TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ለጉብኝት ተከፈተ⬆️

የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ዛሬ #ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ ጳጉሜ 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ. ም. እሥር ቤቱ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማዕከላዊ እስር ቤት አድራሻ፡- ከጊዮርጊስ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መካከል ላይ ይገኛል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ...

"የሜሪጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር እና አምባሳደሮቿ ለአረጋዊያን እና ለህፃናት ለአዲስ አመት ለበዓል ማሳለፊያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ በከተማው ባሉ የንግድ ቤቶች እየዞሩ "አበባየሽ ወይ" ሲሉ ነበር።"

ፎቶው📸ሁሴን የገበያ አዳራሽ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኮምቦልቻ...

"የኮምቦልቻ ተወላጆች ከአዲስ አበባ #አርሂቡ ብለው የሰየሙትን የእርዳታ ድርጂት ለማስመረቅ እና ያስገነቡትን ቤተ መጽሀፍ እና የሃይስኩል አጥር ለማስመረቅ ትላንት ኮምቦልቻ ገብተዋል። ከማህበረሰቡ እና ከከተማ አስተዳደሩ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው።" Gad Medehen

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኮምቦልቻ...

"ዛሬ በኮምቦልቻ የተለያዩ ዝግጅቶች ይደረጋሉ። በዝግጅቶቹ ለመታደም ከመጡ ታዋቂ ሰዎች በጥቂቱ ከኮምቦልቻ ተወላጆች አርቲስ አለማየሁ እሸቴ፣ ኤደን ገብረህይወት፣ መሀመድ ሰይድ፣ ኮይስ አዛሉ ወይም ማክዳ ሃይሌ የመሳሰሉት ይገኙበታል። አለማየሁ እሸቴ የክብር አንባሳደር ነው የሱ ፊርማ ያረፈበት "አርሂቡ ኮምቦልቻ" የሚል ቲሸርት በመቶ ሃምሳ ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል እሁድ ለሚደረገው ሩጫ።" Gad Medehen

ፎቶ📸ፋይል/አርሂቡ ኮምቦልቻ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዘመን መለወጫ በዓል ገበያን #ለማረጋጋት በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዛ የፍጆታ ምርት ለሸማቾች መቅረቡን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ። ሸማቾች በበኩላቸው የገበያ ማረጋጋት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews "ይህ መረጃ ፈፅሞ #የተሳሳተ እንደሆነ እንገልፃለን።" የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#share #ሼር

የአርቲስት #ተዘራ_ለማ የቀብር ስነ ስርዓት - ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በ9፡ 00 ሰዓት ይፈጸማል። #RIP

ምንጭ፦ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappingNow

"የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚንስቴር ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በMagnolia Hotel ስለ ፍኖተ ካርታ እየተወያዩ ነው።" #ROm

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#በMagnoliaHotel የተደረገ የሚገኝ ውይይት⬆️

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጪው አመት አዲሱን የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትን ተግባራዊ ያደርጋሉ ተባለ፡፡ ተቋማቱ ይህንኑ አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡ ይህንን የተሰማው ሚኒስቴሩ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከግል ተቋማት ባለሀብቶችና ተወካዮች ጋር ሲመካከር ነው። በመድረኩ የተገኙት ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ተቋማቱ ወቅታዊነቱንና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት መስጠት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ የሰለጠነና ብቃት ያለው የሰው ሀይል እንዲኖር ጥራትና አግባብነቱን የጠበቀ ትምህርት ማዳረስ አማራጭ የሌለውና ለነገ የማይባል እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ከአሁን በኋላ ባለሀብቶች የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንዲኖራቸው ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡ይሁን እንጂ አሁን ያለው የግል ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በርካታ እንከኖች ያሉበት ነው ተብሏል፡፡ ያለ በቂ ቤተ ሙከራ ተቋማትን መክፈት፣ ለተማሪ ተኮር ትምህርት ትኩረት አለመስጠት፣ ለተማሪዎች ያልተገባ ውጤት መስጠትና የሚሰጡ ትምህርቶችን በተግባር አለመደገፍ ከተለዩት እንከኖች መካከል ይገኙበታል፡፡ በሌሎች አገራት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት ይልቅ ተመራጭና ውጤታማ ናቸው ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርትተው ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡

Via ShegerFM
ፎቶ: ROM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ዛሬ እየተደረገ በሚገኘው ስብሰባ ላይ የ2012 ዓ/ም የአዲስ እና የነባር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ በመስከረም ወር እንዲሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጠንክሮ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

ተማሪዎች ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅት አድርጉ!

Via RoMe የስብሰባው ተካፋይ/TIKVAH-ETH ቤተሰብ/

#TIKVAH_ETHIOPIA

🗓የመግቢያ ቀናትን በሚመለከት ከሚኒስቴሩ እና ከዩኒቨርሲቲዎች የምናገኛቸውን መረጃዎች እናቀርባላን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሯቸው ተወያይተዋል። የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል።

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል። በለውጡ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በውይይቱ የተነሡ ሲሆን፥ በአንዳንድ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ ጥፋቶችን በማንሣት ጳጳሳቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም የእርሳቸውም ሆነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ሁሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መሆኑን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መጠናከርና አንድ መሆን ጥቅሙ ለእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሡ ሲሆን፥ ዓይነታቸው ቢለያይም የተለያዩ የእምነት ተቋማት በለውጡ ሂደት ፈተና አጋጥመዋቸዋል፤ በመሆኑም ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው ብለዋል።

https://telegra.ph/ETH-09-06-2

Via #PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሯቸው ተወያይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሲኖዶሱ ነገ መግለጫ ይሰጣል!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል። ከትላንት ጀምሮ አስቸኳይ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ሰራተኞች ስራ አቁመዋል!

ከቦነስ ይከፈለን ጥያቄ ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ሰራተኞች በዛሬው ዕለት የስራ እንዳቆሙ እዛው የሚሰሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የምስራቅ ኢትዮዺያ ኢሰማኮ ዋና ሀላፊ እና የናሽናል ሲምንቶ ሊቀመንበርን በስልክ ለማግኘት ያደርግነው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ አልተሳካም። ኃላፊውን እንዳገኘናቸው ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ ከ4ሺ 5 መቶ የሚልቁ ዜጎችን ህይወት እንደቀጠፈ ተገለፀ!

በ2011 በጀት ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ የ4ሺ597 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ እንዳለፈ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር ይህን የገለጹት ሚኒስቴር መስሪያቤታቸው “በጷጉሜ ስለ ትራፊክ ደህንነት እንነጋገር” በሚል መሪ ሃሳብ ከጳጉሜን 1-3/2011ዓ/ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ በከፈቱበት ወቅት ነው።

የትራፊክ አደጋው አገሪቱ ካላት አነስተኛ የተሽከርካሪ ቁጥር አኳያ ሲታይ እጅግ የከፋና አሳሳቢ በመሆኑ አፋጠኝ እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚገባ ዲኤታዋ ተናግረዋል።

Via #EPA
ፎቶ📸ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትና የአመራር ሽግሽግ አደረገ!

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ አደረገ። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባደረገው አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትና የአመራር ሽግሽግ አቶ መልካሙ ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ቦንቴ ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ኮሌኔል ሮዳሞ ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣ ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና አቶ ሀይለዮሐንስ ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርጎ መሾሙን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ዘግቧል።

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA

ሹመትና የአመራር ሽግሽግ፦

1. አቶ #መልካሙ_ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ #ቦንቴ_ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣

3. ኮሌኔል #ሮዳሞ_ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣

4. ምክትል ኮማንደር #ኢዮብ_አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና

5. አቶ #ሀይለዮሐንስ_ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ በትናንትናው እለት አድርጓል!

ምንጭ፦ ከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH MAGAZINE

በዋናው ቻናል በስፋት የማይዳሰሱትን ጉዳዮች የሚዳሰስበት ገፅ ነው። ይህም ዋናው ቻናል ላይ ያለውን የመረጃ ጫና በመቀነስ የቤተሰቡን አባላት ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋል!

ቲክቫህ ዩኒቨርስቲ
ቲክቫህ ቱሪዝም
ቲክቫህ ኢቨንት
ቲክቫህ ጥቆማ
👍የግቢ መግቢያ ፕሮግራሞችን ሳይደናገሩ ይከታተሉ

#TIKVAH_ETH በቅርቡ በኦንላይ መፅሄት ይመጣል!

👍አከባቢዎትን ያስጎብኙ
👍ባህሎን ያስተዋውቁ
👍ጠቃሚ ፕሮግራሞችን ያጋሩ
👍አስገራሚና አስተማሪ የምትሏቸውን ጹሑፎች፣ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ለሺዎች አጋሩ!

ይህን👇ተጭነው ለየት ወዳለው ቤታችን ይቀላቀሉ!
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#ድሬዳዋ

የጤና ሚኒስትር ዶክትር አሚር አማን በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር የችጉንጉንያ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚኒስቴሩ እና በከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ፡፡ የጤና ሚኒስትሩ በዚሁ ጉብኝታቸው ሚኒስቴሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተግረዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahiopia @tikvahethmagazine