TIKVAH-ETHIOPIA
እፀገነት አንተነህ⬆️ "የ27 አመቷ የአየር መንገድ ሒሳብ ሰራተኛ እፀገነት አንተነህ ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሰራ በምታመራበት ወቅት #ጭካኔ በተሞላበት ወንጀል አቃቂ መንገድ ላይ ተገድላ ተጥላ ተገኘች። ፓሊስ ምርመራ ላይ ነው። ቀብሯ ዛሬ ተፈፅሟል። ቀለበት አድርጋ ሰርግ ለመደገስ ዝግጅት ላይ ነበረች።" ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት/#CAPITAL/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
እፀገነትን የገደሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወ/ሮ እፀገነት አንተነህን የገደሉ ሦስት #ተጠርጣሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ወ/ሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 30 አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የትራንስፖረት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ሟችን በባጃጅ ተሽከርካሪ ከሳፈሯት በኋላ አንቀው እንደገደሏት ተጠርጥረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሟችን አስክሬን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለዋት እንደተሰወሩ ነው ፓሊስ የገለፀው፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች አለመታወቁ የፖሊስን ስራ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ቀንና ሌሊት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በዘጠነኛው ቀን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ/ም ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙት መርተው አሳይተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ፒያሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዙን አስታውሷል፡፡ ህብረተሰቡም ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠት እና ምስክር በመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቆ ይህንኑን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህን #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ክትትል እንዳደረገና፤ ሦስቱን ወንጀል ፈፃሚዎች ወንጀሉን በፈፀሙ በዘጠነኛው ቀን መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia