አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦
- ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ከበሽታቸው አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል። የጤና ባለሙያዎች ምክርን ተከትሎም ቦሪስ ጆንሰን በአፋጣኝ ወደ ስራቸው አይመለሱም።
- በቤልጂየም የሟቾች ቁጥር 3,600 ደረሰ። ባለፉት 24 ሰዓት 254 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- ባለፉት 24 ሰዓት በስፔን 619 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 16,972 ደርሷል።
- ባለፉት 24 ሰዓት በሩሲያ 130 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ተሰምቷል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ15,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
- በአውሮፓ ብቻ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ75,000 አልፏል።
- በኢራን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 71,686 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 1,657 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተሰምቷል። 117 ሰዎችም መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሳውዲ አረቢያ የተጣለው የሰዓት እላፊ እንዲራዘም ውሳኔ ተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሐረማያ ዩንቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪን በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀመረ፡፡
የሀረሪ ክልል ፕሬዝደንት እና የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ላብራቶሪዎቹን በይፋ ስራ አስጀምረዋል፡፡
ላብራቶሪዎቹ በሀሮማያ ዩንቨርስቲና በሀረር ከተማ በሚገኘው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ነው ስራ እንዲጀምሩ የተደረጉት፡፡
የሀሮማያ ዩንቨርሲቲ ‘Mechanical Ventilator'ን ጨምሮ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያነት የሚያገለግሉ ቁሳ ቁሶችን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡
ምንጭ፦ OBN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀረሪ ክልል ፕሬዝደንት እና የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ላብራቶሪዎቹን በይፋ ስራ አስጀምረዋል፡፡
ላብራቶሪዎቹ በሀሮማያ ዩንቨርስቲና በሀረር ከተማ በሚገኘው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ነው ስራ እንዲጀምሩ የተደረጉት፡፡
የሀሮማያ ዩንቨርሲቲ ‘Mechanical Ventilator'ን ጨምሮ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያነት የሚያገለግሉ ቁሳ ቁሶችን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡
ምንጭ፦ OBN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ የኮሮና ህሙማንን በቅርብ ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ውይይት በተለይ የኮሮና ህሙማንን በቅርበት ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል።
የሕክምና ባለሙያዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የመኖሪያ ቤት፣ ስልጠና እና የመከላከያ አልባሳትን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚንስትሯ የገለፁት።
ምንጭ፦ EBC

#DrDebretsionGebremichael
በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ በሽታ ባልታወቀ ምክንያት እንዳይገባ የክልሉ መንግስት በቅርቡ የሞቱ ሰዎች በምን ምክንያት እንደሞቱ ምርመራ የማድረግ ስራን እየሰራ ይገኛል።
ከሰሞኑን በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተራዘመበት ዕለት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ይህን ሲናገሩ ተደምጠዋል ፦
በሽታው የለም ብለን መደምደም ባንችልም ፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ አልተገኘም። ሌላው ቀርቶ በየአካባቢው የሚሞቱ ሰዎች በምን እንደሞቱ መታወቅ አለበት ብለን እየመረመርን ነው የምንገኘው።
ምክንያቱም ብዙ ሰው ከረገፈ በኃላ አይደለም ወረርሽኝ ነው ብለን የምንለው። እናም ባልታወቀ መንገድ እንዳይገባ ፍተሻ እያደረግን ነው።
ስለዚህ በቅርቡ በሞቱ ሰዎች ላይ ባደረግነው ምርመራም በሽታው ወይም ቫይረሱ ሊገኝ አልቻለም።
በዚህም ሁኔታ ምርመራውን በማጠናከር የኮሮና ቫይረስ አለመግባቱን ካረጋገጥን በኃላ ከክልሉ ውጪ በሚመጡ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገን የምንሰራ ይሆናል። ነገር ግን እስካሁን እዛ ላይ አልደረስንም።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም ወደ UAE (ዱባይ) በረራ እያደረገ ነው ?
የዶክተር ሊያ ታደሰ ምላሽ ፦
"በሂደት ብዙ በረራዎች እንደተቀነሱ ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ ከ80 በላይ የሚሆኑ በረራዎች እንደተቀነሱ የሚታወቅ ነው። ከMARCH 27 ጀምሮ ወደ UAE (ዱባይ) ያሉ በረራዎች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን በኢሜሬትስ የሚደረጉ ከዚህ መሄድም መምጣትም ቆሟል።"

ከተለያዩ ሀገራት በግዴታ እንዲወጡ እየተደረጉ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን!
ዶክተር ሊያ ታደሰ የተናገሩት ፦
ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ የነበረው ሳውዲ አረቢያም ፣ጅቡቲም፣ UAE (ዱባይም የተወሰኑ ነበሩ) በርካታ ሰዎች የማስወጣት ስራ እየሰሩ ነው።
ኢትዮጵያውያኖችን ወደሀገር የመመለስና በግድ የማባረር ስራ እየሰሩ ስለሆነ እነሱን ተቀብሎ ኳረንቲን ውስጥ አድርጎ የመከታተል ስራ ደግሞ ሌላው ትልቁ ስራ ነው።
ይህን ከሰላም ሚኒስቴር ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከደህንነት እና ጤና ሚኒስቴር፣ ባህልና ቱሪዝም፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር አንድ ላይ ሆነን እየሰራን ነው።
በተቻለ መጠን የኳረንቲን ቦታዎች ላይ ብዙ ዩኒቨርሲቲዎችን እየተጠቀምን ነው ያለነው። ምክንያቱም የሚመጡት ዜጎች የየራሳቸው ክፍል ውስጥ መግባት እንዲችሉና እንዳይቀላቀሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
አስገዳጅ ኳራንቲን ከተጀመረበት ሶስት ሳንምንት ጀምሮ በርካታ ምርመራ በማድረግ የተገኙ ፣ምልክትም ያሳዩ በተጨማሪ የኳረንቲን ጊዜያቸው ሊያልቅ ሲል ሁሉንም ምርመራ በማድረግ በሽታውን ለማግኘት እና ለመቆጣጠር ትልቅ እድል ሆኗል። አብዛኛው ኳረንቲን ውስጥ ያለ ነው እየተገኘ ያለው። ያንንም የበለጠ አጠናክሮ የመስራት ስራ ይሰራል።

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በላከልን መልዕክት በተለይም ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉት መንገደኞች በ 'ሳውዲ አረቢያ አየር መንገድ' እንጂ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳልሆነ አሳውቆናል።
አየር መንገዱ ወደሳዑዲ በረራ እያደረገ አይደለም። 3,000 የሚሆኑ መንገደኞችም ከሳዑዲ አረቢያ የመጡት በሳዑዲ አረቢያ አየር መንገድ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከMARCH 24 አንስቶ ወደ ዱባይ የሚያደርገውን በረራውን አቁሟል።

#HawassaIndustrialPark
በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ኢንደስትሪች ወቅታዊውን ሁኔታ ከግሞት አስገብተው ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ገልፀዋል።
በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶች ሥራቸውን ሳያስታጉሉ አስቸኳይ ፍላጎቶችን ለማሟላት እየተጉ ነው ብለዋል።
ድርጅቶቹ በቀን 10 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን እያመረቱ ሲሆን፣ የምርቱን መጠን በቀን ወደ 50 ሺህ ለማድረስ አቅደዋል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
'ሌሎች ድርጅቶችም ፈጠራ በታከለበት እና ለወቅቱ በሚያመች ሁኔታ ሥራቸውን እንዲከውኑ አበረታታለሁ' ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 431 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። ይህ የሟቾች ቁጥር ከMARCH 19 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው። በሌላ በኩል 4,092 ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 737 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ከ10,000 በልጧል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት 5,288 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በፖርቹጋል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው። በአንድ ቀን 598 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። እስካሁን ድረስ 16,585 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል።
- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት 561 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ከ14,000 በልጧል። በተጨማሪ በ24 ሰዓት 2,937 ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.8 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ419,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ113,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

ሌላኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ፈተና - የአንበጣ መንጋ!
- በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በ14 ወረዳዎች የአንበጣ መንጋ በመከሰቱ በበልግ አዝመራ ላይ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል።
- ከቀናት በፊት ደግሞ በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ አዘቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ መግለፁ አይዘነጋም።
- በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የአንበጣ መንጋ በድጋሜ እንደተከሰተና መላው ህብረተሰብ ተገቢውን የመከላከል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ መገለፁ አይረሳም።
- በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታና ከምባ ዙሪያ ወረዳዎችም የበረሀ አንበጣ መንጋ ተከስቶ መቆጣጠር መቻሉን የአርባምንጭ እጸዋት ክሊኒክ ዛሬ ገልጿል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#KenenisaHotel
ትላንት ምሽት በገለፅንላችሁ መሰረት የአትሮኖስ ትሬዲንግ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ተድላ እና አቶ ተስፋዬ አየለ በዛሬው ዕለት በቅርቡ ተከራይተው እንደ አዲስ እየሰሩበት ከሚገኘው 'ከቀነኒሳ ሆቴል' ማነጅመት አባላት ጋር በመሆን የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው የሚችሉ 250 ወገኖችን መመገብ ጀምረዋል። ይህ ተግባር አሁን ያለው ችግር እስኪያበቃ ድረስ በየሳምንቱ #እሁድ ይቀጥላል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት ምሽት በገለፅንላችሁ መሰረት የአትሮኖስ ትሬዲንግ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ተድላ እና አቶ ተስፋዬ አየለ በዛሬው ዕለት በቅርቡ ተከራይተው እንደ አዲስ እየሰሩበት ከሚገኘው 'ከቀነኒሳ ሆቴል' ማነጅመት አባላት ጋር በመሆን የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው የሚችሉ 250 ወገኖችን መመገብ ጀምረዋል። ይህ ተግባር አሁን ያለው ችግር እስኪያበቃ ድረስ በየሳምንቱ #እሁድ ይቀጥላል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዋግ ኽምራ ኮሚኒኬሽን በተላከልን መልዕክት የዳካሶስ ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ የውሃ ማመላለሻ ቦቴ እና የውሃ ሮቶ ታንከሮች ለዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ድጋፍ አድርጓል።
የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት አቶ ካሳወይ አዲሱ ያደረጉት ድጋፍ ፦
- አንድ የውሃ ማመላለሻ ቦቴ
- እያንዳንዳቸው 1000 ሊትር የመያዝ አቅም ያላቸው 12 የውሃ ታንከሮች ናቸው።
የውሃ ታንከሮቹ በዞኑ ለሚገኙ ለሁሉም ወረዳዎች እንደሚከፋፈሉ የተላከልን መረጃ ይጠቁማል።
አለም አቀፉ ወረርሽኝ አገራችን ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ መንግስትና ህዝብ እያደረጉ ካሉት ጥረትና ርብርብ በተጨማሪ የእያንዳንዱ አስተዋጽኦ አስፈላጊ መሆኑንና አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑን አቶ ካሳወይ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 214 ደረሱ!
በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች በፍጥነት እየጨመረ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 434 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥርም 214 ደርሷል። በሌላ በኩል ዛሬ ሁለተኛው ሞት ተመዝግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች በፍጥነት እየጨመረ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 434 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥርም 214 ደርሷል። በሌላ በኩል ዛሬ ሁለተኛው ሞት ተመዝግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RWANDA
በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 1,160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 126 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት (7) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል።

#COVID19
- በሰማሊያ 4 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተስምቷል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 25 ደርሷል። በተጨማሪ ዛሬ በሀገሪቱ 2ኛው ሞት ተመዝግቧል፤ ሟቹ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ እንደሆኑም ተገልጿል። የሀገሪቱ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሰዓት እላፊ አውጇል።
- በዩጋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 169 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 54 ሆኗል። 4 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው አይዘነጋም።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦
• በሩዋንዳ 1,160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ስድስት (6) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
• በኬንያ 766 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ስድስት (6) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
• በጅቡቲ 434 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሀያ ስምንት (28) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
• በኢትዮጵያ 286 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።
• በዩጋንዳ 169 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።