ የተገናኙት ሌሎች ሰዎች በሙሉ ተለይተዋል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ አቶ አይዛክ ሀሰን "ልጆቹ #ተሳስተው ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም ፤ ኳረንቲን 14 ቀን ቢሆንም ልጆቹ 18 ቀን ነበር የቆዩት ፤ ውጤቱ ስለዘገየ ነው። ልጆቹ የተለቀቁት እየታወቀ አይደለም፤ በስህተት ነው" ብለዋል።

አቶ አይዛክ አንድ ላይ ከነበሩት መካከል የ4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ መሆኑን ገልፀው አሁን ሁሉም በደቡብ ክልል በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሞያሌ በነበሩበት ወቅት 2 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እነሱን ሲንከባከቡ የነበሩ አጠቃላይ 9 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንደገቡ መደረጉን አስረድተዋል።

@tikvahethiopiaBot
በአወዳይ ከተማ የቤት ለቤት ልየታ ስራ ተጀምሯል!

(ሕይወት ፋና ሆስፒታል)

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል አስተባባሪነት 40 የሚሆኑ ጠቅላላ እና ስፔሻሊስት ሐኪሞች በአወዳይ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ (Screening) ስራ ተጀምሯል።

አወዳይ ከተማን ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እና በሁሉም አቅጣጫ ሞዴል ዲስትሪክት ለማድረግ በማሰብ ነው የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ (Screening) ስራው የተጀመረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HARGEISA

በሶማሊላንድ ሁለተኛ (2) ሰው በኮቪድ-19 መሞቱ ሪፖርት ተደረገ ፤ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው ግለሰብ የሀርጌሳ ነዋሪ ሲሆኑ ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,382 ላቦራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአ/አ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 5 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 6 - የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 7 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 8 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታ አፋር (የተገኘው አ/አ) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 9 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 10 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 11 - የ53 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።

ታማሚ 12 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 13 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 14 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 15 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 16 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 17 - የ41 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ሶስት (93) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia