TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNews

ይህ በማህበራዊ ሚዲያ በብዛት ሼር ሲደረግ የነበረ "ሀሰተኛ ዜና" ደግሞ አምቦ ከተማን የሚመለከት ሲሆን "በአምቦ ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቷል፣ ግርግርም አለ፤ ቤተክርስቲያንም ሊቃጠል ነው" የሚል ነው። አምቦ ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቅሴ ውስጥ ነው የዋለችው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እልቂት እንዲገባ የሚያነሳሱ ብዙ የፌስቡክ ሰዎች ስላሉ ከፍተኛ ማስተዋል እና ጥንቃቄ ይጠይቃል። በተለይም ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሚፃፉ ፅሁፎችን ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። የምትሰሙትን መረጃ ሁሉ ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ።

ሌላው አምቦ ከተማ ዛሬ "ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ታግተው ነበር፤ በሂሊኮፕተር ነው ያመለጡት" እየተባለ በተለያዩ ገፆች ሲወጡ የነበሩት መረጃዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው። ይህም ሆን ተብሎ ሌላ አከባቢ ያለው ህዝብ ለማነሳሳት እና ወደጥፋት ለመውሰድ የተደረገ ድርጊት ነው። የአምቦ ወጣቶች ጥያቄዎቻቸው፣ ቅሬታቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰምተው ወደየቤቶቻቸው እንደገቡ ቀን ገልጬላችሁ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች ላይ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አረጋግጧል።

የቦርዱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ቦርዱ የሚያውቀው እንዲህ አይነት ስምምነት የለም፤ ጭምጭምታዎችንም ቦርዱ አይሰማም ብለዋል።

(ETHIO FM- ትዕግስት ዘላለም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
EBC ዋልታ የሰራውን ዘገባ #FakeNews ብሎታል!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን አስታወቁ!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በሰጡት መግለጫ “90 በመቶ የሻፌታ ምልክት አሸነፈ” ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን ምክትል ከንቲባው ለኢቲቪ አረጋግጠዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተናገሩት “በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ መስጠቱን በየምርጫ ጣቢያዎች እየወጣ ያለው ውጤት ያሳያል፡፡” የሚለውን ነው፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNews🚨

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ከወራት በፊት መሰል የፈጠራና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የ #የሶማሊያ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሰሞኑን ዳግም የፈጠራ ወሬዎችን ፅፈው ማሰራጨትን ይዘዋል።

እያሰራጩ ካሉት ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ አንዱ " በአዲስ አበባ የተለየ ሁኔታ እንዳለ ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደጨመረ፣ በየቦታው ወታደሮች እንደተበተኑ " የሚገልጽ ነው።

ይህ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ አንዳችም የተለየ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ምንም እንኳን ጉዳዩ ውሸት ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ሀሰተኛ መረጃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ፣ እያጋሩት እንደሆነ መመልከት ተችሏል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ።

#AddisAbaba #Ethiopia

@tikvahethiopia