TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የምዕራብ ኦሮሚያ የፀጥታ ሁኔታ...

የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሰማራ በኋላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው መባሉን ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አጥብቀው ተቃውመዋል።

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል፦

"ይህ ስህተት ነው በተጨባጭ ህዝቡ እያለው የለው ሽፍታን አሰወግዱልን ነው እንጂ መከላከያ ይህን በደለን፣ እንዲህ አደረገን የሚል አንዳችም ነገር የለም። የመንግስት ወታደር ህዝብ ላይ ጉዳት አድርሶ ከሆነ ግን መንግስት ይጠየቃል። እኔም እንደኃላፊነቴ እጠየቃለሁ። እውነት ለመናገር እኔ ያደራጀሁትና እኔ የምመራው ወታደር ህዝብ አይነካም። በደል ተፈፅሞ ከሆነ እኔም በግሌ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቃለሁ፤ እክሳለሁም!"

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ከተንቀሳቀሰ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል። አሁን እያካሄደ ያለው ኦፕሬሽን ከከዚህ ቀደሙ የተለየ ነው?

"ይህ ይለያል፤ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረው ልመናም ጭምር ነበር። ያ ሲሆን ደግሞ ይባስ መጠናከር ጀመሩ፤ ህዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል ይልቁንም ተጠናክሮ ቀጠለ። ህዝቡን ያስፈራራሉ፣ ህዝብ ይዘርፋሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አፍነው 70 እና 60 ኪሎ ሜትር ይዘው ሄደው ለሁለት ሳምንት ደብድበው ይለቃሉ። በዚህ መሰል ዘግናኝ ፀረ ዴሞክራሲ ተግባር የሚታወቀው 'አልሸባብ' ነበር አልሸባብ እራሱ አሁን ላይ እንዲህ ያለ ተግባር አይፈፅምም። ስለዚህ ይህ ሊድን የማይችል የተበላሸ አእምሮ ያለው ኃይል ነው ተብሎ ስለታመነበት መንግስት ከሰሞኑን ጨከን ብሎ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰደ ነው። እስኪወገዱ ድረስ እርምጃው ይቀጥላል። የደገጣ ውጊያ ስነ ምግባር እንኳን የላቸውም!"

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምዕራብ ኦሮሚያ በኮማንድ ፖስት ስር መተዳደር ከጀመረ በኃላ ሰዎች ይታሰራሉ፣ ይለቀቃሉ እንደገና እንደሚታሰሩ ይነገራል በጉዳዩ ላይ ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

ይህ ሀሰት ነው! የስነ ልቦና ጦርነት የሚባል ነገር አለ። አንድ ወታደር ሳይገድሉ 80 ወታደር ገደልን ይላሉ፤ መልሰው ደግሞ እንዲህ በሚባል ቀበሌ ውስጥ ወታደር ገብቶ ሰው ገደለ ብለው ሀሰት ይነዛሉ፤ ገንዘብ እያዋጡ የሚልኩላቸው ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት በማሰብ የላገኙትን ድል እንዳገኙ አድርገው ያወራሉ።

ይህ ደግሞ የደፈጣ ተዋጊ ባህሪ ነው። አንድም ቀን ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተዋግተው አያውቁም። ሁሌም ሲሸሹ ነው የሚመቱት። እየሸሹ ነው የሚያዙት። ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው የመዋጋት አቅምም የላቸውም። ስለዚህ በእነሱ በኩል የሚመጣው ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል ስህተት ነው።

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በምዕራብ በኩል ቀድሞ ኦነግ ስር ከነበሩት ታጣቂዎች ውጪ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሌላ ኃይል አለ ተብለው ከBBC የተጠየቁት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

የለም! ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዷል። የቀሩት ደግሞ አመራሮቹ ናቸው። እነዚህ የቀሩት አመራሮች ደግሞ ታዳጊዎችን እየመለመሉ ይልኩ ነበር። እጅ የሰጡ ተዋጊዎች ትምህርት ተሠጥቷቸው ተመልሰዋል።

አሁን የቀሩት ስፖንሰር ያላቸው ህይወታቸውን በዚህ መልኩ ለመምራት ፍላጎት ያላቸው ብቻ ናቸው የቀሩት። እነሱ ደግሞ ተደብቀው ነው የሚገኙት። የሀገር መከላከያ እየፈለጋቸው ይገኛል።

አሁን ላይ እየተመቱ ጥለው እየወጡ ነው። ባለፉት ሶስት ሳምንታት ሰላም ሆኗል። ለምለም በረሃ በሚባለው ቦታ እንጂ ሌላ አካባቢ ሰላም ነው።

ሁሉም አካባቢ እስኪፀዳ የሰላም ማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። መሮ እራሱ ጦሩ የማይደርስበት ቦታ ተደብቆ ነው የሚኖረው። ሰራዊት እሱ ያለበት ቦታ መድረሱን ሲሰማ ቦታ ይቀይራል። አንድም ቀን መሳሪያ ሳይተኩስ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ታዳጊዎችን ግን ከቀያቸው ሰብስቦ እያስጨረሰ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ 419 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል!

የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ከወሎ ዩኒቨርስቲ እና ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በሶስትዮሽ ስምነነት በድግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 419 ተማሪዎች የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት ተጋባዥ የክልል እንግዶች በተገኙበት ተማሪዎቹን በአሁኑ ሰአት በኮሌጁ የማስመረቂያ አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊት ኮንግረስ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። በትለንትናው እለት የፓርቲው አመራሮች በሰበታ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል።

PHOTO : JAWAR MOHAMMED
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የመድረክ አባል የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ከደጋፊዎቹና አባላቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተገኝተዋል።

PHOTO : SMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABABA

‹‹የአማራ አብሮነት እሴቶች ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ሐሳብ የተለያዩ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል የበይነ መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ደስታ ተስፋው (ዶክተር) ‹‹አማራ የመቻቻልና የመከባበር እሴት ያለው አቃፊ ሕዝብ ነው፤ እውነታው ይህ ቢሆንም በተዛቡ ትርክቶች ምክንያት እንደጨቋኝ መታየቱ ተገቢ አይደለም›› ብለዋል፡፡

ዶክተር ደስታ አብሮነት እና ጠንካራ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመፍጠር መሠራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩም የአማራ የአብሮነት እሴቶችና ተሞክሮዎች፣ የተሳሳቱ ትርክቶች ያስከተሏቸው ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የጤና ሚኒስትሮቹ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል...

የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። ስብሰባው ስለ ኮቪድ አዳዲስ መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ ወረርሽኙን በአህጉር ደረጃ በቅንጅት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተጠራ ነው።

የጤና ሚኒስትሮቹ በወረርሽኙ ዙሪያ የተቀናጀ አህጉራዊ የመከላከልና ለበሽታው ምላሽ የመስጠት ስትራቴጂ ላይ ስምምነት መድረስ የሚያስችል ውይይት ያካሂዳሉ።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከጄኔቭ በቪዲዮ ኮንፍረንስ በቀጥታ በመድረኩ እየተሳተፋ ነው።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች በአሁን ሰዓት እያደረጉ ባሉት አስቸኳይ ስብሰባ በቻይና ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ አፍሪካዊያን ተማሪዎችና ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ እንደሆነ ተሰምቷል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ዝግጅት...

ለበርከታ ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዳይቀርብ ሲከለከል የነበረው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሚሊኒየም አዳራሽ ዝግጅቱ በተጨማሪ ሁለተኛውን የሙዚቃ ዝግጅት በመስቀል አደባባይ ለአድናቂዎቹ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

የዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑ በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደገለፁልን በአሁን ሰዓት በርካታ ታዳሚዎች መስቀል አደባባይ መከተማቸውን ገልፀዋል። የሙዚቃ ዝግጅቱ ከደቂቃዎች በኃላ ይጀምራልም ብለውናል። የፀጥታ ኃይሎችም ዝግጅቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሚገኝ ጨምረው ገልፀዋል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

የኮሮና ቫይረስ መነሻ በሆነችው ውሃን በወረርሽኙ የተጠቁ በሽተኞችን ለመቀበል 19 ጊዜያዊ ሆስፒታሎችን ለመገንባት ማቀዷን ቻይና ገለፀች።

ጊዜያዊ ሆስፒታሎቹ ሲጠናቀቁ እስከ 30 ሺህ አልጋዎችን የመያዝ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።

ውሃን እስካሁን ድረስ 13 ሺህ 348 አልጋዎች ያሉት 13 ቦታዎችን ወደ ጊዜያዊ ሆስፒታልነት የለወጠች ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 9 ሺህ 313 አልጋዎች ቀላል ህመም ያለባቸውን ህመምተኞች ለማከም የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

[CGTN,FBC]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Audio
#UPDATE

የኦሮሚያ ክልል ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫው ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሶኖዶስ በኦሮምያ ቤቴ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ አግባብ አይደለም በማለት ነው።

ምንጭ፦ VOA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#Election2012 የመድረክ አባል የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ /ሲአን/ በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ከደጋፊዎቹና አባላቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩ ላይ የመድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተገኝተዋል። PHOTO : SMN @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

"የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ የሚገኝ ጉዳይ ነዉ" - አቶ ዱካለ ላሚሶ

የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ እንደሚገኝ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሊ/መንበር አቶ ዱካለ ላሚሶ ተናገሩ።

አቶ ዱካለ ይህንን የተናገሩት ሲአን ዛሬ ባካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ነው። እነዚህ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት እንድያገኙ ለጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ደብዳቤ ከመፃፍ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን በሪፖርታቸው ገልጸዋል።

አቶ ዱካሌ ላሚሶ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ደርግ ከፈጸመው በደል ያልተናነሰ የማይረሳ ጠባሳ በሲዳማ ህዝብ ላይ በዚህ በገዥው መንግስትም የተለያዩ በደሎች ተፈፅሟል ብለዋል።

ግንቦት 16/1994 ዓ/ም የተፈፀመው የሎቄ ጭፍጨፋ ለዚህ ማሳያ መሆኑን አንስተው ዛሬም በፖሊቲካ አሻጥር ንጹሃን የሲዳማ ተወላጆች ያለጥፋታቸው በተለያዩ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብለዋል።

አክለውም አቶ ዱካሌ የስልጣን ርክክብ አለመፈፀም እና የምሁራን ኤጄቶች እስራት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ቁጣ እየቀሰቀሰ የሚገኘዉና በግዜ እልባት የሚያስፈልገው ጉዳይ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ምንጭ፦ SMN
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተቃዋሚያቸው የነበሩት ሪክ ማቻርን የሀገሪቷ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

የሪክ ማቻር ሹመት የተሰማው ሁለቱ አካላት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለመመስረት ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።

#CGTN #ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ATTENTION

"ይህ ከላይ የምትመለከቱት ምስል በአርሲ ዞን ሌሙ እና ቢልቢሎ ወረዳ ፣ ከበቆጂ ትንሽ ኪሎሜትሮችን (ወደ አሠላ አቅጣጫ) አምበጣ መንጋ የ አርሶ አደሮችን ማሳ እና ዛፎችን ሲወር ያነሳሁት ነው:: በጣም የሚያስፈራ መንጋ ነው።" - IBRO MAN [Tikvah Family]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia