በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና የሞት አደጋ አደረሰ!
በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ከተማ የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪና ከጥንቃቄ ጉድለት ቅዳሜ ዕለት በአንድ ሰው ላይ የሞት አደጋ ማድረሱን የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ማስቆም ዳይሬክቶሬት የመረጃ ትንተና ባለሙያ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ ገልጸዋል፡፡
አደጋው የደረሰው ሁለት የጭነት ኤፍ ኤስ አር መኪናዎች በተከታታይ ቆመው ከነበሩበት የአንደኛው መኪና ረዳት መኪናውን ሲያንቀሳቅስ በፈጠረው ስህተት የሌላኛውን ኤፍ ኤስ አር መኪና መስተዋት በመወልወል ላይ በነበረው ረዳት ላይ አሰቃቂ አደጋ በማድረሱ የረዳቱ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ መክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ አስረድተዋ፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን የሞት አደጋ ጨምሮ በደቡብ ክልል ከባለፈው መሰከረም 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአራቱ ቀናት ብቻ 13 ያህል የትራፊክ አደጋ መድረሳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ከ13 አደጋዎች 5ቱ የሞት 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳትና ሁለት ቀላል የአካል ጉዳት ያስከተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአብዛኘው የአደጋ መንስኤዎች ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፣ የአሽካርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለትና ፍጥነት ናቸው፡፡ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ ፍጥነታቸውን ገድበው ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ምክትል ሳጅን ተመሰገን አረጋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

October 8, 2019
#DIREDAWA
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ከችጉንጉኒያ ወረርሽ ስጋት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በከተማው ለወራት በዘለቀውና ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያጠቃው ወረርሽኙ ከእረፍት እየተመለሱ ባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ላይም ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡
የቺኩንጉኒያን ወረርሽኝን ለመከላከል በተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች መድሃኒት መረጨቱን የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በድሬ ዳዋ ከአንድ ቤት ከ2-4 ሰዎች በወረርሽኙ እንደተያዘ የተገለጸ ሲሆን መንግስት ጉዳዩን በአጽኖት እንዲመለከተው የህክምና ባለሞያዎች እየጠየቁ ነው፡፡
ከድሬ ዳዋ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የድሬ የበጎ ፍቃድ የህክምና ባለሞያዎች ማህበር ወረርሽኙን ለመግታት የህክምና ዘመቻ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
Via Ahadu TV

በህገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በህገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በአገልግሎትና በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በአቅርቦት ችግር ሳይሆን የህገወጥ ደላሎች ጣላቃ ግብነት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ የዋጋ ንረቱ በተለይም በደሃው ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እያሰደረ ነው ብለዋል፡፡
ጥቂቶች አላስፈላጊ ንዋይ በመሰብሰብ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር አድርጓልም ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህገ- ወጥ ደላሎች አማካኝነት አየር በአየር በመኪና ላይ ህገወጥ ግብይት ሲያካሂዱ የተገኙ 59 መኪኖች አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 52 መኪኖች ጤፍና ሌሎች እህሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ጠቁማዋል፡፡
የቁጥጥርና እርምጃ የመውሰድ ስራ በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡ ደላሎችን ከግብይት ሰንሰለት ውጪ በማድረግና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራቾችና ተጠቃሚዎች በቀጥታ የሚገናኙበትን አግባብ ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ የረጅም ጊዜ እቅድ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ግብፅ በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ላይ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ ነው!
ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ከመግባባት ላይ መድረስ እየተቻለ አይደለም አለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበርያ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት በግድቡ ሁለንተናዊ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር በዛሬው እለት የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የግድቡ ግንባታ ያለበትን ደራጃ እና የታችኛው ተፋሰስ አገራት የሶስትዮሽ ውይይት ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-08
Via #FBC

#UPDATE በጣሊያን የባህር ጠረፍ ሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ከነበሩ መካከል የ13 ሴቶችን አካል የጣሊያን የባህር ጠባቂዎች ማውጣታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን አፍሪካ በድረ ገጹ አስነብቧል። ለስደተኞቹ ሞት በከፍተኛ አየር ጠባይ ለውጥ የተሳፈሩባት ጀልባ በደቡባዊ የሲሲሊ ደሴት ላምፔዱሳ ጠረፍ አካባቢ መስመጧን ተከትሎ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ከተረፉት አንዷ ለሲ ጂ ቴኤን እንደተናገረችው በአደጋው እህቷንና ሌላ የስምንት ወር የእህቷን ልጅ እንዳጣች በሃዘን በተሰበር ልብ ተናግራለች፡፡
Via CGTN/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via CGTN/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 8, 2019
የጤና ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማና ግብ ለኅብረተሰቡ በቀላሉ ለማድረስ የሚያስችለውን አዲስ መለያ ዓርማና መሪ መልዕክት ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል።
@tsegsbwolde @tikvahethiopia
@tsegsbwolde @tikvahethiopia
October 8, 2019
#JimmaUniversity
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በ2011 ዓም የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ስነ-ስርዓት አካሔደ፡፡ በዚህ ስነስርዓትም ላይ አራት ነጥብ ያመጡ 53 ተማሪዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚሁ መካከል ስምንቱ አስሩንም የትምህርት አይነት “A” ያስመዘገቡ ናቸው፡፡
በዕውቅና ዝግጅቱ ላይ የተገኙት #የጅማ_ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ተማሪዎች ጠንክረው በመስራት ለወደፊቱም የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉና ለሌሎች ተማሪዎች አርዓያ በመሆን ጓደኞቻቸውንም ለጥሩ ውጤት እንዲያበቁ፣ የምክርና የሞራል ድጋፍ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ተማሪዎቹን ለአመርቂ ውጤት ላበቁ መምህራን ምስጋናቸውን በማቅረብ ወደፊት ትምህርት ቤቱን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
በዝጅቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዩጭ ም/ፕሬዘደንት ዶ/ር አዱላ በቀለ በበኩላቸው የመምህራንን አቅምና ጥረት መደገፍ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባለፍ ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራ እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎችና በተማሪዎቹ ለተመረጡ 3 መምህራን የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
Via Jimma University

የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ...
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ምንጮች ገልፁልኝ ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።
የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር በዋቢነት የጠቀሰው 'The Times Of Israel' /ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል/ “የኢትዮጵያው መሪ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው በመመለሱ ሂደት ዕገዛ ለማድረግ ተስማምተዋል” ሲል ነው ሰሞኑን የዘገበው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፅህፈት ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን የስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ጉዳይ እንዲያውም በሁለቱ መሪዎች ውይይት አልተነሳም ።
Via VOA የአማርኛው አገልግሎት

በድሬዳዋ ቀፊራና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች መንግስት የህግ የበላይነትን በማስከበር ሰላምን እንዲያረጋግጥ ባካሄዱት ሰልፍ ጠይቀዋል። በድሬዳዋ ቀፊራ፣ አምስተኛ፣ ገንደጋራ፣ ቀብረ ጆሌና ሌሎች አካባቢዎች የተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት የአደባባይ ሰልፍ ላይ እንዳሉት በሚኖሩበት አካባቢ የተደራጁ አካላት ሰርተው በሰላም እንዳይኖሩ እያደረጓቸው እንደሆነ ገልፀዋል። ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት “ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ተጥሰዋል፣ በሰላም እጦት ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት መላክ አልቻልንም” ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-08-2
Via #ENA

የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወስኗል!
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሃገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል በማለም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ዋጋ አሁን በስራ ላይ ያለው የመሸጫ ዋጋ በዚህም ወር ባለበት እንዲቀጥል ተወስኗል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 / 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ በሰጠው መመሪያ መሰረት ከመስከረም 28/ 2012 እስከ ጥቅምት 30/2012 ድረስ ተግባራዊ የሚሆነው ንተመን ይፋ አድርጓል፡፡
የአውሮፕላን ነዳጅ በመስከረም ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 25.56 በአለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 1ብር ከ07 ሳንቲም በመጨመር በሊትር ብር 26.63 እንዲሸጥ ተወስኗል።
ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

#update በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በቅጥር ግቢ ውስጥ በአዲስ መልክ በመገንባት ላይ ላለው አዲስ ቴአትር ቤት ከቅርስነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ታሪካዊ የህንፃው ክፍሎች እንደማይነኩ ተገልጿል። በኢትዮጵያ 60 ዓመታትን በብቸኝነት የብሔራዊ ቴአትር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ቴአትር ቤቱ በ1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የማስፋፊያ ግንባታ እየተደረገለት መሆኑ ይታወቃል፡፡
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 8, 2019
ተጠርጣሪው ለከፈተው ተኩስ በተወሰደ አጸፋ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ!
በደቡብ ጎንደር ዞን የጸጥታ ችግር በመፍጠር ተጠርጥሮ በህግ የሚፈለግ ግለሰብ በጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍቶ በአጸፋ ምላሽ ህይዎቱ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ብርሃኑ ገላው ለአብመድ እንደገለጹት የቀድሞ የፌዴራል ፖሊስ አባል እንደነበረ የሚታወቀው አስቻለው ደሴ የተባለው ግለሰብ 31 አባላትን በማደራጀት በዞኑ በሚገኙ ከተሞች በመንቀሳቀስ፣ መኪና በማስቆም እና ንብረት በመዝረፍ ተጠርጥሮ በህግ ሲፈለግ ነበር፡፡ ግለሰቡ በነፋስ መውጫ፣ በወረታ፣ በአዲስ ዘመን፣ በሊቦ ከምከም፣ በእብናት እና በሌሎች ወረዳዎች እየተንቀሳቀሰ ሰዎችን በማስፈራራት ንብረት ይዘርፍ ነበር በሚል ተጠርጥሮ እንደነበረም ነው ኮማንደር ብርሃኑ የተናገሩት፡፡
ከዚህ ባለፈም የአንድ የፖሊስ አባል ህይዎት በማጥፋት ተጠርጥሮ ሲፈለግ ነበር ብለዋል ኮማንደር ብርሃኑ፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበትና የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቶበት በማረሚያ ቤት የቆዬ ቢሆንም በሀገራዊ ይቅርታ ተጠቃሚ በመሆን ከእስር ቤት ወጥቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ህገ ወጥ ተግባሩን መቀጠሉን እና በክልሉ ሰኔ 15 ላይ በተፈፀመው የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የፖሊስ አባላት ግድያ ተጠርጥሮ በህግ ሲፈለግ መቆቱንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-08-3
Via #AMMA

ከሴኔጋል የተነሳው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ወደ ተነሳበት አየር ማረፊያ ተመልሶ ለማረፍ ተገደደ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET908 የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከሴኔጋል ዲአስ ከተነሳ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ተነሳበት አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን አየር መንገዱ አስታውቋል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑ ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ግልጽ ባያደርግም መንገደኞቹ በመጉላላታቸው ይቅርታ በመጠየቅ ሁሉም ተሳፋሪዎች በተለዋጭ በረራዎች ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።
ምንጭ፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET908 የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከሴኔጋል ዲአስ ከተነሳ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ተነሳበት አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን አየር መንገዱ አስታውቋል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑ ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ግልጽ ባያደርግም መንገደኞቹ በመጉላላታቸው ይቅርታ በመጠየቅ ሁሉም ተሳፋሪዎች በተለዋጭ በረራዎች ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።
ምንጭ፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
October 8, 2019
የአስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የጤና ሁኔታ!
ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ መንቀሳቀስ እና መናገር እንደጀመረ ተሰማ። ግለሰቡ በአሁን ሰአት በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ ነው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቡ በግድያው ቀን በነበረው ተኩስ አንድ አይኑን አጥቷል። አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የተባለው ይህ የጀነራሉ ጠባቂ ሰኔ 15 ግድያውን እንደፈፀመ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳለ ይታወቃል። የመንግስት አካላትም በወቅቱ ይህ ግለሰብ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሰንዝሮ ነገር ግን ቆስሎ በህይወት እንደተረፈ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ በጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በኩል የተጠየቀው የፌደራል ፖሊስ ፤አሁን ላይ ምንም ተጨማሪ መረጃ እንደሌለው፣ ሲኖር ግን ለህዝብ ይፋ እንደሚገረግ ገልጿል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/AP/