TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FightCOVID19

- ሰበታ ከተማ የሚገኘው የይሔይስ አበበ የገበያ ማዕከል ለተከራዮች የ3 ወር ኪራይ ነፃ አድርጓል። በገንዘብ 600,000 ብር ይደርሳል።

- አ/አ የሚገኘው የካሳ ግራንድ ሞል ባለቤቶች በህፃቸው ላይ ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎች፣ የካፌ ባለቤቶችና ሌሎችም የ3 ወር 50% የቤት ኪራይ ቅናሽ ማድረጋቸውን አረጋግጠውልናል።

ሌሎች ቤቶቻቸውን ለመኖሪያ ቤት ያከራዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የቤት ኪራይ ክፍያን ነፃ እያደረጉ እንደሆነ እየገለፁልን ነው። በምንችለው አቅም የደረሱን እናቀርባለን። ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማቅረብ ስለማንችል ይቅርታ እንጠይቃለን!

ሁላችሁንም ለበጎ ስራችሁ እናመሰግናለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 'ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ!' በሚል ፤ የኮሮና በሽታ (COVID-19) ከሚያስከትለዉ የጤና ችግር ባለፈ ፤ በሚያመጣዉ የኢኮኖሚ ችግር ፤ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ይበልጥ እንዳይጎዱ በማሰብ በሀድያ ዞን አስተዳደር የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች መምሪያ በኩል ለተለዩ የእቅም ዉስንነት ላለባቸዉ ከ1,000 በላይ ወገኖች እገዛ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እንዲያስችሉ የላከቻቸው የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል፡፡

የሕክምና ቁሳቁሱ በእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የተገዙ ናቸው፡፡

ድጋፉ የሕክምና ማስኮች፣ የቀዶ ጥገና ጋውኖች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ሙሉ አካልን የሚሸፍኑ የሕክምና አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁስ ተካተውበታል፡፡

ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- የነቀምቴ ከተማ ወጣቶች ባለፉት ቀናት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊቸገሩ ለሚችሉ ወገኖች እገዛ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ እንደነበር አሳውቀውናል።

- በይርጋዓለም ከተማ የሆስፒታል ሰፈር ወጣቶች 'እኛ ለእኛ' በሚል ስያሜ በተቋቋመው ማህበር ከማህበሩ አባላትና ከአንዳንድ በጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ እህል እና የፅዳት መጠበቂያ ሳሙናዎችን ለአቅመ ለሌላቸው ወገኖች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- የዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር/ Dilla Town Health Sport Association ማዕዳቸውን አጋርተዋል። ዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር በየወሩ ከሚያግዛቸው ስዎች በተጨማሪ የኮረና ወረርሽኝ መግባቱ ከታወቀ በኃላ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው በድጋሚ ሁለተኛ ዙር 35 እረዳት የሌላቸውን እናትና አባቶች ድጋፍ አድርገዋል።

PHOTO : (1-ይርጋለም) (2 - ዲላ) (3- ነቀምቴ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- በወልቂጤ ከተማ የሚገኘውን የቁርአን ትምህርት ቤትና በጉብሬ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ኤዋን ህንፃ የኮሮና ቫይረስ የሚጠረጠሩ ሰዎች ቢገኙ ለለይቶ ማቆያ እንዲሆን የእስልምና እምነት አባቶች ለከንቲባው አስረክበዋል። ህንፃዎቹ ከ90 በላይ ሠዎችን የማስተናገድ አቅም አላቸው።

- በምዕራብ ናዝሬት መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች፣ አገልጋዮች እና ምዕመናን ከ120 ለሚበልጡ ቤተሠቦች እገዛ አድርገዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FightCOVID19

- የድሬ ከተማ ተጫዋቾች ከዚህ በፊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን በኮሮና ወረርሽኝን ምክንያት ለሚጎዱ ህብረተሰብ ድጋፍ አድርገዋል። አሁን ደግሞ ቢኒያም ታደሰ እና ሻፊ አብዱረዛቅ የተባሉ የክለቡ ደጋፊዎች ማህበር አባል የሆኑት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር አቅመ ደካማ የሆኑ ህብረተሰብን ለሁለት ሳምንት እየመገቡ ይገኛሉ።

- የሀና መውጫ ወጣቶች ማህበረሰቡን በማስተባበር ለ50 አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የበአል ስጦታ(እቁላልና ዶሮ)፣ እንዲሁም የተለያዩ የምግብ ግብአቶችንና የንፅህ መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድረገዋል።

- የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፖ የሴቶች ኮንዶሚኒዬም ነዋሪ መምህራንና ሰራተኞች ከዚህ በፊት የትምህርት ቁሳቁስ በመግዛት ሲረዷቸዉ የነበሩትን ወላጅ አልባ ልጆችን ጨምሮ በቀበሌዉ ለሚገኙ 25 ቤተሰብ 14,180 ብር በማዋጣት ድቄት ዘይትና ሳሙና ገዝተዉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

PHOTO : (1-JIMMA) (2-ADDIS ABABA) (3-DIREDAWA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FightCOVID19

- የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሜድሮክ ኢትዮዽያ ኢትዮ አግሪሴፍ የተረከባቸውን 45 የደለቡ በሬዎች 'ማዕድ ማጋራት' በሚል ለአርባ ሰፈሮች በቄራዎች ድርጅት ጤናማነቱን ያረጋገጥ እርድ ተከናውኖ እንድሰራጭ በቄራዎች ድርጅት ግቢ ርክክብ ተደርጎል። የስጋ ስርጭቱን የአ.አ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይድ እንድሪስ እና ከአርባ ሰፈር በጎ ፈቃደኞች ወጣቶች ጋር በመተባበር ለመስራት ቃል ገብተዋል።

- አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል አስረክባለች።

- ራይድ #RIDE የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት በተለያዩ የህክምና ተቋማት እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እንዲሆን 50,000 የአፍ መሸፈኛ ማስኮችን ለኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር አስረክቧል።

- ጋስት ሶላር መካኒክስ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የያዛቸው ታካሚዎች አተነፋፈሳቸውን የሚያግዝ ቱቦ ወደ አየር ቧንቧቸው ሲገባ እንደ መከላከያ የሚያግዝ መሳሪያ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እገዛ አድርጓል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FightCOVID19

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ 1 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ያለውን የሚሊኒየም አዳራሽ ማዕከል ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንና የተከናወነውን ስራ መገምገማቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ሚሌኒየም አዳራሽ ለድንገተኛ ወረርሽኝ ምለሽ መስጠት በሚችል ትልቅ ሆስፒታል ደረጃ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት 360 አልጋዎች ዝግጀቱ ሆነዋል፤ ቀሪዎቹም አልጋዎች በሳምንት ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆኑም ነው የተመለከተው።

በህክምና ማዕከሉ 40 የፅኑ ህክምና መስጫ አልጋዎች እና 60 የማገገሚያ አልጋዎችም የኖሩታል። የህክምና ማዕከሉ 700 የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ ሰራተኞች እንደሚኖሩትም ነው የተገለፀው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- የኮሮና በሽታን ቅድመ መከላከል እና በሽታው አስከፊ ደረጃ ላይ ከደረሰ አቅመ ደካሞች በረሀብ እንዳይጎዱ ጎሀጽዮን ከተማ የተማሩ ልጆች 'የወረጃርሶ ልጆች በሚል የቴሌግራም ቻናል' በመሰባሰብ ለወገን የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- በደቡብ ክልል የሀላባ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ጀምዓ ለ250 አቅም ለሌላቸው ምስኪኖች ለረመዳን መያዣ የሚሆን የአስቤዛ ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፉም የተለያዩ እህል፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ለምግብነት የሚውሉ ድጋፎችን አድርገዋል::

- በጅማ ከተማ ሸዋበር መስጅድ የወጣቶች ጀመዓ ለ33 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ድጋፍ አድርጓል። የወጣት ጀመዓው ከበጎ አድራጊዎችና ከአባላቱ ያሰባሰበውን አስቤዛ ጎዳና ለወደቁ እና አቅም ላነሳቸው ቤተሰቦች አድርሷል።

- በአዲስ አበባ ሳሪስ ሷሊህ መስጂድ የሚገኘው ነሲሀቱል አማ የልማትናመረዳጃ ተቋም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት የሚከሰተውን ማህበራዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ታላቁ የረመዳን ወር መቃረቡን ተከትሎ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘው ሸኪህና ህንፃ ለሱቅ እና ለቢሮ አገልግሎት ለተከራዩት በሙሉ የ2 ወር ክፍያ ነፃ ማድረጉን አሳውቆናል። በብር ቢተመን 1,711,746 ይደርሳል #P1

- የጅማ ሆሊላንድ ሆቴል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ሆቴሉን ለጅማ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል። በተጨማሪ የሆቴሉ ባለቤት 'ተሰማ ገበያ' የንግድ ህንፃ ላይ ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎች የ2 ወር ኪራይ ነፃ አድርገዋል #P & #P4

- የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሀገራችን እዳይስፋፋ ለሚደረገው ጥረት ካፍደም ትሬዲንግ /ቃሊቲ / ከህዝብ ከመንግሥት እዲሁም ከተከራይ ደንበኞቻችን ጎን በመቆም ድርጅቱ ለ170 የህንፃው ተከራይ ደምበኞች የ2 ወር 50% ( ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ) ቅናሽ አድርጓል፤ በተጨማሪም ከህንፃው ተከራይ ደንበኞች ፣ ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር በመሆን አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችን ለአንድ ወር የሚሆን የምግብና የንፅህና ግባቶችን ድጋፍ ያረግን መሆኑን አሳውቆናል #P5

- ቢሾፍቱ የሚገኘው ፒራሚድ ሆቴል እና ሪዞርት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ሁለንተናዊ ጫና በመረዳት እገዛ ለሚያስፋጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ አሳውቆናል #P6

- የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኙ የተቸገሩ ህብረተሰብ (100)አንድ መቶ አባወራዎች )የዱቄት፤ ዘይት ፤የእጅ መታጠቢያ ሻምፖ እና በዩኒቨርስቲው የተመረተ ሳኒታይዘር እገዛ አድረገዋል ። እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሰርተዋል #P7

- ከዚህ ቀደም ካሳ ግራንድ ሞል ቅናሽ ማድረጉን አሳውቀናችሁ ነበር፤ ደብዳቤውን ልኮልናል #P2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያን ለኢየሱስ ሕብረት የተሰኘ ስብስብ በሀዋሳ ከተማ ከመናኸሪያ ክ/ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በሀዋሳ በተመረጡ ቦታዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ሰጥቷል። የእጅ ማስታጠብ ስራ ተሰርቷል የክፍለ ከተማው አስተዳደር አቶ አረጋ ሕዝቡ ሳይዘናጋ የጤናን ባለሙያ ምክር በመጠበቅ ከአካላዊ ንክኪ እንዲቆጠብ መልዕክት አስተላልፏል።

- በቦሳ ኪቶ ቀበሌ የክርስቲያን ወጣቶች ህብረት ስለ covid-19 ግንዛቤ የማስጨበጥ እና የእጅ ማስታጠብ ስለሚደረገው ጥንቃቄና በመጨረሻም ሁሉም ወደ ፈጣሪው እንዲጸልይ ለ8 ተከታታይ ቀናት ሰረተናል አሁን የጤና ቢሮ ስልጠና ሰጥቷቸው የቤት ለቤት ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀን ሲሆን በቀጣይነት አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ እንንቀሳቀሳለን ብለውናል።

- ወረዳ 14 አቶ ቶፊቅ ጀማል የተባሉ ባለሀብት 215 አቅመ ደካማ የወረዳው ነዋሪዎችን 1 ሊትር ዘይት፣ 5 kg ሞከሮኒ፣ 5 kg ዱቄት፣ 3 kg ሩዝ እንዲሁም ሌሎች ድጋፎችን አድርገዋል።

- ሀዋሳ በተለምዶ አረብ ሰፈር ተብሎ የሚጠራ አከባቢ ያሉ ሙስሊም ወጣቶች የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ከህብረተሰቡ የሰበሰቧቸውን ዘይት፣ ሳሙና፣ ዱቄት፣ የመሳሰሉትን ለ150 ቤቶች አከፋፍለዋል።

- ደይስታር አካዳሚ በአዳማ ከተማ ነው የሚገኘው ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራንን ባቋቋሙት የበጎ አድራጎት ማህበር ባለፈው ሳምንት ለ380 ሰዎች ምገባ አድርጓል። በመጪው ሀሙስም ተመሳሳይ ፕሮግራም እንደተያዘ ገልፀውልናል።

- የመካኒሳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ኆኅተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት አገልጋዮች ለፋሲካ በዓል በየዓመቱ ቤት ለቤት ያስፈስካቸው ለነበሩ ለ150 አቅመ ደካሞች ቤት ለቤት ደረቅ ምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ እንዲሁም በጎዳና ላይ ላሉ ወገኖቻችን አልባሳት በማሰባሰብ አበርክቷል።

- ራዕይ ፋውንዴሽን በ2005 ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ በጎ ተግባራትን እያከናነ ይገኛል። ራእይ ወላጆቻቸው በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተያዙ ልጆች እንዲሁም ሌሎች የተቸገሩ ልጆችን እየደገፈ ያለ ነው። በስሩ ላሉ ልጆች ባለለፉት 15 ዓመታት ምግብ በመመገብ በተሰቦቻቸው በመደገፍ ቆይቷል። አሁን ግን ሀገራችን በገባው ወረርሽኝ ውስንነቶች አጋጥመዋል። ማገዝ የምትችሉ ወገኖች አግዟቸው። አጠቃላይ የፋውንዴሽኑን ዝርዝር መረጃ ከላይ በፎቶ አስቀምጠናል።

እንግዴ መላው ሀገራችን ላይ በርካታ ሰዎች ብዙ ስራዎችን እየሰራችሁ ነው፤ የሁላችሁንም ማቅረብ ባንችልም፣ ለመልካም ስራችሁ በርቱ ለማለት እንወዳለን!!

እስካሁን ላደረሳችሁን መልዕክት እናመሰግናለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

በነጌሌ አርሲ ከተማ የ'ፋሲካ ኢንተርናሽናል ሆቴል' ባለቤት አቶ አብርሃም ይርጋ የወቅቱን ፈተና አብሮ ለመሻገር በማሰብ ሆቴላቸውን ለለይቶ ማቆያ ይሆን ዘንድ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከባቸውን ነግረውናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BGIEthiopia #FightCOVID19

የፌዴራል ስፓርት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደረሽን እና እግር ኳስ ፌደረሽን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚደግፍ የአንድ (1) ወር የምገባ ፕሮግራም ዛሬ አስጀምረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia