#MekelleUniversity #AddisAbeba
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን የምክክር መድረክ በሀርሞኒ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ "የAlmuni ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል ርእስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።ከ200 በላይ የቀድሞ ምሩቃን፣ መምህራን እንዲሁም የአሁን ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
(ኤልያስ መሰረት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#DILLA
በጌዴኦ ዞን የኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ። “ማህበረሰብ የለውጥ አቅም ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮ የዓለም ኤድስ ቀን በዞን ደረጃ ከትላንት በስቲያ በዲላ ከተማ ተከብሯል።
የዞኑ ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ፈይሳ በወቅቱ እንደገለጹት በዞኑ የቫይረሱ ስርጭት ቀደም ሲል ከነበረበት 1 በመቶ ወደ 3 ነጥብ 7 በመቶ ከፍ ብሏል።
በዘርፉ ይደረግ የነበረው የመከላከል ሥራ መቀዛቀዝ፣ ለበሽታው አጋላጭ የሆኑ የጫት፣ የሽሻና መጠጥ ቤቶች መስፋፋት ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር ምክንያቶች ከሆኑት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‹‹ኢትዮጵያን ለመፍረስ የሚዳርጋት ስጋት የለም›› - ጀነራል ብርሃኑ ጁላ :- ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
በሀገራችን ውስጥ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከጀርባ ባሉ ስውር እጆች በሚደገፉ ኃይሎች ወይንም ቡድኖች የሚፈጠሩ ግጭቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እያለ ኢትዮጵያን የሚበታትን እና ለመፍረስ የሚዳርጋት ስጋት እንደሌለ ተገለጸ፡፡
የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ፖለቲከኞች የሚሉትን ሊሉ ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የት ሄዶ ነው ኢትዮጵያ የምትፈርሰው? ኢትዮጵያን የሚበታትንና ለመፍረስ የሚዳርጋትም ምንም አይነት ስጋት የለም፡፡
እንደ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ገለጻ፣ አሁን በተጨባጭ በሚታየው ሁኔታ ሀገራችን የዳር ድንበር መደፈርና የውጭ ስጋት የለባትም፡፡ በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በምእራብ ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታም ሰላማዊ ነው፡፡
ሕዝቡ ተረጋግቶና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ትብብርና ድጋፉን አጠናክሮ መስራት ይጠበቅበታል። በአጠቃላይ ህዝቡ ሊሸበር አይገባውም፤ በመረጋጋት ሥራውን መስራት አለበትም ብለዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-14

#CARD
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያረቀቀው አዋጅ ላይ ዛሬ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በCARD አዘጋጅነት የማህበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች አዋጁን ይዘት እንዲተዋወቁትና ከባለሞያ ጋር እንዲመክሩበት በመሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) ጹሑፍ አቅራቢነት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም በመድረኩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፤ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል...
" ፖለቲከኞች የሚሉትን ሊሉ ይችላሉ ፤ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የት ሄዶ ነው ኢትዮጵያ የምትፈርሰው?? ኢትዮጵያን የሚበታትንና ለመፍረስ የሚዳርጋትም ምንም አይነት ስጋት የለም፡፡ አሁን በተጨባጭ በሚታየው ሁኔታ ሀገራችን የዳር ድንበር መደፈርና የውጭ ስጋት የለባትም፡፡ በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በምእራብ ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታም ሰላማዊ ነው፡፡ ሕዝቡ ተረጋግቶና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ትብብርና ድጋፉን አጠናክሮ መስራት ይጠበቅበታል። በአጠቃላይ ህዝቡ ሊሸበር አይገባውም፤ በመረጋጋት ሥራውን መስራት አለበት።" - ጀነራል ብርሃኑ ጁላ (የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም)

ኢህአፓ ይቅርታ ጠየቀ!
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ)ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ትግል በሚያካሂድበት ወቅት ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ይቅርታ ጠየቀ። ፓርቲው ከለውጡ በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ አመታዊ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሂዷል። በዓመታዊ ጉባኤው መክፈቻ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ወይዘሮ ቆንጂት ብርሃን እንዳሉት፤ ኢህአፓ በትግል ወቅት በነበረው አስገዳጅ ሁኔታ የሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
በመሆኑም ለተሰራው ስህተትና ለጠፋው የሰው ህይወትም ሆነ ንብረት ፓርቲው ይቅርታ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብን በተለይም ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦችና ግለሰቦች ዛሬ በጉባኤው በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ቀድሞ የተሰራው ስህተት አሁን ላለው ትውልድ ትምህርት እንዲሆንና በየቀኑ በተለያዩ አካላት የሚፈጸሙ ስህተቶች እንዲታረሙ የበኩሉን እንደሚወጣ ጠቁመዋል።
https://telegra.ph/ETH-12-14-2
(ENA)

#ኢህአፓ
ኢህአፓ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ) በኢትዮጵያ ዘመናዊ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያለው ሲሆን በ1966 ዓ.ም በአገሪቱ አብዮት መፈንዳቱን ተከትሎ የመንግስት ስልጣንን ከተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግስት ‘ደርግ’ ጋር መግባባት አለመቻሉን ተከትሎ ብዙ ችግሮች ሊደርሱ መቻላቸው ይታወሳል። በዚህ አለመግባባት የተነሳም በርካታ ወጣት ምሁራን ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል። ብዙዎቹም ለእስር፣ ለአካል ጉዳትና ለስደት ተዳርገዋል።

"ህወሓት በውህደቱ ጉዳይ በጉባኤ እወያይበታለሁ ማለቱ ምንም ችግር የለውም። ዋናው ግን ከዚህ በኋላ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ሲታይ እንደማይዋሀድ የሚያሳይ ነው። ይሁንና ከጠቀመው ችግር የለውም፤ ካልጠቀመው ደግሞ የራሱ የፓርቲው ጉዳይ ነው የሚሆነው።" - አቶ አምዶም ገብረስላሴ (የአረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መቐለ የሚገኘውን አዋሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ዶክተር ደብረፂዮንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን...
ደብረብርሃንን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ሁለተኛ አማራጭ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር ገለፀ፡፡ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ ለዚሁ እገዛ እንደሚያደርግ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ባለመዋዕለ ነዋዮችን እየሳበች ነውም ብለዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሐብቶች የሚሆን ከ2 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ማዘጋጀቱንም ተሰምቷል፡፡ በዚህ ዓመት ለ80 ፕሮጀክቶች ፈቃድ እንደተሰጠም ነው ከንቲባው የተናገሩት፡፡
ደብረብርሃን መጥቶ በማንኛውም ምጣኔ ሐብታዊ ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ላለው በራችን ክፍት ነው ብለዋል፡፡ የከተማዋ የቱሪዝም ዘርፍ እንቅስቃሴም እየተነቃቃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አካባቢው ከሚታወቅበት ተፈጥሯዊ፣ ማህበራዊ እና ታሪካዊ መስህቦች አንፃር ግን ብዙ ይቀረዋል መባሉ ነው የተሰማው፡፡ በአጠቃላይ ከተማዋን ለማዘመንና ሕብረተሰቡንም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡
(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

አልበሽር የሁለት ዓመት እስር ተፈረደባቸው!
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በተከሰሱባቸው የሙስና ወንጀሎች የሁለት ዓመት እስር ዛሬ ተፈረደባቸው። አልበሽር የእስር ጊዜያቸውን በተሃድሶ ማዕከል እንዲያሳልፉም ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤት ወስኗል።
የዛሬውን የፍርድ ውሳኔ በንባብ ያሰሙት አልሳዲቅ አብድልራህማን “ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት ኦማር አልበሽር በማህብረሰብ ተሃድሶ ማዕከል ለሁለት ዓመት ይቀመጣሉ” ብለዋል። ዳኛው አልበሽር ወደ እስር ቤት እንዲላኩ ያላደረጉት 75 ዓመት የሞላቸውን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዕድሜ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ተብሏል። በዛሬው የፍርድ ውሳኔ አልበሽር ከስልጣን ሲወገዱ ከቤታቸው ተገኝቶ የነበረው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ እና የሱዳን ፓውንድ ገንዘብ እንዲወረስ ትዕዛዝ ተላልፏል።
የሚያዘወትሩትን ነጭ ባህላዊ ጥምጣም እና ጀለቢያ የለበሱት አልበሽር የዛሬውን የፍርድ ሂደት በብረት ፍርግርግ በታጠረ ሳጥን ሆነው በዝምታ ሲመለከቱ ተስተውለዋል። የአልበሽር ዋነኛ ተከላካይ ጠበቃ የሆኑት አህመድ ኢብራሂም አልጣሂር በዛሬው የፍርድ ውሳኔ ላይ ይግባኝ እንደሚሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ከዛሬው የችሎት ውሎ መጀመር አስቀድሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአልበሽር ደጋፊዎች በካርቱም ከሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት አቅራቢያ ተሰባስበው ነበር። ወደ ቤተመንግስቱ እና የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሚወስደው መንገድ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ተዘግቶ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል። የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ጉዳይ በተመለከተው ፍርድ ቤትም ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር መታየቱን ዘገባው ጠቁሟል።
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

በክፍያ መንገዶች ላይ ከተፈቀደው ክብደት በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን የምንቀጣበት ህግ ባለመኖሩ የመንገዱን ደህንነት ለማስጠበቅ ተቸግሬአለሁ” ሲል የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ።
የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ከድር እንደተናገሩት፤ ከተፈቀደ ክብደት በላይ የመጫን ችግር በድሬደዋ ደወሌ የክፍያ መስመር ላይ ጎልቶ ይታያል። ቢሆንም ግን በአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ የሚታይ መሆኑን ተናግረዋል።
እስካሁን በነበረው ሁኔታ በአዲስ አበባ አዳማ ፍጥነት መንገድ ከተፈቀደው ክብደት በላይ የጫኑ አሽከርካሪዎችን በነባሩ መንገድ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ቢሞከርም ህግ ጥሰው የሚገቡ እንዳሉ ጠቁመዋል። ችግሩ ጎልቶ በሚታይበት የድሬዳዋ ደወሌ ፍጥነት መንገድ ህግ በመተላለፍ ከተፈቀደው ክብደት በላይ ጭነው በመንገዱ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች 33 በመቶ እንደሚሆኑ አመልክተዋል። ከመጠን በላይ የሚጭኑ አሽከርካሪዎችን በመንገዱ እንዳይገለገሉ የማድረግ ስራ እንደሚጀመርም አቶ ሙስጠፋ ጠቁመዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD
የመብቶችና ዲሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል (CARD) አዘጋጅነት ዛሬ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያረቀቀው አዋጅ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ውይይቱ የማህበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች አዋጁን ይዘት እንዲተዋወቁትና ከባለሞያ ጋር እንዲመክሩበት አልሞ የተዘጋጀ ሲሆን ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡
ውይይቱ በመሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) ጹሑፍ አቅራቢነት ተጀምሮ በተሳታፊዎቹ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከህጉ አስፈላጊነት ጀምሮ አተገባበር ላይ ስለሚገጥሙት እንከኖች በስፋት ተዳሰዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉት የጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በውይይቱ ወቅት የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብዓትነት ይዘዋቸዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የምክክር መድረኩን ካዘጋጀው CARD ኤክስኪዊቲቭ ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ እንደ አቶ በፍቃዱ ገለጻ የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በሦስት መሰረታዊ ነገሮች ላይ መሰራት አለበት ብለው ይመክራሉ እነዚህም ሀቅን ማረጋገጥ(Fact checking )፣ የሚዲያ አጠቃቀም (Media literacy) እና የመንግስት ግልጸኝነት (Transparency ) ናቸው ይላሉ፡፡
ተጨማሪ ከላይ ባለው ፋይል አድምጡ!
#TIKVAH_ETHIOPIA

ኢ/ር ታከለ ኡማ ያልጠበቁት ሽልማት...
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለትምህርት ቤት እድሳት ላበረከቱት አስተዋፆ፤ ተማሪዎች ዩኒፎርም እንዲያገኙ፣ የምገባ ስርዓቱም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እንዲቀጥል ላደረጉት ስራ ከወጣቶች ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። አዘጋጆቹ ስጦታውን የገዙት የተለያዩ ባለሃብቶችን በማነጋገር እና ስፖንሰር በመፈለግ ነው። ስጦታው 120,000 ብር የሚያወጣ የዳይመንድ ቀለበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
(ኢትዮጲካሊንክ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

"አንድ ዩኒፎርም እየተቀያየርን እንለብስ ነበር!" - ኢ/ር ታከለ ኡማ
ኢ/ር ታከለ ዛሬ ጌትፋም ሆቴል በነበረ ልዩ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ላበረከቱት አስትዋፆና ለሰሩት ስራ ልዩ ትኩረት ሊሰጡ የቻሉት በችግር ውስጥ ስላለፉ እንደሆነ ገልፀዋል። ከአምቦ 10 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ቦታ በእግራቸው እየተመላለሱ እንደተማሩ የተናገሩት ኢ/ር ታከለ የተማሪ ዩኒፎርም በሚለብሱበት ወቅት አንድ ጓደኛ እንደነበራቸውና ዩኒፎርሙን እሳቸው ጥዋት ሲለብሱት ጓደኛቸው ደግሞ መልሶ ይለብሰው እንደነበር፤ በዩኒፎርም ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህም ምክንያት በተማሪዎች ዩኒፎርም ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደቻሉ አስረድተዋል።
(ኢትዮፒካሊንክ)

#ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ የካቲት ወር 2020 ዓመተ ምህረት የአፍሪካ ሀገራት ምድር ጦር ጉባኤን ታስተናግዳለች። ጉባኤውንም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ጋር በመተባር እንደሚያዘጋጀውም ነው የተመለከተው። በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ላፍቴ ፍሎራ በጉባኤው ዝግጅት ዙሪያ ለመምከር ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸውም ወቅት ለጉባኤው እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
በጉብኝታቸውም ወቅት የአሜሪካ ጦር በአህጉሪቱ ዘላቂ ፀጥታ ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት ጥረቶችን ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። ለአራት ቀናት በሚካሄደው ጉበኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወታደራዊ አዛዦችን የሚያሰባስብ ነው።
(ኤፍቢሲ)

"ሚዛን ጨምሪያለሁ አሁን፤ ብዙ ስፖርት ያስፈልገኛል እያልኩ ነው!"-ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል(የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር)
📹7.4MB(WiFi ቢሆን ይመረጣል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
📹7.4MB(WiFi ቢሆን ይመረጣል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።
(📸ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።
(📸ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳሳቢው በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለው ስርቆት!
ታህሳስ 04 ቀን 2012 ዓ.ም በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (Tower) ላይ በደረሰው ስርቆት ሞጆ ከተማና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጧል። ይህ የዘረፋ ወንጀል የተፈጸመው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ አካላት ሲሆን የዘረፋው ሰለባ የሆነው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለሞጆ ኃይል ማስተላለፊያ ጣቤያ (Distribution Subsstation) ኃይል የሚያስተላልፍ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሞጆና አካባቢው ደንበኞቹ ይህ ችግር እስኪቀረፍ በከፊል ኤሌክትሪክ የተቋረጠ መሆኑን አሳውቆ ይህንን አይነት እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ዘራፊዎችን በመከታተል ለህግ አስከባሪ አካላት በማሳወቅ ወንጀልን በጋራ በመከላከል በመንግስትና ህዝብ ሀብት ላይ እየረሰ ያለውን ጉዳት እናድን ሲል ጥሪ አቅርቧል። መሠል ተግባራት እንዳይፈጸሙ ህብረተሠቡ መሠረተ ልማቱን እንዲጠብቅም ጥሪውን አስተላልፏል።
(የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

ትኩረት እንዲደረግ!
በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ (አይፓፑ ቀበሌ) ያለውን የፀጥታ ሁኔታ መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው የዳንጉር ወረዳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጠይቀዋል። በትላንትናው ዕለት በሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የነገሩን የቤተሰባችን አባላት ለጉዳይ መንግስት ልዩ ትኩረት እና አስቸኳይ መፍትሄ ካልሰጠ እየሰፈን የነበረውን አንፃራዊ ሰላም ዳግም እንዲደፈርስ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። የመንግስት አካላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩም ቤተሰቦቻችን አሳስበዋል።
ዝርዝር ጉዳዮችን እየተከታተልን እናቀርባለን!