TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 24,088
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,758
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 60
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 75
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 140

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የውጭ አገራት የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው የኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር #እየጨመረ መሆኑ ተጠቆመ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ #ለኢዜአ እንደተናገሩት ፤ ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር "አነስተኛ ነው" በማለት እየተዘናጋ ነው።

የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መዘናጋት አይገባም ብለዋል።

በጎረቤት አገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሆኑንም ገልጸው ይህም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

ሳይንሳዊ ምርምሮችም የቫይረሱ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል እያሳዩ መሆኑን ጠቁመው ኅብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ምክራቸውን ለግሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 490 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,012 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ሀያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ዛሬ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች አስራ አምስቱ (15) ከናይሮቢ አስሩ (10) ደግሞ ከሞንባሳ ናቸው።

በአጠቃላይ በኬንያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 490 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,116 ደርሰዋል!

የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው ሪፖርት 366 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,116 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ከኮቪድ-19 የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በትላንትናው ዕለት 27 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 713 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 756 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስራ ሰባት (17) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 61 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት (3) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰላሳ አምስት (35) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያዎቹ ሁለት (2) ታማሚዎች ከኮቪድ-19 አገገሙ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ አይ ሬድዮ ባሰራጨው መረጃ ከኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መካከል የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች አገግመዋል።

ከበሽታው እንዳገገሙ የተገለፀው በህክምና ክትትል ላይ የነበሩት 'ታማሚ 3' እና 'ታማሚ 4' ናቸው ተብሏል።

በአሁን ሰዓት በደቡብ ሱዳን በአጠቃላይ አርባ (40) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረገጥ፤ ሁለት (2) ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- የሮም 'ቻምፒኖ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ' ሊከፈት እንደሆነ ተገልጿል።

- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከትላንትናው ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ195 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። 1,221 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ69,000 በላይ ሆኗል።

- በኳታር 640 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 16,191 ደርሷል።

- በጃፓን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ግንቦት 23 ተራዝሟል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት24 ሰዓት የ288 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል (ከየካቲት ወር መጨረሻ በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው) አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 28,734 ደርሷል።

- በቱርክ የሟቾች ቁጥር 3,461 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የ64 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 306 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር 250,099 ደርሷል፤ 1,170,448 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,610,189 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID_ORGANIC ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች! በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ…
#COVID_ORGANICS

በማዳጋስካሩ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆሊና የተዋወቀው እና 'የኮሮና ቫይረስ ፈውስ ነው' ለተባለው ባህላዊ መድሃኒት ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ነው፡፡

'ባህላዊ መድሃኒቱ' ከኮቪድ-19 እንደሚያድን የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊ መረጃ እንደሌለ ቢነገርም ፍላጎታቸው አልተገታም' ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

'መድሃኒቱን' ካዘዙት መካከልም መድሃኒቱን ለማምጣት ወደ ደሴቷ አገር አውሮፕላን የላኩት የታንዛኒያው ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ ይገኙበታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኮንጎ ብራዛቪል ፣ ኮንጎ ፣ ጋቦን እና ኮሞሮስ መድሃኒቱን ወደ አገራቸው የማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ ኢኳቶሪያን ጊኒ እና ጊኒ ቢሳዎም የተወሰኑ መድሃኒቶችን ለማምጣት አውሮፕላን ልከዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AndryRajoelina 

የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት ራጆሊና ሀገራቸው ባዘጋጀችው 'ፈዋሽ ነው' በተባለለት መድሃኒት ዙሪያ ከአሜሪካውያን ተመራማሪዎች ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ፈዋሽ ነው ብለው ያዘጋጁት መጠጥ ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና እንዲያገኝ እየሰሩ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ለመከላከል ተብለው በግል የሚወሰዱ መድሃኒቶችን እንደማይመክር ለቢቢሲ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

ባለፉት 24 ሰዓት በማዳጋስካር 161 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በማዳጋስካር እስካሁን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 151 ሲሆኑ 99 ሰዎች አገግመዋል (ዛሬ 1 ሰው አገግሟል) ፤ በአሁን ሰዓት የህክምና ክትትል እያደረጉ ያሉ 52 ሰዎች ናቸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ ፣ የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABABA

የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከረቡዕ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭንብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ሊደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ከረቡዕ ጀምሮ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማይጠቀሙ ተሳፋሪዎችን እንደማይጭንም ገልጿል።

በተጨማሪ የትራንስፖርት እጥረትን ለመፍታት የመጫን አቅምን ከአስገዳጅ የአፍ መሸፈኛ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወደ 43 የሚያድግ ይሆናል ተብሏል - #FBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ወሰነ!

የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሙሉ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የህዝቡን መብት ከትርምስ ለመታደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን በክልል ደረጃ ለማድረግ ዝግጅት እንዲደረግ መወሰኑን አሳውቋል፡፡

የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይህ እንቅስቃሴ የፀረ ኮረና (ኮቪድ-19) ዘመቻዎችን እንዲሁም ተቀባይነት ያላቸውን ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን ባሟላ መልኩ የሚፈፀም ይሆናልም ብሏል።

ከላይ ያለውን ውሳኔ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ የተላለፉ ውሳኔዎችን ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/TPLF-05-04

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ወቅታዊ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ ለTIKVAH-ETH የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,116፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 713

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 490፣ ሞት 24፣ ያገገሙ 173

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 756፣ ሞት 35፣ ያገገሙ 61

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 678፣ ሞት 41፣ ያገገሙ 61

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 140፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 75

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 49፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Ethiopia) #ቤተሰብ አባላት መረጃዎችን የሚለዋወጡባቸው ትክክለኛ ገፆች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ብቻ ናቸው ፦

- @TIKVAHETHMAGAZINE (ከኮቪድ-19 ውጭ ያሉ ወቅታዊ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች እየተሰባሰቡ የሚቀመጡበት) ከ 187,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ያሉበት!

- @TIKVAHETHSPORT (ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መረጃዎች እየተሰባሰቡ የሚቀመጡበት) ከ 72,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ያሉበት!

- @tikvahethAFAANOROMOO (በአፋን ኦሮሞ ወቅታዊ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች እየተሰባሰቡ የሚቀመጡበት) ከ 9,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ያሉበት!

ቲክቫህ በፌስቡክ፣ በኢንስታግራም፣ በትዊተር እና ዩትዩብ ምንም አይነት ገፆች የሉትም!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣይ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የተቀመጡ ሦስት አንቀፆች ህገመንግስታዊ ትርጓሜ እንዲሰጣቸው በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህመንግስቱ አንቀፅ 83 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምርጫውን መራዘም በተመለከተ ትርጉም የሚያስፈልጋቸውን አንቀፆች በአንድ ወር ወስጥ እንዲተረጉም ነው የወሰነው፡፡

የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የህገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቡን አስታውቀዋል።

የውሳኔ ሀሳቡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 54/1 አንቀፅ 58/3 እና አንቀፅ 93 ከህገ መንግስት አላማ እና ግቦች እንዲሁም መሰረታዊ መርሆች ጋር ለማስተሳሰር ትርጉም እንዲሰጥባቸው የሚል ህገ መንግስታዊ የመፍትሄ ሀሳብ ነው ያቀረበው።

#HPR #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኒው ዚላንድ ለሁለተኛ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ዜጋ አልተገኘም ተብሏል። ኒው ዚላንድ ጥላ የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብም እያላላች ትገኛለች - #BBC

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሪፖርት አድርጋለች። በሌላ በኩል በሀገሪቱ ለስምንተኛ ተከታታይ ቀን ሞት አልተመዘገበም።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ዝቅተኛው የሞት መጠን ተመዝግቧል፤ የሟቾች ቁጥር 1015 ሲሆን ይህም ከአንድ ወር በኋላ ዝቅተኛው ነው - #BBC

- ባለፉት 24 ሰዓት በደቡብ ኮሪያ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው (በሀገር ውስጥ ቫይረሱ ሳይገኝ ሁለት ቀን ሆኖታል)

- ካምቦዲያ ባለፉት 3 ሳምንታት በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አላደረገችም። ካምቦዲያ በቫይረሱ ከተያዙ 122 ሰዎች 120ዎቹ በፍጥነት እንዲያገግሙ በመርዳት አመርቂ ውጤት አስመዝግባለች- #BBC

- ደቡብ አፍሪካ በትላንትናው ዕለት ብቻ 437 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7,220 ደርሷል።

- ናይጄሪያ በአንድ ቀን ከፍተኛ ነው የተባለለትን በኮቪድ-19 የተያዘ የሰው ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች፤ ባለፉት 24 ሰዓት 245 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,802 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ የዓለም የእጅ ንጽህና ቀን የሚከበርበት እለት ነው!

የዓለም የእጅ ንጽህና ቀንን በማስመልከት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል ፦

''ዛሬ የዓለም የእጅ ንጽህና ቀንን ስናከብር ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል እና ኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) ጨምሮ ጀርሞች እንዳይሰራጩ ለመከላከል የእጅ ንጽህናን መጠበቅ ውጤታማ መንገድ መሆኑን ተገንዝበን የባህሪ ለውጥ በማምጣት እራሳችንን እና ሌሎችን እንጠብቅ።''

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ባስመዘገብነው ድል ሁላችንም ልንኮራ ይገባል" - ጃሲንዳ አርደን

ኒው ዚላንድ ለሁለተኛ ቀን በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዘ ዜጋ እንዳልተገኘ አሳውቃለች። ሀገሪቷ ጥላ የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብም እያላላች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚንስትር ጃኪንዳ አርደረን 'ባስመዘገብነው ድል ሁላችንም ልንኮራ ይገባል' ካሉ በኋላ የአገሪቱ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል - #ቢቢሲ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,047 ላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ #የሌላቸው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 4 - የ8 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት

ታማሚ 5 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊት የመኖሪያ ቦታ ኦሮሚያ #ባቱ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #ያላት

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት 16 ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia