TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ላይ የሚያገለግል ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ። ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለጊዜው የተጀመረው በ10 ኤርባስ 350 አውሮፕላኖች ላይ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከ6 ቢልዮን ብር በላይ ወጪን የሚጠይቁ የአስፋልት መንገዶች ሊገነቡ ነው!

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ6.1 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ አስፋልት መንገዶች ሊያሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከ6.1 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የ299 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸውን አራት መንገዶች በአስፓልት ደረጃ ሊያስገነባ ነው፡፡

ባለስልጣኑ ለሚያስገነባቸው አዳዲስ የአስፋልት መንገዶች ከአሸናፊ የስራ ተቋራጮች ጋር ነገ ህዳር 25/2012 ዓም ይፈራረማል። በዕለቱም እየተባባሰ የመጣውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል በመሰረተ ልማት ግንባታና ማሻሻያዎችን በተመለከተ በተዘጋጀው መረሃ ግብር ላይ የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል። በነገው እለት መስርያ ቤቱ ከተቋራጮቹ ጋር የሚፈራረምባቸው አራቱ መንገዶች የሀሙሲት-እስቴ፣ የፍስሀገነት - ኮሌ- ሰገን - ገለባኖ ሎት 2 የጩልሴ-ሶያማ፣ የጎዴ ቀላፎ-ፌርፌር እና የአደሌ- ግራዋን መንገዶች ሲሆኑ አጠቃላይ 299 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖራቸዋል ተብሏል።

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ጂቡቲ ውስጥ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት የለም ተባለ!

እስካሁን ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን በጂቡቲ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ ተገለጸ። የባሕር በር አልባዋ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ሦስት አስርት ዓመታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ጂቡቲ ውስጥ መልሳ ልታቋቁም መሆኗ ተነግሯል።

ባለፈው ሳምንት ካፒታል የእንግሊዝኛ ጋዜጣ የኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ጂቡቲ ውስጥ እንደምታቋቁምና ዋና የማዘዣ ጽህፈት ቤቱም በባሕር ዳር ከተማ እንደሚሆን ዘግቦ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን መልሳ የማደራጀት ፍላጎት እንዳለት በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በይፋ መነገሩ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር የሆኑት መሐመድ እድሪስ ፋራህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጉዳዩን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና የጂቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ እንዳሉት የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ጂቡቲ ውስጥ ማቋቋምን በሚመለከት ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ያመላከቱ ሲሆን፤ ነገር ግን "እስከ አሁን የተደረሰ ህጋዊ ስምምነት የለም" ብለዋል።

More👇
https://telegra.ph/BBC-12-04

(BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሮፌሰር መረራ ስለ ዶ/ር አብይና አቶ ለማ...

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ቢለያዩም ልዩነታቸው የተሻለ ሐሳብና ሥራ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህ ግን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ነው መሆን ያለበት”

(ሸገር 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#EPRDF #NEBE #ProsperityParty

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረከቡን ፓርቲው ገልጿል።

(EPRDF Official)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በቃል ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ደውዬ እነግራለሁ ብለውናል!

"በምላሹ ምን ያህል እረካችሁ ለሚለው፤ ማለት ምፈልገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት ነገር አለ፤ የህዝቡ ፍላጎት ይሄ የሚሆን ከሆነ በህግ እና በህገ መንግስታዊ ስርዓት መሰረት እንዲጠናቀቅ አደርጋለሁ። ቃል በቃል ደግሞ ለምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ደውዬ እነግራለሁ ነው ያሉት። ይሄን ያሉት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የቀድሞ የደኢህዴን ሊቀ መንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ባሉበት ነው።" አክቲቪስ ወርቅነህ ገበየሁ (እሁድ የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዱ)

#OMN (ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀረቡ!

በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀረቡ። የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው እንደገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ጨምሮ 21 አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ አቅርበዋል። ሬድዋን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ባደረጓቸው ጉብኝቶች አምባሳደሩ ሲያጅቧቸው ታይቷል። ሬድዋን ሑሴን ወደ አስመራ ከመዛወራቸው በፊት በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ስለ ፓርቲዎች ውህደት...

"የፓርቲዎች ወደ አንድ ውህድ ፓርቲ መሰባሰብ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያስችላል...የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉት ውህደት በስምምነት እንጂ በግዳጅ ላይ የተመሰረተ መሆን የለበትም...በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት መጠናከር የፓርቲዎች መሰባሰብ አስፈላጊ ነው... በተለይ የፓርቲዎች መሰባሰብ አቅማቸውን በማጠናከር የህዝብ ጥያቄን በአግባቡ ለመመለስ ያስችላል።"

(ኢዜአ)

@tikvahethioia @tikvahethiopiaBot
#NEBE #SIDAMA

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ። ባለፈው ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም የህዝበ ውሳኔው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ በዛሬው እለት ደግሞ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል። በዚህም 97 ነጥብ 7 በመቶ የሆኑት መራጮች ሲዳማ በክልልነት እንዲደራጅ ድምጽ ሲሰጡ፥ 1 ነጥብ 47 በመቶዎቹ ሲዳማ በደቡብ ክልል ለመቆየት ድምጽ ሰጥተዋል።

https://telegra.ph/FBC-12-04

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
መቐለ በተካሄደው ሕገ መንግስትን እና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት የማዳን ሁለተኛ አገር አቀፍ መድረክ የተላለፈው የአቋም መግለጫ!

አገራችን ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ በጋራ የመሰረቷት ቤት እንደመሆንዋ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል ሕገ መንግስት እና ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝምን በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ይሁንታ ፀድቆ ወደ ሥራ ከገባ ወዲህ ከሃያ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

በነዚህ ዓመታት ውስጥ ሕገመንግስታዊነትንና ህብረ ብሄራዊ የፌደራልዝም ስርዓትን ቀስ በቀስ እግር እየተከሉ በሰላም፣ በልማት እና በዴሞክራሲ ረገድ ብዙ ለውጦች የተመዘገቡ ቢሆንም ቅሉ በመንግስት ውስጥ እየገነገነ በመጣው ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የፀረ ዴሞክራሲ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግር የተጀመረውን መልካም ሥራ በተለይም ሕገ መንግስቱንና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓቱን ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል። ኢህአዴግ በህብረ በሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት እንዲመራት በአደራ የተቀበላት አገርና የተሰጠው የፖሊተካ ስልጣን መንገድ ስቶ አገሪቷን ወደ መበታተን አያመራች ነው።

More👇
https://telegra.ph/TPLF-12-04

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#HARAR

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት "ሂላል" በሚል ስያሜ የሸርዓ መርህን መሠረት በማድረግ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ በሐረር ከተማ ከፍቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በሐረር ከተማ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን ከፍቶ ሥራ መጀመሩን አስታውሰው፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የሸርዓ መርህን መሠረት አድርጎ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ መክፈቱን ገልፀዋል፡፡

(CBE)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day2 #Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፦ የሃሳቡ ደጋፊዎች፣ ተካፋዮች ፣ አስተባባሪዎች የሆኑ እጅግ የምናከብራቸው የሀገራችን ወጣቶች በተለያዩ የከተማው ክፍሎች በመዘዋወር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሮሸሮችን በመበተንና ስለ ዓላማው በማስረዳት ስራቸውን ሲሰሩ ውለዋል። ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ነገ የ3ኛው ቀን ስራ ይቀጥላል!

ሃሳብ፣ መልዕክት የላችሁ፣ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ልታግዙን የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት ካላችሁ እነዚህ አድራሻዎች ተጠቀሙ፦ @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde 0919743630

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
"የትራፊክ አደጋ እየገደለን ነው፣ ቀስ ብለን እናሽከርክር፣ #እንደርሳለን"