#MOJO
ትላንት ለሊት 10:00 በሞጆ ከተማ ገበያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር። የሞጆ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ ለሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት መረጃው ባይኖራቸውም በንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱን በስፍራው ተገኝተው አረጋግጠዋል። እሳቱን ከሰዓታት በፊት ነው መቆጥጠር የተቻለው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በባህር ዳር ከተማ 1661 ዩኒት ደም ተሰብስቧል!
የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር-ባህር ዳር (EMSA-Bahir Dar) አባላት፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ከባህር ዳር ደም ባንክ፣ ከክለብ 2/12፣ ከKeep Hope Alive(KHA) እና ከሌሎች በጎ ፍቃደኞች ጋር በመተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
Via EMSA-Bahir Dar
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር-ባህር ዳር (EMSA-Bahir Dar) አባላት፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ከባህር ዳር ደም ባንክ፣ ከክለብ 2/12፣ ከKeep Hope Alive(KHA) እና ከሌሎች በጎ ፍቃደኞች ጋር በመተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
Via EMSA-Bahir Dar
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦዪንግ አመነ፤ ይቅርታ ጠየቀ!
737 ማክስ ጄቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አምኗል። የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ምዩለንበርግ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ከትናንት በስቲያና ትናንት ሲጠየቁ ስሕተትና ጥፋት መፈፀሙን አምነው “እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ” ብለዋል። የኩባንያቸው መታመን እንደገና እንዲያንሠራራ ለማድረግ በርትተው እንደሚሠሩና እንዲያ ዓይነት ጥፋት እንደማይደገምም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የንግድ፣ የሣይንስና የትራንስፖርት ኮሚቴ ተናግረዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦችና የሕግ ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል። የቦዪንግ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬም በተወካዮች ምክር ቤቱ የትራንስፖርት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል።
Via VOA

ቀይመስመር ተጥሷል!
ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሰሞኑን ሀገራዊ ጉዳይ አስመልክቶ በቲውተር ገጻቸው እንዲህ ብለዋል፡-
"ዘርና ሀይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሀን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል፣ ለቅሶ፣ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል ሃዘናቸው ሃዘኔ/ሃዘናችን ነው። ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል። አገራችንን ካንዣበበባት ክፉ አዳጋ ለማዳን ሁላችንም ሚና አለን፤ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው፡ቀይ መስመር መጣስ የለበትም እንበል።"

#AMBO
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአምቦ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተጨማሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተዋል።
በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይም የአምቦ ከተማ፣ የምእራብ ሸዋ ዞን፣ የደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን፣ የቡራዩ፣ የሆለታ እና የወሊሶ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል። በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ያለው ውይይትም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ከኦቢኤን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Via OBN

#ነቀምቴ
የአራቱ የወለጋ ዞኖች ማለትም የምስራቅ፣ ምእራብ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኢህአዴግ እና የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ በኮንፍረንሱ ላይ በመገኘት ተሳታፊዎችን በማወያየት ላይ ይገኛሉ።
በውይይቱ ላይ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ በዳሳ ጂንፌሳ ባስተላለፉት መልእክት፥ የኦሮሞ ህዝብ ባለው እሴት አንድ ሆኖ የባርነት ቀንበርን እንደሰበረ ሁሉ ችግሮቹንም በአንድነት በመሆን በውይይት መፍታት አለበት ብለዋል። አንድ መሆን ከቻልን ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንችላለን ሲሉም ከንቲባው መልእክት አስተላልፈዋል።
Via FBC

TIKVAH-ETHIOPIA
#MOJO ትላንት ለሊት 10:00 በሞጆ ከተማ ገበያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር። የሞጆ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ ለሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት መረጃው ባይኖራቸውም በንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱን በስፍራው ተገኝተው አረጋግጠዋል። እሳቱን ከሰዓታት በፊት ነው መቆጥጠር የተቻለው። @tsegabwolde @tikvahethiopia
በሞጆ ከተማ የደረሰው የእሳት አደጋ!
በሞጆ ከተማ " ገበያ " ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ ዛሬ ለሊት 10፡00 ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 የሚሆኑ ሱቆች መውደማቸውን ነው የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያታወስታወቀ፡፡ የእሳት አደጋውም ወደሌሎች አካባቢ እንዳይዛመት በህብረተሰቡና በእሳት አደጋ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጽህፈት ቤቱ ገልቷል፡፡
አደጋውን ለመከላከልም የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ፣ ከአዳማ፣ ከቢሾፍቱ እና ከግል ድርጅቶች የተወጣጡ መሆናቸውንም ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡ በእሳት አደጋውም የወደመውን የንብረት መጠን ተጣርቶ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ የሞጆ ከተማ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ ኮማንደር ሙሃመድ አህመድ መግለጻቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው።

#NewsAlert ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አንደሚሾሙ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንዳሉት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አንደሚሾሙ ተናግረዋል።
(Ethio Fm107.8)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
(Ethio Fm107.8)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትራምፕ ጀግና ለተባለው ውሻ ሜዳሊያ እንደሰጡ የሚያሳይ ሀሰተኛ ፎቶ መልቀቃቸው እያነጋገረ ነው!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ተሳትፎ ለነበረው ውሻ ሜዳሊያ ሲሰጡ የሚሳይ የተቀነባረ ፎቶ በመልቀቃቸው ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ የለቀቁት ፎቶ በአይ ኤስ መሪ አል ባግዳዲ ግድያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበረው ጀግና ውሻ በአንገቱ ላይ ሜዳሊያ ሲያጠልቁለት ያሳያል፡፡
ነገር ግን ይህ ፎቶ በተግባር ያልተደረገ እና አሶሴትድ ፕሬስ በ2017 ጄሜስ ማክክሎከን የክብር ሜዳሊያ ሲበረከትላቸው የሚያሳየውን ፎቶ በማቀነባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
አል ባግዳዲ በተገደለበት ዘመቻ ላይ ተሳትፎ የነበረው ይህ ውሻ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዳልገባ እና ጉዳት አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም ወደ ሌላኛው ሃላፊነት መሰማራቱ ነው የተነገረው፡፡
ይህ የፕሬዚዳንት ተግባርም በአሁን ወቅት ከፍተኛ ችግር የሆነው የሀሰተኛ ዜናዎች መገለጫ ነው በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡ ጄሜስ ማክክሎከን ም ፎቶዋቸውን ተቀነባብሮ ጥቅም ላይ በማወሉ ምን አይነት ምላሽ እንዳልሰጡና በተግባሩ እንደተስማሙ ይመስላል የሚል ግምት እየተሰጠ ነው፡፡
ምንጭ፡- ሃፊንግተንፓስት(ኤፍ ቢ ሲ)

#Photoshop🤔ዶናልድ ትራምፕ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ፎቶ ትዊተር ገፃቸው ላይ በመልቀቃቸው ተቃውሞ እየቀረበባቸው ይገኛል። አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ተሳትፎ ለነበረው ውሻ ሜዳሊያ ሲሰጡ የሚሳይ የተቀነባረ ፎቶ ነው በትዊተር ገፃቸው የለቀቁት።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ትክክለኛው የውሻው ፎቶ ይሄ ነው። በነገራችን ላይ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ከቀናት በፊት በትዊተር ገፃቸው ላይ ውሻው አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ትልቅ የሚባል ተሳትፎ እንደነበረው በመግለፅ አሞጋግሰውት ነበር።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba
የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት የአራተኛው ቀን መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛን። ፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።
PHOTO: ziz(ቲክቫህ ቤተሰብ)

አምቦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ እንዲሁም የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከተለያዩ የህበረሰት ክፍሎች ጋር ውይይት ከሚያደርጉበት አዳራሽ ፊት ለፊት ወጣቶች የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
PHOTO: HA(አምቦ ቲክቫህ ቤተሰብ)

DBRE TABOR UNIVERSITY
አጀማመሩ ብዙ ውጣ ውረዶች የበዙበት እንደነበር የሚነገርለት የደም ባንክ አገልግሎት በአገራችን በ1962 ዓ.ም እንደተጀመረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ምሁራን በ1962 ዓ.ም የነበረውን ልምድ ሲገልጹ ፡- ማህበረሰቡ ባለው የግንዛቤ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠ በመምጣቱ ዛሬ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ አስተዋጽኦ እያደረገ ቢሆንም ደም መስጠት በተጀመረበት ዘመን ግን ተግባሩን ለማስለመድ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች እንደነበሩ ያወሳሉ።
የዛሬ 50 አመት ደም ልገሳ በኢትዮጵያ ሲጀመር ሀሳቡን በበጎ የተቀበሉና እውቀቱ የነበራቸው ሰዎች የመኖራቸውን ያህል ድርጊቱን የኮነኑ እንደነበሩ የሚገልጹት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ግንዛቤው እየጨመረ የሌላው አለም ተሞክሮ እየታየ የደም ልገሳ ሰብአዊ አገልግሎት መሆኑ ታምኖበት እነሆ ዛሬ በቂ ባይባልም የተሻለ ደረጃ ላይ ተደርሶአል ሲሉ በመስኩ የሚያገለግሉ ግለሰቦች ያስረዳሉ፡፡
ደም ልገሳ የተከበረ እና ሰብአዊ ተግባር መሆኑን የተገነዘቡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ሰራተኞችና ተማሪዎች ከጥቅምት 15-17/2012 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት ደም ለግሰዋል፡፡ ለተከታታይ 3 ቀናት በቆየው የደም ልገሳ 307 በጎ ፈቃደኞች ደም ለግሰዋል፡፡
Via ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

#NewsAlert
ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ከእስር ተለቀዋል።
ምንጭ፦ Tahir Mohammed

❤️የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኩሓ አካባቢ የሚገኙ ገበሬዎችን እያገዙ ይገኛሉ። በሚነገራቸው መሰረት ያጭዳሉ፣ ይሰበስባሉ። ከአማራ ፣ ከትግራይ፣ ከጋምቤላ፣ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ...የተውጣጡ የሀገራችን ወጣቶች በአንድነት እየተሳተፉ ነው።
PHOTO: B(መቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO: B(መቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AxumUniversity
ማሕበረሰብ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጉዕዞ ናብ ወፍሪ መኸተ ወራር ዕስለ አንበጣ!
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የአምበጣ መንጋ የመከላከል ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ።

#ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአሜሪካ ዋሸንግቶን ዲሲ በሚካሄደው የሶሰትዮሽ ስብሰባ ላይ እንደምትካፈል አስታወቀች። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴት ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአሜሪካ ዋሸንግተን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ላይ ትሳተፋለች። የዋሸንግተኑ ስብሰባ ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አሜሪካ በአደራዳሪነት እንድትሳተፍ በቀረበ ጥያቄ መሰረት መዘጋጀቱ ተገልጿል።
(Ethio FM 107.8)

#AMBO አምቦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ እንዲሁም የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከተለያዩ የህበረሰት ክፍሎች ጋር ውይይት ከሚያደርጉበት አዳራሽ ፊት ለፊት ወጣቶች የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ። PHOTO: HA(አምቦ ቲክቫህ ቤተሰብ) @tsegabwolde @tikvahethiopia
#AMBO
ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ከተደጠረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ ጋር ለመወያየት አምቦ ከተማ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከወጣቶች በኩል ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ወጣቶቹ ከአዳራሹ ፊት ለፊት የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
PHOTO: H(አምቦ ቲክቫህ ቤተሰቦች)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ከተደጠረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ ጋር ለመወያየት አምቦ ከተማ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከወጣቶች በኩል ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ወጣቶቹ ከአዳራሹ ፊት ለፊት የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።
PHOTO: H(አምቦ ቲክቫህ ቤተሰቦች)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዶክተር ደረጄ ገረፋ ቱሉ...
"የመከላከያ ሰራዊት ህዝቡ ቁጣውን ካሰማ በኃላ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲገባ ተረጋግቶ እየጠየቀ ነው። መከላከያው ይህ አካሄዱ ይሰካለታል ቢዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ህዝቡም ይተባበራል ቢዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሁላችንም እሄ እንዲሳካ የበኩላችንን እናደርግ።"