TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NEW

•ለራያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

•የጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎቹ የሚገቡበት ቀንን ይፋ አድርጓል።

•የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት ተማሪዎች ቅሬታ

•ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል

•የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት የሚጠበቅበትን ውጤታማ ስራ አላከናወነም ተብሏል።

•አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአገር ውስጥ ባሻገር በምስራቅ አፍሪካም የልህቀት ማዕከል ለመሆን ፖሊሲዎችን ነድፎ እየተገበረ መሆኑን ገልጿል።

•የወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች መግቢያ ይፋ ተደርጓል።

•የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎችን አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን በTIKVAH-MAGAZINE መከታተል ትችላላችሁ!

Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethmagazine
2
ወደከፋ ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል!

የቱርክ ወታደሮች በሰሜናዊ ሶሪያ ዘመቻ ጀምረዋል፤ ይህም በአሜሪካ ከሚደገፈው የኩርዲሽ መር ጦር ጋር ወደ ከፋ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጅማሮውን ‹‹ሠላማዊ ቀጣና የመፍጠር ዘመቻ›› ብለውታል፡፡

በዘመቻውም የኩርድ ታጣቂዎችን ከቀጣናው ለመደምሰስ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡ በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ኃይልም ንጹኃን በቱርክ የአየር ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአወዛጋቢ ሁኔታ ወታደሮቻቸውን ከሰሜን ሶሪያ ማስወጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ትራምፕ ወታደሮቻቸውን ከአካባቢው ያስወጡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከኤርዶሃን ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ መሆኑ ደግሞ ትችት እያስከተለባቸው ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ/አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ንቁ!

በፎቶው የምትመለከቱት ሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ የሚገኘውን "የኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ሙዚየም" ነው። ይህን ለሰው ልጆች ሁሉ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥን ሙዚየም የጎበኘ አንድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ይህን ብሏል፦

"ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ይሁነን፤ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል። ይሄ ታሪክ ተደግሞ ተገዳድለው አለቁ የሚባል ሙዝየም ለማሰራት አንደርደር። በአንድነት እና በፍቅር ስለመኖራችን ለልጆቻችን ሃውልት እናቁም!"

#ሼር #share

PHOTO: D/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሡዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ!

የሡዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ እንዲሁም የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
😱1
#GELAN

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ በ42 ሚሊዮን ብር የተገነባ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡ ፋብሪካው በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን የተገነባ ነው፡፡ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል።

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪርና የሶማሊያው ፕሬዝዳን ሙሐመድ አብደላሂ በአንድነት ፓርክ ምረቃ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንድነት ፓርክ ዛሬ ይመረቃል!

በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራው የአንድነት ፓርክ በዛሬው እለት ይመረቃል። በዛሬው እለት የሚመረወቅ የአንድነት ፓርክ የመደመር እሳቤ ማሳያ ነው ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፥ ያለፉትን ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶቻችን እየዘከርንና ለመጪው ትውልድ እያጎለበትን እንሂድ ሲል ጋብዟል። አንድነት ፓርክ ለጋራ ግባችን በአንድነት ቆመን የፍፃሜውን ምዕራፍ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ የሕብረት አቅም ማጠናቀቅ የመቻላችን ተምሳሌትም ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በዛሬው እለት የሚመረቀው የአንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት የሚደረግ ይሆናል። በዚህም መሰረት በነገው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራውን የአንድነት ፓርክ የሚጎበኙ ይሆናል። ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ በእድሜ ታላላቅ ዜጎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤተ መንግስቱን ይጎበኛሉ። ከሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት እንደሚችልም ተገልጿል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መንገደኞች የሚጓዙት #በመከላከያ ታጅበው ነው" - የማዕከላዊ ጎንደር ኮሙኒኬሽን

ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተለይ ጭልጋ አካባቢ በቅማንት የማንነት ጥያቄ አስመላሽ ኮሚቴና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት በዞኑ ማህበራዊ አገልግሎቶችና መንገዶች እስከመዘጋት መድረሳቸው ይታወሳል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ጌታሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግጭቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች መካከል ቢያንስ በሶስት ወረዳዎች እስከ አሁን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል።

አቶ ሃብታሙ እንደሚሉት "በዞኑ ከሶስት ወረዳዎች ውጭ ሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየተከናወነ ይገኛል"። እንቅስቃሴው የተገደበባቸው ሶስቱ ወረዳዎችም ጭልጋ ነባሩ፤ ጭልጋ አዲሱ (በቅማንት የራስ አስተዳደር የተካለለው) እና አይከል ከተማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-10

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

12ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በአል የፊታችን ሰኞ እንደሚከበር ተገለጸ። ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት 12ኛው የሰንደቅ አላማ በዓል የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓም “ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ በተለያዩ ዘግጅቶች ይከበራል ተብሏል።

Via ETHIO FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የብ/ጀ አሳምነው ጽጌ ባለቤት ደስታ አሰፋ በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ከጥብቅ ማሳሰቢያ ጋር ምርመራውን አጠናቆ እንዲያመጣ ለፖሊስ በድጋሜ 28 ቀን ተፈቅዶለታል።

Via Samrawit Lemma
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኬኒያው ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ!

የኬኒያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ የሚመረቀው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአፋር ክልል በርካታ የቀድሞ አመራሮች እና አንዳንድ ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ተሰምቷል። የጉዳዩ መነሻ ሶስት አወዛጋቢ ቀበሌዎች የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ስልጣን ላይ እያሉ ወደ አፋር ክልል መካተታቸው ነበር። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ጭምር በተገኙበት ነበር። በቅርቡ ደግሞ የሶማሌ ክልል እነዚህ ቀበሌዎች…
የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ከአፋር!

ከሰሞኑ የተሰራጨው መረጃ የተዛባ ነው፤ ከሁለቱም ወገን ያማከለ አይደለም ሲሉ በአፋል ክልል የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። ስለሁኔታውም ተከታዩን ብለዋል፦

----
በአፋር ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት የቀድሞ አመራሮችና ባለሀብቶች መኖራቸው #እውነት ብሆንም የተያዙበት ምክንያት ግን ከአፋር-ሱማሌ(ኢሳ) ጉዳይ ምንም የሚያገናኘው ነገር የለውም። የተያዙት ከአፍዴራ ጨው አምራቾች ማህበር (ከዳባ) ጋር በተገናኘ ስሆን ከተሰሩት ውስጥ አፋር የልሆኑም ይገኝበታል። እስሩ አሁንም እንደቀጠለ ስሆን እስካሁን ከመንግስት በኩል ግልፅ የሆነ መግለጫ አልተሰጠበትም።

የአፋር–ሱማሌ(ኢሳ) ግጭት በተመለከተ ግን ለ 80+ አመታት የዘለቀ ግጭት ሲሆን ያሁኑ ግጭት መንስኤው ከኢሳ በኩል ያሉ አንዳንድ አካላት የአፋርን ባንድራ አውርዶ በማቃጠል "በአፋር ክልል ስር አንተዳደርም" በማለታቸው ነው። ግጭት ከተጀመረ አሁን 9ነኛ ወር የያዘ ሲሆን ከመንግስት በኩል የተሰጠ #መፍትሔ የለም። ባለፈው ሳምንት በተፈጠረው ግጭት ከአፋር ወደ 30 ሰው እንደሞተ ተደርጎ የተዘገበው የተገጋነነ ዘገባ ነው። የሞቱት ከአፋር በኩል 7 ሲሆን 3 ቆለዋል። ግጭቱ አሁን መልክ እየቀየረ እስከ ጅቡቲ ደረስ እየዘለቀ በመሆኑ ከመንግስት በኩል አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው የቀጠናው ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን መታወቅ አለበት።"
------

በዚህ አጋጣሚ ከመንግስት በኩል ምንም ይፋዊ ነገር ባለመገለፁ፤ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ያልተረጋገጡ ናቸው፤ የሟቾች ቁጥርም በተለያዩ አካላት የሚገለፀው የተለያየ ነው። በአካባቢው የሚገኙ TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጉዳዩን እየተከታተሉ መረጃዎችን ያደርሱናል።

የመንግስት ዝምታ ግን🤔

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የትራፊክ አደጋ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ ነው!

TIKVAH-ETH ጂንካ ቤተሰቦች፦

''እባካችሁ እንጠንቀቅ! በተለይ አሽከርካርዎች! ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አደጋ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ ከጂንካ 32 Km ርቀት ላይ አንድ ዶልፊን ሚኒባስ ከአይሱዙ መኪና ጋር ተጋጭተው የደረሰ አደጋ ሲሆን በዶልፍን ተሳፍረው ከነበሩ 19 ሰዎች የሁለቱ ህይወት ወድያውኑ ሲያልፍ ለሎች ላይ አባድና ቀላል አደጋ ሊደርስ ችሏል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከከተማ ተወካዮች ጋር በሰለማዊ መማር ማስተማር ዙርያ ውይይት ኣካሄደ!

ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በሃገሪቱ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ሰለማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የሚያከናውኑ ዩኒቨርስቲዎች ኣንዱ ነው። የዩኒቨርስው ሰላማውነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለኣንደኛ ኣመት ተማሪዎች ለሚደረግላቸው ደማቅ ኣቀባበል ዙርያ ከከተማው የተወከሉ የሃይማኖት መሪዎች፣ ያገር ሽማግሌዎች፣የፀጥታ ተወካዮች፣ የተለያዩ ማሕበራት ተወካዮች፣ የከተማውና የዞኑ የስራ ሓላፊዎች በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዷል።

ውይይቱ የመሩት የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ እንደተናገሩት የዩኒቨርስቲው ሰላም ካለ የከተማው ማሕበረሰብ እገዛ የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ሕብረተሰቡ እንደተለመደው ተማሪውቹ በከተማ ሲንቀሳቀሱ የእንግድነት ስሜት እንዳይሰማቸው እንዲሁም ኣንደኛ ኣመት ተማሪውች በሚገቡበት ወቅት ደማቅ ኣቀባበል በማድረግ ከተማውና ዩኒቨርስቲው እንደ ሁለተኛ ቤታቸው እንዲያዩት ለማድረግ የከተማው ማሕበረሰብ እንደሁልጌዜ ከዩኒቨርስቲው ጎን በመሆን መስራት እንዳለበት ፕረዚዳንቱ ኣሳስቧል።

የከተማው ግዝያዊ ከንቲባ ኣቶ መንግሽ በበኩላቸው የከተማው መስተዳድር የዩኒቨርስቲ ሰለማዊ መማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር እንደ መደበኛ ስራው እንደሚሰራ በመድረኩ ተናግርዋል።

የከተማው ተወካዮችም ዩኒቨርስቲው ለከተማው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የጀርባ ኣጥንት እንደመሆኑ ኣንፃር ሕብረተሰቡም ወደ ዩኒቨርስቲው ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ ተማሪዎች ምንም ችግር ሳይገጥማቸው ተምረው እንዲመለሱ ኣጠንክረው እንደሚሰሩም በውይይቱ ሃሳባቸው ገልፅዋል።

ምንጭ፦ አቶ ዮሃንስ ከበደ/የዩኒቨርስቲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia