TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የቢጫ ወባ ወረርሽኝን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ!

- በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን እነሞርና ኢኖር ወረዳ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ የቢጫ ወባ ህመም ምልክት የታየባቸው ሰዎች ሪፖርት ተደርጓል።

- የበሽታው ወረርሽኝ በየካቲት 24 የጀመረ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በበሽታው የተያዘ ሰው ሪፖርት የተደረገው መጋቢት 20 ነው።

- አጠቃላይ 86 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን 4 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።

- በወረዳው በሽታው በስፋት በታየባቸው አምስት ቀበሌዎች የቤት ለቤት ቅኝት የተካሄደ ሲሆን 1,275 ቤቶችና 2 ትምህርት ቤቶች በቅኝቱ ታይተዋል።

- ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 27,178 ሰዎች የቢጫ ወባ ክትባት ተከትበዋል።

- ወረርሽኙን በመጋቢት 20 #መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሪፖርት የተደረገ አዲስ ታማሚ #የለም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#መልዕክት

1. የፌስቡክ እና ዩትዩብ አድራሻ የለንም !

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚገናኙበት ወይም እርስ በእርስ መልዕክት የሚለዋወጡበት ምንም አይነት የፌስቡክ (Facebook) ሆነ ዩትዩብ-Youtube (አክቲክቭ) አድራሻ #የለም። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም አይነት የፌስቡክ ገፆች እና ግሩፖች እንዲሁም አክቲቭ የሆኑ ዩትዩብ አካውንቶች ቤተሰቡን አይወክሉም።

2. ማስታወቂያ እንሰራል ከሚሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ !

ቲክቫህ የድርጅት ባለቤት፣ ለተቋማት አመራር፣ የማርኬቲንግ ባለሞያ ለሆኑ የቤተሰቡ አባላት መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ የሚያመቻች ቢሆንም በፕሮግራምና በተመጠነ መንገድ ብቻ ነው። የተለያዩ ግሩፕ በቲክቫህ ስም ከፍተው ማስታወቂያ እንሰራለን የሚሉ አጭበርባሪዎች ናቸው። (በዚሁ አጋጣሚ የዚህ ዓመት ማስታወቂያ ያበቃ ሲሆን ከመስከረም 20/2015 ጀምሮ በአዲስ መልክ ይጀምራል)

3. ገንዘብ ከሚሰበስቡ ተጠንቀቁ !

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ውስጥ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይሰበሰብም፤ ለሰዎች እገዛ ሲሆን የሚነገረው እገዛውን የሚሹ አካላት አድራሻ ብቻ ነው። በቲክቫህ ቤተሰብ ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ አጭበርባሪዎች ናቸውና ተጠንቀቋቸው። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ከአባላት ጋር በተገናኘ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይጠየቅም አይሰበሰብም፤ ከገንዘብ ጋር የሚገናኝ ምንም ስራ የለም

4. የመልዕክት መቀበያ አድራሻ !

ይህ መልዕክት መለዋወጫ @tikvahethiopiaBOT ስላስቸገረ በአዲሱ @officialtikvahethiopiaBOT መልዕክችሁን ላኩ። ባለፉት ሳምንታት መልዕክት ልካችሁ ያልታየም በአዲሱ መቀበያ አልያም (0919743630) አሳውቁ።

5. የመማሪ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (አዲስ አበባ) ለማበርከት 0919743630 ይደውሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ #ድርድር ምንድነው ያሉት ? " ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ ይጀመራል። ይህንን ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አብዝቶ ይፈልገዋል። በዚህ ድርድር የሚሳተፉ ወገኖች ሁሉ የዛሬዋን ቀን እያሰቡ ፣ ከግጭት፣  ከጦርነት እንደማናተርፍ አውቀው ህግ እና ስርዓት ተከትለን ይቅር ተባብለን ሀገራችንን በጋራ ማነፅ እና መገንባት…
#ታንዛኒያ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ #ታንዛኒያ ገብተዋል።

አቶ ደመቀ በ4 የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ያደርጋሉ የተባለ ሲሆን የመጀመሪያውን ጉብኝታቸውን በታንዛኒያ ጀምረዋል።

ከታንዛኒያ በመቀጠል በኮሞሮስ ፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ጉብምት ያደርጋሉ ተብሏል።

አቶ ደመቀ ዛሬ ታንዛኒያ ከገቡ በኃላ #በዛንዚባር የሚገኘውን የአፄ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ታንዛኒያ ለጉብኝት ያመሩት ትላንት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ኦነግ ሸኔ " ሲሉ ከተጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር መንግሥት ነገ በታንዛኒያ ድርድር እንደሚጀምር ካሳወቁ በኃላ ነው።

አቶ ደመቀ የታንዛኒያ ጉዟቸው በ4 የአፍሪካ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉብኝት የመጀመሪያ ሀገር ከመሆኑ በዘለለ ይደረጋል ከተባለው ድርድር ጋር ይገናኝ እንደሆነ ወይም በዚህ ድርድር ላይ ይገኙ/አይገኙ የታወቀም ሆነ ይፋ የተደረገ መረጃ #የለም

@tikvahethiopia